ፈልግ

የቅዱስ ሉዊጂ ጎንዛጋ ምስል የቅዱስ ሉዊጂ ጎንዛጋ ምስል 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የዓለም ወጣቶችን ለቅዱስ ሉዊጂ በአደራ አቀረቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአምስተኛውን ክፍለ ዘመን ወጣት ቅዱስ ሉዊጂ ጎንዛጋን ባስታወሱበት የትዊተር ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው፥ ቅዱስ ሉዊጂ በእግዚአብሔር እና በባልንጀራ ፍቅር የተሞላ ወጣት እንደ ነበር እና የካቶሊክ ወጣቶች ጠባቂ መሆኑን አስታውሰዋል። በ 23 ዓመት ዕድሜ የያረፈው ሉዊጂ ከምቾት ሕይወት ይልቅ ቅዱስ ወንጌልን መሠረት በማድረግ በድህነት እና በበሽታ ከሚሰቃዩት ጋር ለመሆን የመረጠ ወጣት እንደ ነበር ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የወጣት ወታደር ሉዊጂ ታሪክ በሰለጠነው በዛሬው ዓለም ውስጥ የሰው ልጅ ክብር አልባነት መገለጫ ነው። ትንንሽ እጆች ኳስ ከመጫወት ይልቅ ጠመንጃ በመያዝ ሰውን ለመግደል ይሰለጠኑ ነበሩ። ከ 450 ዓመታት በፊት ሕጻን ልጅ የነበረው ሉዊጂ በ 5 ዓመት ዕድሜው የወታደር ትጥቅ ለብሶ በደስታ ይፈነድቅ እና በቦምቦች ይዝናና ነበር። ከለበሰው ዩኒፎርም እና ከጦር መሣሪያ በሚመነጭ የኃይል ስሜት ይደሰት የነበረው ወጣት ሉዊጂ የአባቱን የማርኪይስ ፌራንቴ ጎንዛጋ ፈለግ ይከተል ነበር።

ከነፍስ እና ከሰይፍ የቱ?

ብሩህ አዕምሮ የነበረው እና ጠንካራ ገጸ-ባህሪን ያሳይ የነበረው ወጣት ሉዊጂ፥ ከአባቱ እንደሚወርስ ከሚጠበቀው ባህሪዎች እና ከጠንካራ የፖለቲካ ችሎታው ጋር የአባቱን የማስተዳደር ችሎታ መውረስ ነበረበት። አባቱ ማርኪይስ ፌራንቴ ጎንዛጋ በሉዊጂ አዕምሮ ውስጥ የወታደራዊ መኰንንነት ፍቅር ቀስ በቀስ እንዲገባ ቢያደርግም የእምነት ሰው የነበረች እናቱ ማርታ ዲ ሳንቴና ያንን የልጇን ክፍት አእምሮ በተቃራኒ መንገድ መለወጥ ጀመረች። ሁኔታዎችን በፍጥነት ግምት ውስጥ በማስገባት ዓመፅ እና ደም ማፍሰስ ከነፍስ ጋር የተሳሰረ ስለ ነበር የሃሳብ ግጭትን አሸነፈ።

ከፍርድ ቤት እስከ ምንኩስና ልብስ

ከ10 ዓመት ዕድሜ በኋላ ሉዊጂ የወታደርነት ሕልም አልነበረውም። በጣሊያን ፍሎረንስ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርቦ እራሱን ለእመቤታች ቅድስት ማርያም ለማቅረብ ወሰነ። ማርያም እራሷን ለእግዚአብሔር እንዳቀረበች ማለት ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጦርነት ይልቅ ለጸሎት ያለው ፍላጎት እየጨመረ ሄደ። ከዓለም ቅንጦት ይልቅ ድህነትን መረጠ። 18 ዓመት እስኪሆነው ድረስ አባቱ አንዳንድ ቆነጃጅት አጣሚዎች ተጠቅመው እንዳያዘናጉት በማሰብ ወደ ጣሊያን ፍርድ ቤት ላከው። ነገር ግን ሉዊጂ ብኩርናውን በይፋ ለመተው ወሰነ። አባቱ በኃይል ተቆጣው፤ ዘመዶቹም አፌዙበት። ጉዳዩን ይከታተል የነበረው ጠበቃም ማመን አቃተው። የወንድሙ ሉዊጂ ምርጫ ለሁለተኛ ወንድ ልጃቸው ሮዶልፎ የወደፊት ሕይወቱ መልካም ዕድል ከፈተለት። ወጣቱ ሉዊጂ ለሚጠይቁት ሁሉ፥ “መዳን እፈልጋለሁ፤ እናንተም እርሱን እየፈለጋችሁት ነው! ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም፤ ምድራዊ መንግሥትን እያገለገሉ ራስን ማዳን በጣም ከባድ ነው” የሚል ሃሳብ ይዞ የኢየሱሳውያን ማኅበር ለመቀላቀል ወደ ሮም መጣ።

እግዚአብሔር ዕረፍቴ ነው!

በማኅበሩ ዘርዓ ክህነት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ መምህራን አባቶች ሉዊጂ ውድ ልጅ መሆኑን ወዲያው ተገነዘቡ። በውስጡ የነበረው ትዕቢት ንሰሐ እንዳይገባ እየተጫጫነው ቢሆንም በጸሎት እየበረታ ንሰሐ መግባት ይመኝ ነበር። የሚያስጨንቁ እና እግዚአብሔርን እንዳያስብ የሚያደርጉ ስሜቶችን ለማሸነፍ ምን ማድረግ እንዳለበት የገዳሙ አባቶች መንፈሳዊ ምክሮችን ይለግሡት ነበር። “ለመጸለይ ጥረት በማደርግበት ጊዜ ጭንቅላቴን እንዳልታመም በመፍራት የገዳም አለቆቼ እንዳልጸልይ ይከለክሉኝ ነበር። ነገር ግን በዚህ ሰላምን እና ዕረፍት አገኘሁ እንጂ ሕመም አልሆነብኝም” በማለት ሉዊጂ ተናግሯል።

"እንደ ሌሎች በወረርሽኝ መካከል ነበርኩ”

በዚያን ዘመን በሮም ከረሃብ በኋላ ኃይለኛ ወረርሽኝ ተከሰተ። ከተማዋ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአስፈሪ ሁኔታ የሚሞቱባት ቦታ ሆነች። በቫይረሱ ​​የተያዙ ሰዎችን በመርዳት ግንባር ቀደም የነበሩት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ስለነበሩ ሉዊጂም ከእነርሱ የተለየ አልነበረም። ከመኳንንት ቤተሰብ ቢወልድም በልቡ “እኔም እንደ ሌሎቹ” የሚል መፈክር ስለያዘ የነዋሪዎችን በሮችን እያንኳኳ በበሽታው የተጎዱ ሰዎችን ለመደገፍ ዕርዳታ ይለምን ነበር። አንድ ቀን የተቸገረ እና ብቻውን የቀረ ሰው አይቶ ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ተሸክሞት በጓዝ ጀመረ።

ወጣት ሉዊጂ ቀድሞውንም ታሞ ስለነበር ምናልባትም ያ የድፍረቱ እና የልግስና የመጨረሻ ምልክቱ ምንም ተጨማሪ ተስፋ ሳይሰጥ ሁኔታውን አባባሰው። ለኢየሱስ ክርስቶስ ጀርባውን ሳይሰጥ የተከተለው ሀብታሙ ወጣት፣ የጥንቱ ወታደር ወጣት ሉዊጂ እንደ ጎሮግሮሳውያኑ ሰኔ 21/1591 ዓ. ም. በ23 ዓመቱ አረፈ። የወቅቱ ር. ሊ. ጳ. ቤኔዲክቶስ 12ኛ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 1729 ዓ. ም. ቅድስናውን ይፋ አድርገዋል።

22 June 2023, 17:42