ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለአለም የወጣቶች ቀን ምልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለአለም የወጣቶች ቀን ምልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሊዝቦን የሚካሄደው የአለም የወጣቶች ቀን ተሳታፊዎች መልዕክት አስተላለፉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጪው ሐምሌ ወር ላይ በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን ለሚካሄደው ለዓለም ወጣቶች ቀን ተሳታፊ ወጣቶች የቪዲዮ መልእክት ልከዋል፣ እናም ከሌሎች ጋር ለመገናኘት እና በተስፋ እንዲያድጉ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የዓለም ወጣቶች ቀን (WYD) ሊከበር ከሦስት ወራት ያነሰ ጊዜ ስቀረው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሊዝበን ፖርቱጋል እ.አ.አ ከነሐሴ 1 እስከ 6/2023 በሚከናወነው ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ለተመዘገቡ ተሳታፊዎች ማበረታቻቸውን ልከዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሙስ ዕለት ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም በለቀቁት የቪዲዮ መልእክታቸው ወጣቶቹ ካቶሊካዊያን ለመጓዝ ሲዘጋጁ የሚሰማቸውን ደስታ አድንቀዋል።

“በአእምሮህ ውስጥ ሊኖርህ የሚገቡትን ነገሮች እንዴት ማድረግ እንዳለብህ መገመት እችላለሁ፡ ይህ እንዲሆን ማድረግ፣ የስራ ወይም የጥናት ፈቃድ፣ ለጉዞህ የሚያስፈልጋችሁን ነገሮች ለማግኘት የምታደርጉት ጥረት እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ አሳሳቢ ጉዳዮች” በአእምሮዋችሁ ውስጥ እንደሚመላለሱ አስባለሁ ብሏል።

በዚሁ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወጣቶች ደስታቸውን እና ተስፋቸውን እንደ መሰላል ድንጋይ በመጠቀም "ወደ አድማስ እንዲመለከቱ" አሳስበዋል።

በጉጉት ላይ የተገነባ ተስፋ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአለም የወጣቶች ቀን ላይ መሳተፍ "በሚፈጸሙ ክስተቶች ተስፋ ላይ የተገነባ "ቆንጆ ነገር" መሆኑን አምነዋል።

ለወጣቶቹ “በዚህ ግለት ራሳችሁን አዘጋጁ” ያሉ ሲሆን "ተስፋ ይኑራችሁ፣ ምክንያቱም አንድ ሰው እንደ የአለም ወጣቶች ቀን ባለው ዝግጅት ላይ ሲሳተፍ ብዙ ያድጋል" ብሏል።

እስካሁን ላያስተውሉት ይችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን ወጣቶቹ ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የመጡ ሰዎችን ሲያገኟቸው እና በጋራ እሴቶች ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ሲፈጥሩ አስደናቂ አዳዲስ ነገሮችን እንደሚያገኙ መጠበቅ ይችላሉ ብሏል።

ከአለም የወጣቶች ቀን በፊት ከአያቶቻችሁ ጋር ተነጋገሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቤተክርስቲያን "በወጣትነት ጥንካሬ" በመደሰት የተባረከች እንደሆነች ገልፀው በአለም የወጣቶች ቀን ላይ ያሉ ተሳታፊዎች ወደፊት ለሚጠብቃቸው ነገር በደንብ እንዲዘጋጁ ያበረታቱ ሲሆን እንዲሁም ለትክክለኛው ዝግጅት የሚሆን "ምስጢር" አካፍሏቸዋል።

“በደንብ ለመዘጋጀት” እንደ አያቶች ካሉ ከአዛውንቶች ጋር መገናኘት ሥር መሰረቶቻችሁን ለመመልከት ይረዳል ብሏል።

በሊዝበን በሚካሄደው የአለም የወጣቶች ቀን ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች አያቶቻቸውን “ምን ማድረግ አለብኝ ብላችሁ ታስባላችሁ?” ብለው መጠየቅ አለባቸው ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

የኛ የእድሜ ባለጸጎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ገለጹት ከሆነ “ጥበብን ይሰጣችኋል” ያሉ ሲሆን

እናም ወጣቶቹ በሊዝበን ሊያገኛቸው በጉጉት እንደሚጠባበቁ በመግለጽ ወጣቶቹ “ወደ ፊት ለመሄድ እንዲታገሉ” በማበረታታት የቪዲዮ መልእክታቸውን አጠናቋል።

04 May 2023, 13:09