ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከመንፈስ ቅዱስ ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ከመንፈስ ቅዱስ ማሕበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለስፕሪታን አባቶች እግዚአብሔርን በውስጣችን ስንፈቅድ አዲስ ነገርን ይፈጥራል አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተለምዶ ስፕሪታንስ በመባል የሚታወቁ (የመንፈስ ቅዱስ ማኅበር) ልኡካን ቡድንን ባነጋገሩበት ወቅት፣ መንፈሳዊ አባቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ሆነው ወንጌልን በመስበክ እና በማገልገል የሚያደርጉትን አስቸጋሪ ተልእኳቸውን አበረታተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በንጽሕት ድንግል ማርያም ንጹሕ ልብ ጥበቃ ሥር ለሚገኘው የመንፈስ ቅዱስ ማኅበር አባላት ንግግር ያደረጉት እንደ እግዚአብሔር እጅ “ሕዝቡን የሚንከባከብ፣ እያንዳንዳችሁን የሚንከባከብ፣ የርኅሩኅ አምላክ ነው” በማለት ፍቅራቸውን ገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን በተለይም የሃይማኖታዊ ሥርዓተ ክህሎትን አንዳንድ መሠረታዊ እሴቶችን አጽንዖት ሰጥተው ነበር የተናገሩት “አዲስ ነገርን ይሠራ ዘንድ ድፍረትን፣ ግልጽነትን እና የመንፈስን ተግባር መፈጸም ይኖርብናል” ብሏል። እ.አ.አ በ1848 ዓ.ም ከቅዱስ የማርያም ልበ ማኅበር ጋር የተቀላቀለው የመንፈስ ቅዱስ ማኅበር ዳግመኛ የተመሰረተበትን 175ኛ ዓመት ለማክበር በተዘጋጀበት ወቅት ነበር ከቅዱስነታቸው ጋር የተገናኙት።

የመጀመሪያው መሠረት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል እነዚህ እሴቶች በትእዛዙ የመጀመሪያ መሠረት ታሪክ ውስጥ ቀድሞውኑ በግልጽ እንደነበሩ አስታውቀዋል። የመንፈስ ቅዱስ ማሕበር መስራች፣ ያኔ ወጣት ዲያቆን፣ ከአስራ ሁለት የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ጋር፣ በመንፈስ ተነሳስተው፣ በድፍረት ያልተጠበቀ ማሕበር እንደ መሰረቱ ቅዱስነታቸው ገልጿል።

አባ ክላውድ ፍራንሷ ፓውላርት ዴስ ፕላስ “የወደፊቱን ጸጥ ያለ ተስፋ በመተው ከሀብታም ቤተሰብ የተገኘ ጥሩ ቄስ ብቻ ሊሆን ይችል ነበር - ገና ላልተገኘ ተልእኮ ራሱን ለመሥዋዕቶች፣ አለመግባባቶች እና ተቃውሞዎች በማጋለጥ፣ በጣም ደካማ ጤንነት ያለው ሕልሙን ሙሉ በሙሉ ዘውድ አድርጎ ከማየቱ በፊት ወደ መጀመሪያው ሞት መራው” ሲል ጳጳሱ አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብዙ ያልተጠበቁ ክስተቶች፣ የመንፈስን ተግባር መማር ህይወቱን ወደ ተከታታይ “ደፋር ቁርጠኝነት፣ እግዚአብሔር በእርሱ እና ከእርሱ እና በሌሎችም አዲስ ነገርን የጀመረበት” ሕይወትን እንደለወጠው ጠቁመዋል።

ሁለተኛ መሠረት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.አ.አ በ 1848 ስለ ተካሄደው ሁለተኛው የጉባኤው መሠረት ተናግሯል ። መንፈስ ቅዱስ "ህብረተሰቡ ያለፈውን ፍሬ በአዲስ ሁኔታ እንዲያካፍል ጠየቀ" ብለዋል ።

ይህ ጊዜ ከአዳዲስ ባልደረቦች ጋር የምንቀላቀልበት ጊዜ ነበር፡- የቅድስት ልብ ማርያም ማኅበር፣ ሚስዮናውያንም ነበሩ ነገር ግን የተለየ ታሪክ ያላቸው በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ይህን ለማድረግ በእርግጠኝነት ፍርሃቶችን እና ቅናትን ማስወገድ አስፈላጊ ነበር፣ እናም የሁለቱም ቤተሰቦች ወንድሞች ፈተናውን ተቀብለው ኃይላቸውን በማጣመር እና ያላቸውን አዲስ ጅምር ለማካፈል" በጋራ መሥራት መምረጣቸው የሚያስደንቅ ተግባር ነው ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግሯል።

ለመነሻቸው ታማኝ መሆን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከ175 ዓመታት በላይ በተዘረጋው በዚህ የበለጸገ ታሪክ ዛሬ “እኛ በመለኮታዊ ጥበቃ ለጋስ እና ደፋር ትምህርታቸውን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተሸለመ እናያለን፡ በአምስት አህጉራት ላይ በስልሳ አገሮች ውስጥ ይገኛሉ፣ 2,600 ካህናት እና ብዙ ተሳትፎ ያላቸው ምዕመናን ጋር አብረው በመሥራት ላይ የገኛሉ በሏል።

ማሕበሩ አድጓል በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ምክንያቱም አባላቱ ምንጊዜም ለተነሱበት መንፈስ ታማኝ ሆነው ይቆያሉ፡- “ድሆችን መስበክ፣ ሌላ ሰው መሄድ የማይፈልግበትን ተልእኮ መቀበል፣ በጣም የተረሱ አገልግሎትን መደገፍ፣ ሕዝብና ባህሎችን ማክበር፣ ሁሉም በወንድማማችነት እና በቀላል ህይወት እና በፀሎት ትጋት ውስጥ የአካባቢ ቀሳውስት እና ምእመናን በመፍጠር ለሰው ልጅ ሁለንተናዊ እድገት በመሥራት ላይ ይገኛሉ” ብሏል።

“የእናንተ ጨዋነት፣ ክፍት ልቦና እና አክባሪነት፣ በተለይ ዛሬ ውድ ነው፣” ሲል ተናግሯል፣ “የባህሎች እና የመደመር ተግዳሮት ህያው እና አጣዳፊ በሆነበት ዓለም፣ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እና ከእሱ ውጭ የምታደርጉት ተሳትፎ እጅግ በጣም የሚያስደስት ነው” ሲሉ ተናግሯል።

ጽናት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁ እያንዳንዱ ሰው ድፍረቱንና ውስጣዊ ነፃነቱን እንዳይተው ይልቁንም እንዲያዳብር እና የሐዋርያዊ ተግባራቸው መገለጫ እንዲሆን አሳስበዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሲያጠቃልሉ "ይህ የመስራቾቻችሁ ታላቅ ሀሳብ እና ከእናንተ በፊት የሄዱት የብዙ ወንድሞች እና እህቶች ውብ ምስክርነት ነው። እናም ይህ ደግሞ ዛሬ ለእናንተ ዛሬ የምነግራችሁ ምኞት እና ግብዣ ነው" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቋል።

 

 

10 May 2023, 13:31