ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር አባላት ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካቶሊካዊያን መምህራን ክፍት እና ሰብአዊ የሆነ አእምሮን እንዲፈጥሩ አበረታቱ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ የሆኑ መምሀራን ከርዕዮተ ዓለም አስተሳሰቦች አልፈው የጋራ ጥቅምን ማጎልበት የሚችሉ ወጣቶችን እንዲፈጥሩ አበረታተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ሁለንተናዊ” በሚል አስተሳሰብ “ካቶሊክ” የሆኑ ወጣቶችን ማቋቋም አለብን፣ “አእምሮ፣ ልብ እና እጅ እንፈልጋለን” በማለት ከርዕዮተ ዓለም ውስንነት ወጥተው የሰው ልጅ ቋንቋ የሚናገሩ እና የሁሉንም ባህል የሚያገናዝቡ እንዲሆን አበረታተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ሐሙስ ሚያዝያ 26/2015 ዓ.ም በቫቲካን ከእርሳቸው ጋር ለተገናኙት የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር አባላት ባደረጉት ንግግር፣ በሀብታሞች እና በድሆች መካከል እየጨመረ ያለውን ልዩነት እና በተለያዩ አገራት መካከል ያለውን ልዩነት በማሰብ የተናገሩ ሲሆን  “የተወደደውን” የላቲን አሜሪካን አህጉር እያሰቃየ የሚገኝ ኢፍታዊ ተግባራት እንደ ሚያሳስባቸው ገልጸዋል።

ኢ-እኩልነት፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች፣ የርዕዮተ አለም እና የፖለቲካ ዋልታ ረገጥነት አኅጉሪቱን ወደ ትርምስ የከተቷት ይመስላሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር እጅግ በሚያምርና በፈጠራ መንገድ የሚሠራበት ቦታ ነው” ብሏል።

አውታረ መረቡ

የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር በቺሊ ሊቀ ጳጳስ አልፍሬዶ ሲልቫ ሳንቲያጎ ከብዙ የካቶሊክ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የተቋቋመ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ 115 ዩኒቨርሲቲዎችን በማካተት ከአንድ ሚሊዮን ተኩል በላይ ተማሪዎችን፣ ከ110 ሺህ በላይ ፕሮፌሰሮችን እና 5 ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ የልህቀት ፕሮግራሞችን ይወክላል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር ተወካዮች በብሔራዊ እና ድንበር ተሻጋሪ አውድ ውስጥ "ከትምህርት ጋር በተያያዙ ፖሊሲዎች እንዲቀረጹ አስተዋጾ እንዲያደርጉ" አበረታቷቸዋል።

“ወረርሽኙ እና ውጤቶቹ በዓለም ዙሪያ የፖለቲካ እና ወታደራዊ አውዶችን አባብሰዋል ፣ ርዕዮተ ዓለም ዋልታ ረገጥነት የልማት ጥረቶች እና የነፃነት ፍላጎት በሮችን የሚዘጋ ይመስላል” ብለዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል እየታዩ ያሉት ቀውሶች የኢኮኖሚ ሥርዓቶችና ሞዴሎች ጊዜ ያለፈባቸው መሆኑን ለመገምገም ዕድል የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን፣ በርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሠረተ ጭፍን ጥላቻን የሚያባብሱና ወደ ባሕላዊ መገለል የሚያደርሱን መፍትሔዎች እንድንሻገር ያደርገናል ሲሉ ተናግሯል።

ስለዚህ ቅዱስ አባታችን እንደ የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር ያለ የኔትወርክ ሥራ ለጋራ ጥቅም መሥራት የሚችሉ “ካቶሊክ አእምሮዎችን” ማቋቋም ነው ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግሯል።

"ዩኒቨርሲቲ" የሚለው ቃል ከ "ዩኒቨርስ" ከሚለው ቃል የተገኘ ከሆነ - ሁሉም ነባር ጉዳዮች እና ቦታ በጠቅላላ ግምት ውስጥ ያስገባ "ካቶሊክ" የሚለው ቅፅል ይህንን ጽንሰ-ሐሳብ ያጠናክራል እና ያነሳሳ ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግሯል።

በትምህርት ላይ ያለው ጽኑ ዓለም አቀፍ አቋም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በስፓኒሽ ቋንቋ ባደረጉት ረዥም ንግግር ትምህርት የግለሰባዊ ባህል መድሐኒት እና የለውጥ ሂደት ይሆን ዘንድ በአንድነት እና በጋራ የወደፊት ራዕይ ላይ የተመሰረተ ተስፋ እንዲሰንቁ ተሳተፊዎቹን አበረታተዋል።

በዚህ ረገድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች ወንድና ሴት ምዕመናን “ሚስዮናዊ ልብ” ያላቸው እና “የሰው ልጅ” የሚለውን ቋንቋ ደጋግመው እንዲናገሩ የተማሩትን በተግባር ለመተርጎም በሚጥሩበት ጊዜ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ተናግሯል።

 

 

04 May 2023, 13:12