ፈልግ

Papa Francesco 'tennis e padel non perdano la loro amatorialit�'

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስፖርት ጥልቅ ስሜት መግለጫ ሆኖ መቀጠል አለበት ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሮም በተካሄደው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቴኒስ እና ፓዴል ሲምፖዚየም ተሳታፊዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን በስፖርትና በትምህርት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት አጉልተው ገልጸው ስፖርት ጨዋታ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አስታውሰዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 28/2015  በሮም በተካሄደው በስድስተኛው ዓለም አቀፍ ቴኒስ እና ፓዴል ሲምፖዚየም ላይ ከ30 በላይ አገሮች የተውጣጡ መምህራንን፣ ሕጻናትን እና ወጣቶችን በቫቲካን አነጋግረዋል።

ከሚያዝያ 28-29/2015 ዓ.ም የተካሄደው ዝግጅት በትምህርት እና ስልጠና ላይ ያተኮረ ነበር። ይህንን ወሳኝ ገጽታ በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው በስፖርትና በትምህርት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት አጉልተዋል።

በስፖርት እና በትምህርት መካከል ያለው ግንኙነት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት "የቴኒስ ወይም የፓድል አሰልጣኞች" የቴክኒኮች አስተማሪ ብቻ ሳይሆኑ እኔ ደግሞ ከሁሉም በላይ 'አስተማሪ' ናቸው እላለሁ ያሉ ሲሆን ስለሆነም በቦታው የተገኙት ሰዎች ለዚህ "ትምህርታዊ ገጽታ" ትኩረት መስጠቱን እንዲቀጥሉ አበረታቷቸዋል። እናም በፓደል ተጫዋቾች ልምድ ላይ በመመርኮዝ ጥሩ ጨዋታ "ከትክክለኛው የማጥቃት እና የመከላከል ሚዛን" ውጤት እንደሚገኝ ሀሳብ አቅርቧል ።

በስጋት እና በጥንቃቄ መካከል ያለው ሚዛን

ጥሩ የቴኒስ ወይም የፓድል ተጫዋች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት ከሆነ “ሁልጊዜ ዝም ብሎ ማጥቃት ወይም ስጋት ላይ ሊወድቅ እንደማይችል ጠቁመዋል። እሱ ወይም እሷ መከላከያን እንዴት እንደሚፈጥሩ ማወቅ አለባቸው ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ "በማጥቃት ላይ ወይም በመከላከል ላይ ብቻ የሚያተኩር አስለጣኝ ተማሪውን በሌላኛው በኩል 'ተጋላጭ'" ያደረገዋል ብሏል።

ስለዚህ "ጥሩ አሰልጣኝ ስጋትን እና ጥንቃቄን እንዴት ማመጣጠን እንዳለበት ያውቃል" ያሉ ሲሆን ስጋትን መቀበል ወይም መውሰዱ፣ ለምሳሌ፣ ልጆች ከዚህ በፊት ያላገኙትን አዲስ ልምድ እንዲኖራቸው መፍቀድ ነው፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ከአቅማቸው ጋር የሚመጣጠን መሆን አለበት ሲሉ አክለው ገልጿል።

"በሌላ በኩል እውነተኛ ጥንቃቄ እንደ ጥሩ መከላከያ ነው" እናም "በትምህርት ሥራ ውስጥ የእያንዳንዱን ወንድ ወይም ሴት ልጅ አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ሁኔታዎችን በትክክል ለመገምገም አስፈላጊ ነው" ብለዋል።

“አሰልጣኞች በተለይ ወጣቶችን በትዕግስት ማሰልጠን አለባቸው፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ እና በጣም አስቸጋሪ ለሚሆኑ ጥያቄዎች እንኳን ምላሽ ለመስጠት የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለባቸው፣ ምክንያቱም ፈጣን እና ቀልጣፋ ምላሽ ሌላውን ተጫዋች ስለሚያበረታታ ነው በማለት መናገራቸውም ተገልጿል።

የስፖርት አማተር መጠን

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሲናገሩ "ውድድር" ሁሉም የ'ጨዋታ' አካል ከሆነ ጤናማ ነው። አንዴ ሁሉም ነገር ፉክክር ከሆነ፣ የተለያዩ ራስን የማሳየት ዓይነቶች እየጎለበቱ ሲመጡ ግጭቶችን ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፣ በስፖርት ውስጥ አንድ ነገር አለ - በቴኒስም ሆነ በፓድል ወይም በማንኛውም ስፖርት -- በጭራሽ ልንሸነፍ አይገባም የሚለው አስተሳሰብ ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል፣ ስለዚህም ስፖርት ጨዋታ እና ፉክክር ሊሆን ይገባል እንጂ የጠብ እና የግጭት መንስሄ ሊሆን ይገባም ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አተናቀዋል።

 

06 May 2023, 11:02