ፈልግ

ፍልስጤማዊ-እስራኤል-ጋዛ-ግጭት ፍልስጤማዊ-እስራኤል-ጋዛ-ግጭት  (AFP or licensors)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በእስራኤል እና በፍልስጤም መካከል 'የተኩስ አቁም' እንዲኖር መጸለያቸው ተገለጸ!

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በእስራኤል እና በጋዛ ሰርጥ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በመጸለይ በቅድስት ሀገር የሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“መሳሪያ ዝም ይበል፣ ምክንያቱም የጦር መሳሪያዎች ደህንነት እና መረጋጋት ማስገኘት አይችሉም። ይልቁንም የሚሳካላቸው የሰላም ተስፋን ማጥፋት ብቻ ነው” ሲሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የተናገሩ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ደግሞ እሁድ ግንቦት 06/2015 ዓ.ም ለቅድስት ሀገር ሰላም በጸለዩበት ወቅት ነበር ይህንን ጥሪ ያቀረቡት።

እስራኤል እና እስላማዊ ጂሃድ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ታጣቂዎች ከማክሰኞ ጀምሮ በተካሄደው የእስራኤል የአየር ጥቃት ሶስት የቡድኑን ዋና አዛዦችን ከገደለ በኋላ ግጭቱ መቀስቀሱ የተገለጸ ሲሆን በግብፅ አደራዳሪነት የተፈረመው የተኩስ አቁም ስምምነት ቅዳሜ ተግባራዊ ሆኗል፣ እናም እሁድ እለት በይፋ እንደ የሚጀመር ይመስላል።

ስለ ሰላም የተደረጉ ጸሎቶች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእሁድ እለት “የሰላም ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የተሰኘውን ጸሎት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምዕምናን ጋር ከደገሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር “በእስራኤል እና ፍልስጤማውያን መካከል በተደረገው በጦር መሣሪያ የተደገፈ ግጭት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ንፁሀን ዜጎች ህይወታቸውን በማጣታቸው” የሰው ህይወት በመጥፋቱ አዝነዋል።

በጋዛ በጥቃቱ ምክንያት በትንሹ 13 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸው ተነግሯል፣ ከነዚህም መካከል እድሜያቸው 4 አመት የሆኑ ህጻናትን ጨምሮ ማለት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅርቡ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲኖር እና ሁለቱም ወገኖች መሳሪያቸውን እንደሚያስቀምጡ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል ።

“መሳሪያ ዝም ይበል፣ ምክንያቱም የጦር መሳሪያዎች ደህንነት እና መረጋጋት ማስገኘት አይችሉም። ይልቁንም የሚሳካላቸው የሰላም ተስፋን ማጥፋት ብቻ ነው” ብሏል።

 

15 May 2023, 11:51