ፈልግ

2023.05.12 Auditorium di via della Conciliazione: Stati Generali della Natalità

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ‘መልካም የእናቶች ቀን!’ እንዲሆን መመኘታቸው ተገለጸ!

ብዙ አገሮች የእናቶችን አለም አቀፍ ቀን እሁድ ግንቦት 06/2015 ዓ.ም ሲያከብሩ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸኮስ ሁሉንም እናቶች ለቅድስት ድንግል ማርያም በአደራ መስጠታቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ ቀን ሁሉም እናቶቻቸውን በአመስጋኝነት እንዲያስታውሷቸው አበረታተዋል። የእናቶች ቀን በግንቦት ወር ሁለተኛ እሁድ ላይ በብዙ አገሮች ይከበራል። ልጆችን ለወለዱ ሴቶች አድናቆታቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው ለእመቤታችን ጥበቃ አደራ ሰጥቷቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ሁሉንም እናቶች፣ አሁንም ከእኛ ጋር ያሉትን እና ወደ መንግሥተ ሰማይ የሄዱትን ሁሉ በአመስጋኝነት እና በፍቅር እናስታውስ" ብለዋል። "ለኢየሱስ እናት ለማርያም አደራ እንስጣቸው" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

“ሁሉንም እናቶች፣ አሁንም ከእኛ ጋር ያሉትን እና ወደ መንግሥተ ሰማይ የሄዱትን ሁሉ በአመስጋኝነት እና በፍቅር እናስታውስ። ለኢየሱስ እናት ለማርያም አደራ እንስጣቸው” ሲሉ በድጋሚ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት ደግሞ በግንቦት 06/2015 ዓ.ም በቫቲካን “የሰላም ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የተሰኘውን ጸሎት ካደረጉ በኋላ እንደ ነበረም ተግልጿል።

 

15 May 2023, 11:54