ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዘለኔስኪ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዘለኔስኪ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለዩክሬን ፕሬዝዳንት የወይራ ቅርንጫፍ ዝንጣፊ የሚያመለክት ስጦታ ሰጡ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪን ጋር በቫቲካን ማገናኘታቸው ተገልጿል። ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ ከጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ እና ከፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጋር በሮም ከተገናኙ በኋላ ነበር ከቅዱስነታቸው ጋር የተገናኙት።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የዩክሬይን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ አመሻሹ ላይ 4፡00 ላይ ወደ ቫቲካን የመጡ ሲሆን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ባደረጉት ቆይታ በቫቲካን በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ ውስጥ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

"ታላቅ ክብር ነው" ሲሉ የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ስለጉብኝቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን ያመስገኑ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች የውይይት ጊዜያቸውን ያሳለፉት በአስተርጓሚው በአባ ማርክ ጎንጋሎ ፖላንዳዊ ዜጋ እና በቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት በሚሰሩ ካህን አማካኝነት እንደ ነበረ ተገልጿል።  

ለ40 ደቂቃ ያህል የፈጀው ስብሰባ በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ በሰብአዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለፕሬዚዳንቱ ለሰላም በሚያቀርቡት በርካታ ይፋዊ ተመጽኖዎች እና ልመናዎች የተመሰከረላቸው የዘወትር ጸሎታቸውን አረጋግጠውላቸዋል።

ለህዝቡ የሚሰጠውን ሰብዓዊ ርዳታ ለመቀጠል በሚያስችሉ መስፈርቶች ላይ ተስማምተዋል ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለይም “ሰብዓዊ እንቅስቃሴ” በሚገታ መልኩ በግጭቱ ሰለባ ለሆኑ ንፁሀን ወገኖች “የሰብአዊነት ርዕራኄ” እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ፕሬዚዳንት ዘለኔስኪ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ፕሬዚዳንት ዘለኔስኪ በቫቲካን በተገናኙበት ወቅ

የስጦታ መለዋወጥ

እንደተለመደው ሁለቱ መሪዎች ስጦታ ተለዋወጠዋል።  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የሰላም ምልክት የሆነውን የወይራ ቅርንጫፍ የሚወክል የነሐስ ቅርጽ ያለው ስጦታ መስጠታቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና በአል-አህዛር ታላቅ ኢማም አህመድ አል-ታይብ እ.አ.አ 2019  የተፃፈውን ሰብዓዊ ወንድማማችነት ለአለም ሰላም እና አብሮ መኖር የሚዳስስ ሰነድ በስጦታ መልክ አበርክተዋል። እ.ኤ.አ. በመጋቢት 27/2020 በላቲን ቋንቋ “ስታቲዮ ኦርቢስ” (የዓለም ጣቢያ) በተሰኘ አርእስት  የተጻፈ መጽሐፍ እና ስለዩክሬን ሰላም በተመለከተ የጻፉትን ሐዋርያዊ መልዕክት በስጦት አመልክ አቅርበዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ለብፁዓን ጳጳሳት ከጥይት መከላከያ ሰሃን የተሰራ የጥበብ ስራ እና በግጭት ወቅት ህፃናትን ሲገድሉ የሚያስይ “ኪሳራ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን ሥዕል በስጦት መልክ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለፕሬዚዳንት ዘለኔስኪ ከሰጡት ስጦታ መካከል አንዱ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለፕሬዚዳንት ዘለኔስኪ ከሰጡት ስጦታ መካከል አንዱ

ከሊቀ ጳጳስ ጋላገር ጋር የተደረገ ግንኙነት

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ተከትሎ ቫቲካን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ጋር መገናኘታቸው ተገልጿል።

"ከሊቀ ጳጳስ ጋልገር ጋር በተደረገው መልካም ውይይት በመጀመሪያ ትኩረቱ በዩክሬን ስላለው ወቅታዊ ጦርነት እና ከሱ ጋር ተያይዞ በተከሰቱት አስቸኳይ ጉዳዮች በተለይም በሰብአዊነት ጉዳዮች ላይ እንዲሁም ሰላምን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት መቀጠል አስፈላጊ በመሆኑ ላይ ነው" መግለጫው አክሎም “በአጋጣሚው በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች በተለይም በሀገሪቱ የምትገኘውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ሕይወት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየቱ አስደሳች ነበር” ብሏል።

ፕሬዚዳንት ዘነሌስኪ ከሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ጋር በተገናኙበት ወቅት
ፕሬዚዳንት ዘነሌስኪ ከሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ጋር በተገናኙበት ወቅት

በሊቀ ጳጳሱ እና በዜለንስኪ መካከል የተደርገው ሁለተኛ ስብሰባ

የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ  አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ሮም አቅነተው እ.አ.አ በየካቲት ወር 2020 ዓ.ም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚያ አጋጣሚ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዱስ ማርቲን ዴ ቱርስ ምስል የሰፈረበት ሜዳሊያ ለፕሬዚዳንቱ በስጦታ መልክ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ ቅዱስ በምሥራቃዊው ዓለም በጦርነት እየተሰቃዩ ያሉትን የዩክሬን ሕዝብ እንዲጠብቅ ያላቸውን ተስፋ በወቅቱ መግለጻቸው ይታወሳል።

የዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ከካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን እና ቫቲካን ከአገራት እና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ጋር ተወያይተዋል።

የቅድስት መንበር የፕሬስ ጽ/ቤት መግለጫ በዚሁ ወቅት እንዳስታወቀው ውይይቱ በሰብአዊ ሁኔታ እና በዩክሬን እ.አ.አ ከ 2014 ጀምሮ ባለው ግጭት ውስጥ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ ያተኮረ ነው ብሏል።

በዚህ አጋጣሚ ሁሉም የሚሳተፉት ወገኖች በሁከቱ ለተጎዱት የህዝብ ፍላጎቶች ከፍተኛ ትብብር እንዲያሳዩ እና "በንግግር ውስጥ ያለውን ቁርጠኝነት እና ቅንጅት" እንደሚያሳዩ ተስፋ ተሰጥቷል ።

የስልክ ጥሪዎች

የመጀመሪያው የተከሰተው ጦርነቱ ከጀመረ ከሁለት ቀናት በኋላ እ.አ.አ. የካቲት 26 ቀን 2022 ነበር። በዚያ አጋጣሚ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለፕሬዚዳንቱ “በአገራቸው እየተከሰቱ ባሉት አሳዛኝ ክስተቶች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን” ተናግረው ነበር።

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና በዩክሬን ፕሬዚዳንት መካከል ሌሎች የስልክ ጥሪዎች እ.አ.አ በመጋቢት እና በነሐሴ 2022 ተካሂደው ነበር፣ በዚያን ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለዩክሬይን ሕዝብ ስቃይ እና ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለዘለንስኪ ስቃይ ያላቸውን ስጋት እና ሀዘን በድጋሚ ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

13 May 2023, 22:42