ፈልግ

cq5dam.thumbnail.cropped.1500.844.jpeg

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት እንዲጀመር ድጋፍ ሰጡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት (የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት ዓላማው ለአዳዲስ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ፖሊሲዎች፣ ለአካባቢው አዲስ አገልግሎቶች እና የሐዋርያዊ አገልግሎቶች እንቅስቃሴዎችን ከቤተሰብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር ለማስተሳሰር ያቀደ የስራ አጀንዳ ነው። ከቤተሰብ ጥናትና ምርምር ጋር በተያያዙ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል እና በእነርሱ እና በልዩ አብያተ ክርስቲያናት የቤተሰብ ሐዋርያዊ እንክብካቤ መካከል ያለው "ዓለም አቀፍ ስምምነት" ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች ጋር ሲነፃፀሩ ብዙ ሀብቶችን ፣ሌዕቃን ፣ድርጅታዊ እና የገንዘብ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ የሚያነቃቃ ይሆናል ። የምርምር ቦታዎች ስለሆኑም ጭምር። "በሲቪል እና በሐዋርያዊ እንክብካቤ አካባቢ ለቤተሰቦች መልካም የአገልግሎት ልምዶችን ለማዳረስ" የሚደግፍ እና "ቤተሰብን እውነተኛ ማኅበራዊ ርዕሰ ጉዳይ በማድረግ ቤተሰብን የህብረተሰቡ ዋና ገጸ ባህሪያት" የሚያደርግ ስምምነት። ለሁለት ዓመታት በሚጠጋ ሥራ ሰነዱን ያዘጋጁት የቤተሰብ፣ የምመናን እና ሕይወት ጉዳዮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ዋና ጽሕፈት ቤት እና ጳጳሳዊው የማኅበራዊ ሳይንስ አካዳሚ አማካኝነት ይፋ የሆነ ሰነድ ነው) የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት ማስጀመሪያ ላይ  ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በቤተሰብ ላይ የጥናት እና የምርምር ማዕከላት ጋር በመተባበር ለቤተሰብ ስለሚደርገው ሐዋርያዊ  እንክብካቤ ላይ ውይይት ለማድረግ ዓላማ ላለው ተነሳሽነት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቤተሰብን ደኅንነት ለመደገፍ “ለዓለምና ለቤተ ክርስቲያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወሳኝ” በሚል የተጀመረውን የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት ያላቸውን ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማክሰኞ ግንቦት 22/2015 ቀን ባስተላለፉት መልእክት የሰነዱ ጥራዝ ግቦችን አወድሰዋል።

በውይይት የሚደረግ የሐዋርያዊ እንክብካቤ

የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት በተለይ ቤተሰቦች ዛሬ የሚያጋጥሟቸውን አዳዲስ ፈተናዎች በማሰብ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተሰብ ጥናትና ምርምር ማዕከላት ላይ የቤተሰብን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ወደ ውይይት ለማምጣት ያለመ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመልእክታቸው "በተለይ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች የሐዋርያዊ እንክብካቤን በካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች ከሚደረጉ የምርምር እና የትምህርት እና የሥልጠና መርሃ ግብሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል" ግቡ ለሁለቱም የሚጠቅም ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዩኒቨርሲቲዎችን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት መርሃ ግብሮችን አንድ ላይ በማጣመር የቤተሰብ እና የህይወት ባህልን በዚህ እርግጠኛ ባልሆነ እና በጭንቀት ጊዜ እንዴት እንደሚያሳድጉ አስተውለዋል። ተስፋው ዛሬ ሰዎችን ማረጋገጥ ነው እና አዲሶቹ ትውልዶች የጋብቻ እና የቤተሰብ ህይወትን ውበት፣ ዋጋ እና አስፈላጊ ጠቀሜታ እና የሰውን ህይወት ማፍራት እና መንከባከብ የበለጠ ማድነቅ ይችላሉ ስሉ ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አስፍረዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ “አሞሪስ ላይቲስያ” (ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ) የተሰኘውን ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ በመጥቀስ ግቡን አጠቃለዋል፡- “ይበልጥ ኃላፊነት የተሞላበት እና ለጋስ ጥረት ለማድረግ… ትዳርን እና ቤተሰብን ለመምረጥ እና በዚህ መንገድ ወንዶች እና ሴቶች ለተሰጠው ጸጋ የተሻለ ምላሽ እንዲሰጡ ለመርዳት እግዚአብሔር ያቀርባቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

በችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች

ዛሬ በብዙ እና አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቁ ፈተናዎች እንዲሁም በህብረተሰብ እና በፖሊሲ ደረጃ በቤተሰብ ሕይወት ላይ ጫና የሚፈጥር "በቤተሰብ ግንኙነት ላይ የሚፈጠር ቀውስ" ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመለከትን ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰዋል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት "ቤተሰብ የማህበራዊ ህይወት ዋነኛ ምንጭ ሆኖ ይቀጥላል፣ እናም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊካፈሉ እና ሊተዋወቁ የሚገባቸው መልካም ልምዶች መኖራቸውን ይጠቁማሉ። በእነዚህ ጥረቶች ላይ ቤተሰቦች እራሳቸው ምስክር እና መሪ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

አራት ግቦች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክት የረዥም ጊዜ ሂደት አካል የሆኑትን አራት ግቦችን ዘርዝረዋል። የመጀመሪያው የቤተሰብ ጉዳዮችን በሚመለከቱ የዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከላት መካከል ውይይት እና የበለጠ ትብብር መፍጠርን ይመለከታል ፣ በመካከላቸውም የበለጠ ትስስር ለመፍጠር ማለት ነው። ሁለተኛው ግብ በክርስቲያን ማህበረሰቦች እና በካቶሊክ ዩኒቨርስቲዎች መካከል በይዘት እና ግቦች ላይ የላቀ ቅንጅትን መፍጠርን ይመለከታል። ሦስተኛ በኅብረተሰቡ ውስጥ የቤተሰብን እና የሕይወትን ባህል ማሳደግ፣ እንዲሁም አጋዥ የሕዝብ ፖሊሲ እንዲወጣ ማድረግ ነው። በአራተኛ ደረጃ ደግሞ ግቡ ቤተሰቡ በመንፈሳዊ፣ በሐዋርያዊ፣ በባህላዊ፣ በሕጋዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች በተሻለ ሁኔታ እንዲገለገልበት የሚያስችል ሐሳብ  በጋራ ማራመድ ነው።

"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለው ብዙዎች ሕልሞች የሚፈጸሙት በቤተሰብ ውስጥ ነው።"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመልእክታቸው ሁሉም ሰው ቤተሰቡን እንዲረዳ እና እርግጠኛ ባልሆነ ሁኔታ ፣ በግለሰባዊነት እና በፍጆታ ወይም ወደፊት ግለሰቦች ለራሳቸው ብቻ በሚቆሙበት ምክንያት የሚመጣው ውድቀት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል ።

"እንደ የህይወት እና የፍቅር ማህበረሰብ፣ ልዩ እና የማይፈታ ቃል ኪዳን በወንድ እና በሴት መካከል፣ ትውልዶች የሚገናኙበት ቦታ፣ ለህብረተሰቡ የተስፋ ምንጭ በመሆን ለቤተሰብ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ደንታ ቢስ መሆን አንችልም" ሲሉ ተናግሯል።

በማጠቃለያው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቤተሰብ ግሎባል ኮምፓክትን የተቀላቀሉትን ሁሉ አመስግነው ፈጣሪያቸውን እና በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ቤተሰቡን በሐዋርያዊ እንክብካቤ እና በማህበራዊ ቁርጠኝነታችን ውስጥ ለማድረግ ለሚረዱ ጥረቶች እንዲሰጡ ጋብዘዋል።

31 May 2023, 16:24