ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፖል ስድስተኛ እና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ III እ.አ.አ (1973-2023) ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፖል ስድስተኛ እና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ III እ.አ.አ (1973-2023)  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዋድሮስ ዳግማዊ የካቶሊክ-ኮፕቲክስ ውይይትን አወድሰዋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ታዋድሮስ ዳግማዊ በካቶሊክ እና በኮፕቲክ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ የቀጠለውን ታሪካዊውን “የጋራ ስነ-ክርስቶሳዊ ድንጋጌ” 50ኛ ዓመት በዓልን አክብረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የካቶሊክ እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመሪዎቻቸው መካከል የተደረገው የመጀመሪያው ዘመናዊው ስብሰባ ሃምሳ ዓመታትን ባከበረበት ወቅት፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ዳግማዊ ለአዲሱ መጽሃፍ የጋራ መግቢያ የሚሆን መቅድም ፅፈዋል።

ረቡዕ ግንቦት 02/2015 በመጻሕፍት መደርደሪያን ላይ ይገኛል ተብሎ ታስቦ የተዘጋጀው መጽሐፉ “የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ዐብይ ርእስ ሥር ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፖል ስድስተኛ እና በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ III እ.አ.አ (1973-2023) መካከል የተደረገው ስብሰባ 50ኛ ዓመት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

ማክሰኞ ግንቦት 01/2015 ዓ.ም የተለቀቀው መቅድም ለዚያ ታሪካዊ ግኑኝነት ያበቃውን የውይይት መንገድ እና ባለፈው ግማሽ ምዕተ-አመት ያስገኘውን ፍሬ ይዳስሳል።

ወደ ሙሉ ኅብረት ቀጣይ ጉዞ

ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት መቅድሙን መጻፍ የጀመሩት ቤተክርስቲያኖቻቸውን “ወደ ሙሉ ኅብረት ለመጓዝ” ያላቸውን ፍላጎት በመግለጽ እስካሁን የተደረገውን እድገት በማስታወስ ነው።

“በተጨማሪም እኛ ከምናስበው በላይ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ቀደም ሲል የተወሰዱ እርምጃዎችን እና የተጓዝንበትን ርቀት በማስታወስ እግዚአብሔርን ማመስገን አለብን” ሲሉ ጽፈዋል፣ ይህ የታሪክ ትውስታ የመጽሐፉን ዓላማ እንደሚወክልም ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ እ.አ.አ ከግንቦት 9-13/1973 በቫቲካን ውስጥ ከጳጳስ ሺኖዳ ሳልሳዊ ጋር ተገናኝተው ነበር፤ ይህ ስብሰባ ከ1,000 ለሚበልጡ ዓመታት ውስጥ “የሮም ጳጳስ እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት” መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ስብሰባ ሲሆን በዚህ ጊዜም የጋራ በሥነ-ክርስቶስ ላይ የጋራ ድንጋጌ ስምምነትን ፈርመዋል።

መግለጫው ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ተከትሎ በካቶሊክ እና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለዓመታት የዘለቀው ኢኩሜኒካዊ እና ሥነ-መለኮታዊ ውይይት አክሊል ተድርጎ በወቅቱ ተወስዶ ነበር። በ451 የኬልቄዶን ጉባኤን ተከትሎ የተነሳውን የሥነ-ክርስቶስ ባሕሪይ ውዝግብ ማብቃቱንም አመልክቷል።

የጋራ መግባባት እያደገ ይሄዳል

በጳውሎስ ስድስተኛ እና በሺኖዳ ሳልሳዊ መካከል የተደረገው ስብሰባ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መካከል የጋራ አለም አቀፍ ኮሚሽን መፈጠሩን ጨምሮ በኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች ፍሬ ማፍራቱን ቀጥሏል።

የኮሚሽኑ ሥራ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዋድሮስ ዳግማዊ፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል የሚደረገውን አንድነት ለመምራት የሚረዱ መርሆችን እ.አ.አ በ1979 በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሼኑዳ ሳልሳዊ እና በዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መካከል እንዲፈረሙ አድርጓል።

"ይህ ተልእኮ እ.አ.አ በ2003 በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና በመላው የምስራቃውያን ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቤተሰብ መካከል ለሚደረገው ሥነ-መለኮታዊ ውይይት መሠረት መንገድ ጠርጓል፤ ይህ ውይይት በአብያተ ክርስቲያናችን መካከል እያደገ መምጣቱን የሚያሳዩ ጠቃሚ ሰነዶችን አዘጋጅቷል" በማለት የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ተናግረዋል።

በወንድማማችነት ፍቅር እና ጓደኝነት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዋድሮስ ዳግማዊ እ.አ.አ በግንቦት 10/2013 በሮም የተካሄደውን የመጀመሪያ ስብሰባቸውን አስታውሰዋል። ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት የክርስቶስን ጸሎት "ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ" ነው ለተሰኘው ጸሎት ምላሽ በመስጠት በሁለቱ ቤተክርስቲያኖቻቸው መካከል ያለው መንፈሳዊ ጉዞ ፍሬ እንዲያፈራ ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ የመቅድመ ጹሑፎቻቸውን ያጠቃልላሉ።

"ዓለም ያምን ዘንድ" በአንድ መሠዊያ ላይ አብረን የምናከብርበት እና ከአንድ ጽዋ የምንቀበልበት ቀን እስኪደርስ ድረስ ቤተክርስቲያናችንን የሚያስተሳስር ወንድማዊ ፍቅር እና ወዳጅነት እስከ ተባረከ እና የምንናፍቀው ቀን ድረስ እያደገ ይቀጥል!"

 

10 May 2023, 13:27