ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን የንጉሣዊው የሃይማኖቶች ጥናት ተቋም አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን የንጉሣዊው የሃይማኖቶች ጥናት ተቋም አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ክርስትና እና እስልምና ለመልካም ሕይወት የጋራ ቁርጠኝነትን ይጋራሉ አሉ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በክርስትና እና በእስልምና መካከል ስላለው የመፍጠር የጋራ ጉዳዮች በማንፀባረቅ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ያደረጉ ሲሆን በስብሰባው ላይ የተገኙትን ሁሉ የሕይወት ዓላማ አንድ እንደሆነ እና ለእግዚአብሔር ክብር እንደሚሰጥ አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሃይማኖቶች መካከል ውይይት እና በንጉሣዊው የእምነት ጥናት ተቋም መካከል በተካሄደው ስድስተኛው የሊህቃን ኮንፈረንስ ወይም ሴሚናር ላይ ለተሳተፉት ተሳታፊዎች ንግግር ሲያደረጉ ይህ ስድስተኛ ስብሰባ በመሆኑ ፅናታቸው ግልፅ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሃይማኖቶች መካከል ያሉ የሚዛመዱ ነገሮች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በክርስትና እና በእስልምና እምነት መካከል ያሉ የፈጠራ የጋራ ጉዳዮች” በሚል መሪ ቃል “እያንዳንዳችን በረዥም ሰንሰለት ውስጥ ያለን ትስስር እንዴት እንደምንሆን ያንፀባርቃል። ብዙ ሰዎች በሚያምር እና ፈታኝ በሆነው የግንኙነት እና የወዳጅነት ጎዳና ላይ ቀድመውናል። በህዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት መሰረት የሆነውን የወንድማማችነት ስሜት በማረጋገጥ ተስፋ እንደምናደርግ እና ስንጸልይ ሌሎች ይከተሉናል” ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል የዮርዳኖስ ንጉሥ አብዱላህ ዳግማዊ ለገዛ አገራቸው ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙት የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ትኩረት ስላሳዩ አድናቆታቸውንና ምስጋናቸውን አቅርበዋል፣ “በተለይ በግጭትና በዓመፅ በታወኩ ጊዜያት” ውስጥ ለሚገኙት ክርስቲያኖች የሚያደርጉትን ጥበቃ አድንቀዋል።

የቅርስ ጥበቃ

የንጉሣዊው የሃይማኖቶች ጥናት ተቋም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "ከዋና ዓላማዎቹ መካከል የአረብ ክርስቲያናዊ ቅርሶችን መጠበቅ እና ማጎልበት" ነው ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በዚህ ረገድ “የበለጠ ምስጋና ማቅረብ የምችለው፣ ይህ ለትናንት እና ለዛሬው ክርስቲያን ዜጎች የሚጠቅም ብቻ ሳይሆን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ቅርሶችን በመጠበቅና በማጠናከር በጎሣ፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ በቋንቋ የበለጸገ በመሆኑ ይህን ቅርስ በመጠበቅና በማጠናከር ነው ወጎች እና ባህሎች ለሌሎች ለመጭው ትውልድ ሊተላለፍ የሚችለው" ሲሉ ተናግሯል።

ጥሩ ህይወት ለመኖር የሚደረግ ቁርጠኝነት

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ባጠቃለሉበት ወቅት እንደተናገሩት የተለማመደው እና የሚያራምደው ውይይት ፍሬያማ እንዲሆን ከተፈለገ ቅንነትን እና መከባበርን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው "የሁለቱንም ግጥጥሞሽ እና ልዩነቶች ግንዛቤ" እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ለሁሉም ሰው ርኅራኄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ቅዱስነታቸው "እኛ ደግሞ ሁሉም ነገር በሞት የሚያልቅ እንዳልሆነ፣ ነገር ግን ሌላ የዘላለም ሕይወት እንዳለ እናምናለን፣ ይህም ለድርጊታችን ለእግዚአብሔር መልስ የምንሰጥበት እና ሽልማት ወይም ቅጣት የምንቀበልበት ነው" ብሏል።

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የእኛ የጋራ ቁርጠኝነት ለመልካም ሕይወት ጠቃሚ ነው" እናም ይህም "ለእግዚአብሔርን ክብር እና በምድራዊ ጉዞ ላይ ለምናገኛቸው ሁሉ ደስታን ይሰጣል" በማለት ከተናገሩ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን ደምድመዋል።

 

04 May 2023, 13:16