ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት   (REMO CASILLI)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ኮሪያዊ ቅዱስ አንድሪያ ሐዋርያዊ ቅንዓት ነበረው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ በቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በግንቦት 16/2015 ዓ.ም ያደረጉት አስተምህሮ ከእዚህ ቀድመ “ለስብከተ ወንጌል ያለው ፍቅር፡-የምእመናን ሐዋርያዊ ቅንዓት” በሚል ዐብይ እርዕስት ጀምረውት ከነበረው አተምሮ ቀጣይ እና ክፍል 14 አተምሮ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ መስረት በእለቱ “የቅዱስ አንድሬያ ኪም ታጎን” ምስክርነት በሚል ንዑስ አርእስት ባደረጉት የተቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ኮሪያዊ ቅዱስ አንድሪያ ሐዋርያዊ ቅንዓት ነበረው ማለታቸው ተገልጿል።

ቅዱስ አንድሪያ ኪም ታጎን በደቡብ ኮሪያ የኖር የነበረ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህን ነበር። እ.ኤ.አ. በ1984 በሴኡል ካቴድራል አስክሬኑ ባረፈበት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ስምተ ቅድስናው ታውጆ ነበር። በወቅቱ በደቡብ ኮሪያ በክርስትያኖች ላይ በተነሳ ስደት የተነሳ 103ቱ የኮሪያ ሰማዕታት መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ቅዱስ አንድርሪያ ከእነዚህ መካከል አንዱ ነበር።

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚከተለው ነበር

“ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፣ ሎሌም ከጌታው አይበልጥም፤ ደቀ መዝሙር መምህሩን፣ ሎሌም ጌታውን ከመሰለ ይበቃዋል። ባለቤቱን ‘ብዔልዜቡል’ ካሉት፣ ቤተ ሰዎቹንማ እንዴት አብልጠው አይሏቸውም! በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን አውሩት፤ በጆሯችሁ የሰማችሁትን በአደባባይ ዐውጁት (ማቴ 10፡24-25፣27)።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡርና እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አስተናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዚህ ተከታታይ ትምህርት ውስጥ ራሳችንን በአንዳንድ ቅዱሳን ትምህርት ቤት ውስጥ እናስቀምጣለን እንደ አርአያ ምስክሮች፣ ሐዋርያዊ ቅንዓትን ያስተምሩናል።

ዛሬ እዚህ ራቅ ባለ ሀገር ማለትም የኮሪያ ቤተክርስቲያን ያለውን የስብከተ ወንጌል ስሜት ታላቅ ምሳሌ እናገኛለን። ኮሪያዊው ሰማዕትና ቀዳማዊ ካህን ቅዱስ እንድርያስ ኪም ታጎን ዛሬ እንመለከታለን። ህይወቱ ለወንጌል መስበክ ታላቅ ቅንዓት ምስክር ሆኖ ቆይቷል።

የዛሬ 200 ዓመት ገደማ የኮሪያ ምድር በክርስትና እምነት ላይ ከባድ ስደት ደርሶበት ነበር። በዚያን ጊዜ በኮሪያ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት እስከ ሞት ድረስ ለመመሥከር ዝግጁ መሆን ማለት ነበር። በተለይም ከቅዱስ አንድሪያ ኪም ምሳሌ የህይወቱን ሁለት ተጨባጭ ገፅታዎች ማውጣት እንችላለን።

የመጀመሪያው ከምእመናን ጋር የሚገናኝበት መንገድ ነው። በጣም የሚያስፈራውን አውድ ስንመለከት፣ ቅዱሱ ክርስቲያኖችን እና በሌሎች ሰዎች ፊት ሁልጊዜ በጥበብ ለመቅረብ ተገዷል። ከዚያም የእርሱ ከእነርሱ ጋር በውይይቱ አብሮ መካፈሉ ያለውን ክርስቲያናዊ ማንነት ለማረጋገጥ ቅዱስ እንድርያ እነዚህን መሣሪያዎች ተግባራዊ አድርጎ ነበር፣ በመጀመሪያ እውቅና ምልክት ላይ ቀደመ ስምምነት ነበር፣ ከዚያ በኋላ “የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነህን?” የሚለውን ጥያቄ በድብቅ ይጠይቅ ነበር። ሌሎች ሰዎች ውይይቱን እየተመለከቱ ስለነበር ቅዱሱ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ጥቂት ቃላት ብቻ በመናገር ዝግ ባለ ድምፅ መናገር ነበረበት። እንግዲያውስ ቅዱስ አንድሪያ ኪም የክርስቲያኑን አጠቃላይ ማንነት የሚያጠቃልለው አገላለጽ “የኢየሱስ ደቀ መዝሙር” ነው።

በእርግጥ የጌታ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት እሱን መከተል፣መንገዱን መከተል ማለት ነው፣ ይህም ለወንጌል ህይወቱን መስጠትን ይጨምራል። ስለዚህ ክርስትያን በተፈጥሮው ሚስዮናዊ እና ምስክር ነው፣ ኢየሱስም የአብ ወንጌላዊ እና ምስክር እንደሆነ ሁሉ። እያንዳንዱ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ይህን ማንነት ከመንፈስ ቅዱስ ይቀበላል፣ እና መላው ቤተ ክርስቲያን፣ ከጰንጠቆስጤ ቀን ጀምሮ ይህንን ኃላፊነት ይቀበላል። ወንጌሉ በሙላት ሲኖር ሰውየው ለራሱ አይሰጥም፣ ነገር ግን ስለ እምነትን ይመሰክራል፣ ስለዚህም ተላላፊ እምነት ያደርገዋል። የወንጌል አገልግሎት ፍቅር የተወለደበት ቦታ በትክክል ነው። እናም በዙሪያው ያለው አውድ ተስማሚ ባይሆንም እንኳ አይለወጥም፣ በተቃራኒው የበለጠ ዋጋ ያለው ይሆናል። በስደት ጊዜ ለወንጌል መመስከር ለእምነት ብዙ ፍሬ እንደሚያፈራ ቅዱስ አንድሪያ ኪም እና ሌሎች ኮሪያውያን አማኞች አሳይተዋል።

አሁን ሁለተኛውን ተጨባጭ ምሳሌ እንመልከት። ገና የዘረዓ ክህነት ተማሪ በነበረበት ጊዜ፣ ቅዱስ እንድርያ ከውጭ የሚመጡ የሚሲዮናውያን ካህናትን በድብቅ የሚቀበልበትን መንገድ መፈለግ ነበረበት። የወቅቱ አገዛዝ ሁሉም የውጭ ዜጎች ወደ ግዛቱ እንዳይገቡ አጥብቆ ስለሚከለክል ይህ ቀላል ስራ አልነበረም። አንድ ጊዜ በረዶው እየወረደ እያለ ምግብ ሳይበላ፣ ለረጅም ጊዜ ሲራመድ፣ ደክሞ መሬት ላይ ወድቆ፣ ራሱን ስቶ በወደቀበት ሥፍራ በረዶ ሆኖ ቀረ። በዛን ጊዜ በድንገት "ተነስ ሂድ!" የሚል ድምጽ ሰማ። ያንን ድምፅ የሰማ አንድሪያ ወደ ልቦናው መጣ፣ አንድ ሰው እየመራው እንዳለ ጥላ የመሰለ ነገር በጨረፍታ እያየ።

ይህ የታላቁ ኮሪያዊ ምስክር ተሞክሮ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ሐዋርያዊ ቅንዓት እንድንረዳ ያደርገናል፥ ማለትም አንድ ሰው ሲወድቅ ለመመለስ ድፍረትን እንዲያገኝ የሚረዳው ኃይል እንዳለ ያሳያል። ሁኔታው ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ለወንጌል መልእክት ምንም ቦታ የማይሰጥ ሊመስል ይችላል— ተስፋ ልንቆርጥ እና በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆነውን ማለትም የወንጌል አገልግሎትን ከማሳደድ መራቅ የለብንም። ምናልባት አንዳንድ ጊዜ በውጫዊ መሰናክሎች ምክንያት ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን፣ እናም ለወንጌል መመስከር አለመግባባትን እና ንቀትን ሊያመጣ ይችላል። ሆኖም በተመሳሳይ ጊዜ፣ ሁልጊዜም ወደ ኋላ ልንነሳ እንችላለን፣ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስ ፈጽሞ አይተወንም፡ ሁል ጊዜ ቅርብ ነው፣ ያበረታናል፣ እናም እጃችንን ይዞ ያነሳናል።  እናም ሁሌም ይህንን ቃል ይደግምልናል "ተነስ ሂድ!" ከሙታን የተነሣው እርሱ ራሱ ነው። የእርሱ ትንሳኤ ከውድቀት ሁሉ የምንነሳበት ሁኔታ ስር የሰደዱበት ምስጢር ነው። ወደፊት እንድንሄድ የሚያስችለን የጥንካሬ ምንጭ ነው።

ወንድሞች እና እህቶች ተስፋ አንቁረጥ፥ ጣፋጭ የሆነውን የወንጌል ደስታ እንዳንነጠቅ (ጳውሎስ 6ኛ)፡ እና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰጠን ብርታት ወደ ፊት እንሂድ።

24 May 2023, 10:36