ፈልግ

በማያንማር በርማ የተከሰተው ሞካ የሚል መጠሪያ የተሰተው አውሎንፋስ ያስከተለው ጉዳት በማያንማር በርማ የተከሰተው ሞካ የሚል መጠሪያ የተሰተው አውሎንፋስ ያስከተለው ጉዳት   (Copyright © Partners Relief & Development)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሞካ በተሰኘው አውሎንፋስ የተጎዱ ማህበረሰቦች ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ ግንቦት 20/2015 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደበባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት እንደ ገለጹት ሞካ የሚል ስያሜ በተሰጠው አውሎንፋስ ለተጠቁ ሰዎች በሙሉ ጸሎት እንዲደረግ የተማጸኑ ሲሆን ሁሉም ክርስቲያኖች በእዚህ የተፈጥሮ አደጋ ለተጠቁ ሰዎች የታቻላቸውን ርዳታ እና ጸሎት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.አ.አ ባለፈው ግንቦት 22/2023 ዓ.ም 150ኛው የሙት አመት የተዘከረለት ከታዋቂዎቹ የስነ-ጽሁፍ ባለሞያዎች መካከል አንዱ የነበረው አሌሳንድሮ ማንዞኒ የሞተበት መታሰቢያ መዘከሩን ቅዱስነታቸው ያስታወሱ ሲሆን በስራዎቹ አማካኝነት ለተጠቂዎች እና ለአቅመ ደካሞች የሚሆን መልእክት በማስተላለፍ የበኩሉን አስተዋጾ ማደረጉን ገልጸው "የሚፈጥር እና የሚገድል፣ የሚቀጣው ከዚያም በፍቅር ይፈውሳል" በሚለው መለኮታዊ ጥበቃ በሚመለከት ድንቅ የሆነ ሥራ ሠርቶ እንደ ነበረ ጠቁመዋል።

በማይናማር እና በባንግላዲሽ አዋሳኝ ድንበር ላይ ለሚኖሩ፣ በከባድ አውሎ ንፋስ ለተመታ ህዝብ እንድንጸልይ ለሁላችሁ ጥሪ አቀርባለሁ በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከእነዚህ ህዝቦች ጋር ያለኝን ቅርበት በደግሜ ስገልጽ፣ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና የሀገሪቷ መሪዎች ሰብአዊ ርዳታ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ፣ እናም የሰብአዊ እና የቤተክርስቲያን አጋርነት ስሜት ለእነዚህ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንዲደረግላቸው በትህትና እጠይቃለሁ ብሏል።

እ.አ.አ በመጭው ረቡዕ፣ በግንቦት ወር መጨረሻ፣ በመላው ዓለም በማሪያም ስም በተሰየሙት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ቀጣዩን የጳጳሳት ሲኖዶስ መደበኛ ጉባኤ ዝግጅት ለመደገፍ በመላው ዓለም በሚገኙ የማርያም ቤተ መቅደሶች የጸሎት ጊዜያት ታቅደዋል ያሉት ቅዱስነታቸው ድንግል ማርያም ይህንን ጠቃሚ የሲኖዶስ መድረክ በእናቶች ጥበቃ እንድትሸኘው እንጠይቃለን። እናም ለእሷ እንዲሁም በአለም ዙሪያ ያሉ የብዙ ህዝቦች በተለይም ዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን አደራ እንሰጣለን ሲሉ ተናግሯል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም መልካም እሁድ ለሁላችሁም ይሆን ዘንድ እመኛለሁ ካሉ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው እና ቅዱስነታቸው ዘወትር እንደሚሉት “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ አትዘንጉ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቋል።

28 May 2023, 10:33