ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን እና የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ታዋድሮስ በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን እና የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ታዋድሮስ በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና የእሳቸው ታዋድሮስ እቅፍ፡ ጉብኝታቸው በኅብረት እንድናድግ ይረዳናል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ በአንድነት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በሚያደርጉት የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ ተሳትፈው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ በ2013 እና በ1973 በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በጳውሎስ ስድስተኛ እና የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ በሺኖዳ ሳልሳዊ መካከል ከተደረገው ስብሰባ ከ10 ዓመታት በኋላ የተደረገ ግንኙነት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን “ይህ ጉብኝት ሕብረት የምንፈጥርበት እና አንድ የምንሆንበት ቀን ቅርብ እንዲሆን ያደርጋል” በማለት የተናገሩ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2015 በሊቢያ ለተገደሉት 21 የኮፕት ክርስቲያኖች ሀሳብ፡ "የኮፕቲክ ሰማዕታት የእኛም ሰማዕታት ናቸው" ሲሉ ቅዱስነታቸው በወቅቱ መናገራቸው ይታወሳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ይህ ጉብኝት በክርስቶስ አንድ የምንሆንበት ለተባረከ ቀን ፈጥኖ እንዲደርስ ያድርገን!"

በመጀመሪያ መተቃቀፉ፣ ከዚያም የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ የሆኑት ታዋድሮስ ዳግማዊ በአንገታቸው ላይ ያጠለቁትን ሜዳሊያ ቅዱስነታቸው መሳማቸው የተገለጸ ሲሆን (ይህ መዳሊያ ፔክቶሪያል መስቀል በመባል ይታወቃል፥ በሰንሰለት የተሠራ ትንሽ መስቀል፣ አብዛኛውን ጊዜ ከቆዳ፣ ከብር ወይም ከወርቅ የተሰራ ሲሆን ቀሳውስቱ በሚለብሱት ልብሰ ተክህኖ ምልክት እና መለያ ምልክት ሆኖ ለካህናቱ መንፈሳዊ ኃይል እና ጥበቃ ይሰጣል ተብሎ ይታመናል”፣ ጥቂት የቃላት ልውውጦች በአስተርጓሚ ታግዘው ካድረጉ በኋላ በመጨረሻም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወደሚገኘው መድረክ ጎን ለጎን እየተራመዱ ሕዝቦን ለመባረክ ወደ እዚያው ማቅናታቸው ተገልጿል።

ልክ ከአስር አመታት በኋላ - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ ጥቂት ወራት ካለፈ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ ጋር በድጋሚ ተገናኙ። በሮም ኤጲስ ቆጶስ እና በአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ መካከል የመጀመሪያው ሰላምታ ከቀረበ አሥር ዓመታት በኋላ ከሃምሳ አመት በፊት በአባቶቻቸው ጳውሎስ 6ኛ እና ፓትሪያርክ ሺኖዳ ሣልሳዊ (እ.አ.አ 1973) መካከል ከተካሄደው ታሪካዊ ስብሰባ በኋላ “የማይረሳ የጋራ ሥነ-ክርስቶሳዊ ድንጋጌ መግለጫ ለመፈረም ያበቃው በትክክል እ.አ.አ ግንቦት 10 ቀን” ነው። ድርብ የምስረታ በዓል በፓትርያርኩ የሮም ጉብኝት እስከ እሁድ ድረስ በሮም በሚያደርጉት ቆይታ እየተከበረ ይገኛል።

የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ
የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ

"ውድ ጓደኛዬ እና ወንድሜ" በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ መቀበላቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት  በአረብኛ ቋንቋ ፓትርያርክ ተዋድሮስ የቀረበውን ሰላምታ ተከትሎ ነበር። "በዚህ ድርብ የምስረታ በዓል ላይ ግብዣዬን ስለተቀበሉኝ አመሰግንሃለሁ፣ እናም የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን የሮምን ጉብኝቶን፣ እዚህ የምያደርጓቸውን ጠቃሚ ስብሰባዎች እና በተለይም የግል ውይይቶቻችንን እንዲያበራሎት እጸልያለሁ" ሲሉ ቅዱስነታቸው መናገራቸው ተገልጿል።

ለወዳጅነት ያለው ቁርጠኝነት

የኦርቶዶክስ ካቶሊኮች እና ኮፕቲኮች ፣ በወዳጅነት እና በሰማዕታት ምልክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ፓትርያርኩን “በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መካከል እያደገ ላለው ወዳጅነት” ላሳዩት ቁርጠኝነት ሞቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ከዚያም እ.ኤ.አ. በ 2013 ወደ መጀመሪያው ስብሰባቸው በመመለስ እርሳቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ከፓትሪያርኩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ በወቅቱ ፓትርያርክ ታዋድሮስ በእየ አመቱ እ.አ.አ በየግንቦት 10 "የኮፕቲክ-ካቶሊክ ወዳጅነት ቀን" ለማክበር ሀሳብ ማቅረባቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።  "ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እያከበርነው እንገኛለን፥ በየዓመቱ በስልክ እንገናኛለን፣ ሰላምታ እንላላካለን፣ ጥሩ ወንድሞች እንሆናለን፣ አልተጣላንም” ሲል ተናግረዋል።

አንድ ቅዱስ ማሰሪያ

በመቀጠልም ለኤጲስቆጶሳት፣ ለምእመናን፣ ለኮፕቲክ-ኦርቶዶክስ ልዑካን ቀርቦ ሁሉም ሰው ሁሉን የሚችለውን አምላክ እንዲለምን ይጠይቃል፣ “በኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን እና ሰማዕታት ምልጃ፣ በአንድ እና በቅዱስ ማሰሪያ በኅብረት እንድናድግ ይረዳናል። የእምነት፣ የተስፋ እና የክርስቲያን ፍቅር" ሥር መሰረቶቻችን ናቸው ሲሉ ተናግሯል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ታዋድሮስ የሮም ጉብኝት እንዲባርክ እና መላውን የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንዲጠብቅ በቦታው የተገኙ ሁሉ እንዲጸልዩ እጠይቃለሁ ሲሉ ቅዱስነታቸው የተናገሩ ሲሆን በመጨረሻም፣ “ከጥቂት ዓመታት በፊት ሰማዕታት ለሆኑት በሊቢያ ባህር ዳርቻ ላይ መስዋዕት ለሆኑት ሰማዕታት” ያላቸውን ሐሳብ አቅርበዋል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ራሳቸው በሌሎች አጋጣሚዎች እንዳስታውሱት የክርስቶስን ስም እያንሾካሾኩ የሞቱት በሊቢያ የባህር ዳርቻ ስለሞቱት ሰማዕታት ተናግሯል።

የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ በበኩላቸው  የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና የመላው ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አካላት ሰላምታ ለሊቀ ጳጳሱ በማቅረቡ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያላቸውን አድናቆቱን ገልጿል “በዚህ የአገልግሎት ዘመን በሁሉም መስክ ለአለም ላደረጋችሁት ሁሉ፣ እና ክርስቶስ በመልካም ጤንነት እንዲጠብቆ  እና ረጅም እድሜ እንዲሰጦት እጸልያለሁ” ሲሉ ተናግሯል።

የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ አክለው ሲናገሩ ከአሥር ዓመታት በፊት ለተደረጋላቸው ምቅ ያለ አቀባበል፣ የእቅፍ መታሰቢያ እና በጳጳስ የተደረገ "ፍቅር" አቀባበል እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት "በወንድማማችነት ፍቅር የተሞላ ቅዱስ ጊዜ ከእናንተ ጋር አሳልፈናል" ሲሉ አስታውሰዋል።  ይህ ፍቅር በየአመቱ "የወንድማማች ፍቅር ቀን" ተብሎ የሚከበረው "ምልክት እና መፈክር" ሆኗል፡ "እርስ በርሳችን እንነጋገራለን እና እንጽፋለን በየዓመቱ ለማደስ እና የክርስቲያን መንፈስ እና የክርስትና መንፈስን ያካተተ ቀን ነው እንዲሆን ጠንክረን እንሠራለን” ሲሉ እግዚአብሔርን በማገልገል እና ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በሰው ልጆች በማገልገል አንድ የሚያደርገን ፍቅር” ልንገልጽ ይገባል ሲሉ የአሌሳንድሪያው ጳጳስ እና የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ታዋድሮስ ዳግማዊ ተንግሯል። “ፍቅርን መርጠናል፣ ከስግብግብነትና ከራስ ወዳድነት ዓለም ማዕበል ጋር ብንቃወምም፣ ክርስቶስ የሚጠይቀንን የፍቅር ተግዳሮት ተቀብለናል፣ እናም እኛ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንሆናለን እና ዓለምም የበለጠ ሰብዓዊ ትሆናለች ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ እና ስሙም ከፍ ያለ ስሙ እንደ ሆነ ዓለም ሁሉ ያውቃል” ሲሉ ተናግሯል።

10 May 2023, 13:17