“ከአፍሪካ ላይ እጃችሁን አንሱ!” የሚለው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አዲስ መጽሐፍ በየመደብሮቹ ተሰራጭቷል
አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
“እጃችሁን ከአፍሪካ ላይ አንሱ!” ‘አፍሪካን አንቆ መያዝ ይቁም’ ለመበዝበዝ የተዘጋጀች የማዕድን ቦታ አይደለችም ወይም ለመቀማት እና ለመዘረፍ የተዘጋጀች ምድር አይደለችም። አፍሪካ የራሷ እጣ ፈንታ ዋና ተዋናይ ትሁን!”
እነዚህ ቃላቶች ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በዚህ ዓመት መጀመሪያ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባደረጉት ጉብኝት የመጀመሪያ ቀን ላይ የተናገሩት ቃላት ናቸው።
የቫቲካን አሳታሚ ድርጅት አዲስ መጽሃፍ መለቀቁን ያሳወቀ ሲሆን ፥ ይህ በጣሊያንኛ የተፃፈ እና ‘እጆቻችሁን ከአፍሪካ ላይ አንሱ’ የሚል አርዕስት የተሰጠው መጽሃፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ከዚያም በደቡብ ሱዳን ባደረጉት ሃዋሪያዊ ጉዞ ወቅት ያደረጓችውን ንግግሮች ያካተተ እንደሆነም ተነግሯል።
ዋናው ነገር ግን መጽሐፉ የጳጳሱን ድምጽ ብቻ ሳይሆን ያካተተው ፥ በጉዞው ወቅት ያገኟቸውን እና ያናገሯቸውንም ሰዎች ሃሳቦች ጭምር ይዟል። በአሰቃቂ ግጭት ምስቅልቅላቸው የወጣው እነዚህ ሁለቱ ሃገራት ማለትም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የጦርነት ሰለባዎችን ምስክርነት እና ታሪኮቻቸውን በዚያን ወቅት አድምጠው የነበረ ሲሆን ፥ ይህም በመጽሃፋቸው ውስጥ ተካተዋል።
የመፅሃፉ መቅድም የተጻፈው በናይጄሪያዊቷ የሴቶች መብት ተከራካሪዋ እና ደራሲ ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቺ ሲሆን ፥ ስለ መጽሐፉም ስትናገር “ለኮንጎ ህዝብ እና እኔ ቤቴ ብዬ የምጠራት የአፍሪካ አህጉር ውስጥ ለሚኖሩ ተወዳጆች እና ልባቸው ለተሰበረባቸው ህዝቦች ትንሽ ተስፋ ሰጥቶኛል” ብላለች።
ሃዋሪያዊ የሠላም ጉዞ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን በዚሁ ዓመት ከጥር 31 እስከ የካቲት 5 ቀን ሃዋሪያዊ ጉዞ ማድረጋቸው ይታወቃል።
“ሃዋሪያዊ የሠላም ጉዞ” ሲሉ የገለጹት እና አንድ ሳምንት የፈጀው ይህ ጉብኝት ፥ ግጭት ባለባቸው ሀገራት ዕርቀ ሠላም እንዲሰፍን እንዲሁም ከውጭ ጣልቃ ገብነት ነፃነታቸውን እንዲያውጁ ለማበረታታት ያለመ ጉዞ ነበር።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከመንግስት ባለስልጣናት ፣ ጳጳሳት እና ወጣቶች ጋር ተገናኝተው ሲናገሩ “‘የአፍሪካ የፖለቲካ ቅኝ ግዛት’ ወደ ‘ኢኮኖሚያዊ ቅኝ ግዛት’ የተሸጋገረ ሲሆን ይህም የባርነት አገዛዝ ጋር እኩል ነው” ብለዋል ብጹእነታቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፥ ደቡብ ሱዳን ውስጥ በመጣላት ላይ ያሉ ፖለቲከኞችንም በማናገር ፥ እርስ በእርስ የሚያደርጉት ግጭት ሀገሪቷ ላይ ከባድ ውድመት እንዳደረሰ እና አሁን “ከዚህ በኋላ ይበቃል” የሚባልበት ጊዜ እንደሆነ አበክረው ተናግረዋል።
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የዓለም ዝምታ
አዲቺ በመጽሃፉ መግቢያ ጽሁፏ ላይ እንዳስቀመጠችው ፥ በተለይም የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱን ወደ ኮንጎ ባደረጉት ጉዞ ላይ ያተኮረች ሲሆን “ሀብቷ ለረጅም ጊዜ ሲበዘበዝ የኖረች ሀገር ፣ በዘረፋ እና በግጭት የተዳከመች ሀገር እንዲሁም እንደገና ለማገገም ተስፋ የምትቆርጥ ሀገር” በማለትም ገልፃለች።
“የሁኔታው ትልቁ አሳዛኝ ነገር” ትላለች አዲቺ ፥ “አፍሪካን ይበልጥ የሚጎዳው የእርስ በርስ ግጭቱ ብቻ ሳይሆን የዓለም ዝምታ እና የአፍሪካን ሀብት በስግብግብነት የሚዘርፈው ዓለም የሚያደርጉት የአፍሪካን ሰብዓዊነት የሚያዋርደው ንግግራቸው ነው” ትላለች። በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ፥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጉብኝት እና በዚያ ያስተላለፉት ‘ኃይለኛ’ መልእክቶች ለበለጸጉ አገሮች እንደ ‘አስፈላጊ ተግሣጽ’ ይነበባሉ ትላለች።
አዲቺ ንግግሯን በመቀጠል፣ “የእርሳቸው መልእክት ለኮንጎ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ አፍሪካም አስፈላጊ ነው ፥ ነገር ግን ይህ በአንድ ምክንያት ብቻ አይደለም ፥ ዓለም አቀፉ ሰሜናዊው ክፍል የተመካበት ለሃብቷ ብቻ ሳይሆን ፣ እንዲሁም አህጉሪቱንም በመፍራት አይደለም ፥ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት እንደተከሰተው ሁሉ የምዕራባውያን የውክልና ጦርነቶች ቦታ ዳግም ልትሆን ትችላለች በማለትም አይደለም ፥ ነገር ግን በቀላሉ በሰዎች ምክንያት ነው ፥ አህጉሪቷ ላይ ለሚኖሩ ለሰው ልጆች በሙሉ ሲባል ነው አፍሪካ አስፈላጊ የምትሆነው።” በማለት ሃሳቧን አጠቃልላለች።