ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጳጳሳት፡ የእርቅ እና የሰላም ነቢያት ሁኑ ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካቶሊካዊያን ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው በነበረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት እግዚአብሔር ለኮንጎ ሕዝብ ነቢይ ለመሆን በአገልግሎታቸው ቅርብ መሆኑን እንዲያስታውሱ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ኮንጎ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ በአራተኛውና በመጨረሻው ቀን በብሔራዊ ጳጳሳት ጉባኤ ዋና መሥሪያ ቤት ከአገሪቱ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው እንደ ገለጹት ከሆነ በመጀመሪያ እ.አ.አ. በነሐሴ 2022 ዓ.ም አገሪቱን ለመጎብኘት ቀጠሮ ይዘው እንደ ነበረ ያስታወሱ ሲሆን በወቅቱ ያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባለመሳካቱ እና አሁን ደግሞ ጳጳሳቱ ለጉብኝቱ ሁለት ጊዜ እንዲዘጋጁ በማድረጋቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ባለው ሰፊ ደን ውስጥ የኮንጎን ህዝብ እምነት ለመገንባት እና "የፍጥረትን ውበት" ለመጠበቅ ስላላቸው ተልእኮ አነጋግሯቸዋል።

የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንም ከህዝቦቿ ጋር በመከራ ውስጥ ትሰቃያለች እንዲሁም ደስታቸውንም ትቋደሳለች ያሉት ቅዱስነታቸው “ኢየሱስ በዚህ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ሲሰቃይ፣ ሲሰቀልና ሲጨቆን አይቻለሁ፣ ርኅራኄ በሌለው ዓመፅ የተመሰቃቀለ፣ በንጹሐን ስቃይ ተጎድቶ፣ ኅብረተሰቡን ከሚበክል የሙስና እና የፍትሕ መጓደል ጋር ለመኖር ተገደደ፣ እና በብዙዎቹ ድህነት ውስጥ ሲሰቃይ አይቻለሁ፣ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ልጆችን ጨምሮ” ሲሉ በሐዘን እና በቁጭት ተናግረዋል።

በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል “የእግዚአብሔርን ቅርብ መሆን እና እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ቅርበት ትንቢት መናገር ” አስፈላጊ መሆኑን ለጳጳሳቱ ተናግረዋል።

ሌሎች 'ወደ በጎ እረኛው እንዲቀርቡ'' ለመርዳት በእግዚአብሔር ቅርበት መጽናኛ እንዲያገኙ አሳስቧቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በኤጲስ ቆጶሳት መካከል የሚደረጉ የስልጣን ወጥመዶች እና ራስን መጎልበት አውግዘዋል፣ እንዲህ ያሉ አመለካከቶች በጸሎት ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ችላ እንዲሉ ያደርጋቸዋል፣ ስለዚህ መጠንቀቅ ይኖርብናል ብለዋል።

“ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቅርርብ ከፍ አድርገን ስንመለከት ወደ ህዝባችን እንቀርባለን እናም በአደራ ለተሰጡን ምንጊዜም እንራራለን” ብሏል።

የኤጲስ ቆጶሳት እረኝነት አገልግሎት "ቁስሎችን መንካት እና የእግዚአብሔርን ቅርበት ማሳወቅ" አለበት፣ ስለዚህም የኮንጐ ህዝብ ከ"ውርደት እና ጭቆና" እንዲላቀቅ መሥራት ይኖርባችኋል ብለዋል።

ነብያት ኢፍትሃዊነትን ከሥሩ ነቅለው ይጥላሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል ወደ ትንቢቱ ጭብጥ ዘወር አሉ፣ ጳጳሳቱም ሊቀበሉት የሚገባው ቃሉ በውስጣቸው ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር ለመምራት “አብክረው እንዲሰሩ” እና እንዲነቃነቁ ጥሪ አድርገዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“የእግዚአብሔር ቃል በውስጣችን የሚነድና እንድንወጣ የሚገፋፋን እሳት ነው! እንግዲህ እኛ እንደ ኤጲስ ቆጶሳት የሆነው ይህንን በተግባር ላይ ለማዋል ነው፤ በእግዚአብሔር ቃል የተቃጠሉ ለእግዚአብሔር ሕዝብ በሐዋርያዊ ቅንዓት የተላኩ ሰዎች ነን”።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጠማማነትና በፍትህ እጦት በተሞላ ዓለም ውስጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለመገንባት እንዲረዱ እግዚአብሔር ነቢያቱን ይጠራል ብለዋል።

የጥላቻ፣ የቂም እና የአመጽ መርዞች ከህብረተሰቡ፣ ከሙስና እና ብዝበዛ ጋር የተቆራኙ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ፖለቲካ ሳይሆን ቃሉን ማወጅ

ሆኖም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተናገሩት ጳጳሳት “ቃሉን እንዲሰብኩ፣ ኅሊናን እንዲያነቁ፣ ክፋትን እንዲያወግዙ፣ ልባቸው የተሰበረና ተስፋ የቆረጡትን እንዲያበረታቱ” ስለተደረጉ የክርስቲያኖች ትንቢት ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር መምታታት የለበትም ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

ኤጲስ ቆጶሳቱን ከካህናቶቻቸው እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከሚሰጡ ምዕመናን ጋር እንዲቀራረቡ እና የይቅርታ እና የወንጌል ቅንዓት ያላቸው ምሳሌ እንዲሆኑ ጋብዟል።

"ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን ቸል እንዳትሉ ወይም የትንቢት ነበልባል ከስልጣናችሁ ጋር ባላችሁ አሻሚ ግንኙነት ወይም ቸልተኛ እና መደበኛ ህይወት እንዳይጠፋ እለምናችኋለሁ" ብለዋል።

በዓመፅ ፊት የምሕረት ምስክሮች

በማጠቃለያም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጳጳሳት የሟቹን ሊቀ ጳጳስ ክሪስቶፍ ሙንዚሂርዋን ምሳሌ እንዲመለከቱ አሳስበዋል።

የኢየሱሳውያን ማሕበር አባል የነበሩ ሊቀ ጳጳስ “ደፋር እረኛ እና ትንቢታዊ ድምፅ” ነበሩ እናም በ1996 ዓ.ም ህዝቡ የሚደርስበትን ጥቃት በመከላከል ላይ በነበሩበት ወቅት ነበር በከተማ አደባባይ በታጣቂዎች የተገደሉት።

በሃብት ምዝበራና በጎሳና በዘር ግጭት ብቻ ሳይሆን በክፉው የእግዚአብሔር ጠላት የጨለማ ሃይል በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ የምህረት እና የእርቅ ምስክሮች ሁኑ፣ ሰብዓዊነትን መስክሩ” ሲሉ ከተናገሩ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።  

 

03 February 2023, 14:36