ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለደቡብ ሱዳናዊያን ኢየሱስ ያውቃችኋል እና ይወዳችኋል ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ኢየሱስ እያንዳንዳችንን በግል እንደሚያውቀንና እንደሚወደን በመግለጽ ለደቡብ ሱዳን ምእመናን "የምድር ጨው" እና "የዓለም ብርሃን" እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን የተናገሩት በጥር 28/2015 ዓ/ም በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ በጁባ በነበራቸው የመጨረሻ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምዕመናን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ኢየሱስ ጭንቀታችሁን እና በልባችሁ ውስጥ የምትሸከሙትን ተስፋ፣ በህይወታችሁ የምታሳዩትን ደስታዎችና ተጋድሎዎች፣ የሚያጠቃችሁን ጨለማ እና በሌሊት የምትዘምሩትን መዝሙር እና ወደ በሰማያዊው አባታችሁ ላይ ያላችሁን  እምነት ያውቃል። ኢየሱስ ያውቃችኋል ይወዳችኋል። እናንተ በእርሱ ብትኖሩ ከቶ አትፈሩም፤ ምክንያቱም ለእኛ ደግሞ መስቀል ሁሉ ትንሣኤ፣ ሐዘንም ሁሉ ወደ ተስፋ፣ ልቅሶም ሁሉ ወደ ደስታ ይለወጣል”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን አጽናኝ ቃል ለደቡብ ሱዳን ምእመናን በሀገሪቱ ዋና ከተማ ጁባ እሁድ ጠዋት ጥር 28/2015 ዓ.ም በሀገሪቱ እያደረጉ የነበሩትን የመጨረሻ ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ከማጠናቀቃቸው በፊት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት ላይ ነበር።

በ"ጆን ጋራንግ" መካነ መቃብር ስፍራ ውስጥ በጉጉት ለተሰበሰበው ታላቅ ሕዝብ ንግግር ያደረጉት የቅዱስ አባታችን በወቅቱ ባደረጉት ቃለ ምእዳን በደቡብ ሱዳን በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ እና ለአገሪቱ ምዕመናን የኢየሱስን ተስፋ እና ቅርበት ለማምጣት ያላቸውን ፍላጎት በመግለጽ ጀመሩ።

እዚህ የተገኘውት ኢየሱስን ለማወጅ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሁለተኛው ንባብ ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ማኅበረሰብ የተናገረውን የራሱን ቃል ለመናገር እንደሚፈልጉ ተናግሯል፡- “ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ያውም የተሰቀለውን፣ እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና (1ኛ ቆሮ 2፡1-2) የሚለው ጠቅሰዋል።

የቅዱስ ጳውሎስም ጉዳይ የቅዱስ ጳውሎስ ጭንቀት ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን፡- “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፍቅር አምላክ በመስቀሉ ሰላምን ባገኘ አምላክ፣ ስለ ሁላችን የተሰቀለው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ስም ከእናንተ ጋር እሰበሰባለሁ። የተሰቀለው በተሰቃዩት፤ ኢየሱስ በብዙዎቻችሁ ሕይወት፣ በዚህች አገር በብዙ ሰዎች ውስጥ የተሰቀለው፣ ኢየሱስ፣ የተነሣው ጌታ፣ በክፋትና በሞት ላይ ድል ነሺ ነው ብለዋል።

“ኢየሱስን ልሰብክና በእርሱ ላጸናችሁ ወደዚህ መጣሁ የክርስቶስ መልእክት የተስፋ መልእክት ነውና” ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ህመማቸውን እና ተስፋቸውን እንደሚያውቅ እና እያንዳንዳቸውን በግል እንደሚያውቃቸው እና እንደሚወዳቸው አስታውሷቸዋል።

ከጌታ ጋር አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ ፈጽሞ እንዳይፈሩ አሳስቧቸዋል፣ ምክንያቱም እርሱ ሁል ጊዜ ከጎናቸው ይሆናልና ያሉ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዛሬው ወንጌል በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ... እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ያለውን የጌታን ቃል በማሰላሰል የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆነው እነዚህ ምስሎች ለእነርሱ ምን ዓይነት አድምታ እንደ ሚሰጡ ለምዕመኑ ጥያቄ አቅርበዋል።

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ

“የምድር ጨው” መሆናችንን ቅዱስ አባታችን እንደተናገሩት ጨው ለምግብ ጣዕም እንደሚሰጥ እና “ለሁሉም ነገር ጣዕም ሲሰጥ የማይታይ እና የሚሟሟ ንጥረ ነገር ነው” እናም ያለዚያ ሁሉም ነገር ደካማ እና ጣዕም የሌለው ይሆናል ያሉ ሲሆን ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በተራራ ላይ ስብከት ላይ ስለብፅዕና ካስተማረ በኋላ ወዲያውኑ የጨው አምሳያ እንደተጠቀመ በማስታወስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ ብፅዕና የክርስትና ሕይወት ጨው መሆኑን እናያለን ምክንያቱም የሰማይ ጥበብን ወደ ምድር ስለሚያወርዱ ነው ብለዋል።

ይህንን እናስታውስ፡ ብፁዓን የሆኑ ተግባራትን በተግባር ካዋልን፣ የኢየሱስን ጥበብ ከያዝን፣ ለራሳችን ህይወት ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰብ እና ለምንኖርበት ሀገር ህይወትም ጣዕም እንሰጣለን ያሉ ሲሆን ጨው ምግብን ለረጅም ጊዜ ሳይበለሽ እንዲቀመጥ ለማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በመጠቆም እነርሱም ቢሆኑ ሳይበለሹ በትጋት ክርስቲያናዊ ግዴታቸውን መወጣት እንደ ሚገባቸው አክለው ገልጸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሳባቸውን ሲያጠናክሩ ከሌሎቹ ሁሉ በላይ ሊጠበቁ የሚገባቸው አንድ “ምግብ” አለ፣ እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ቃል ኪዳን እንዳለ ማስታወስ ነው ብለዋል።

ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እንጠብቅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጨው ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ለመጠበቅ መሠረታዊ ፍላጎታችንን ያስታውሰናል ያሉ ሲሆን ምክንያቱም እርሱ ለእኛ ታማኝ ነው፣ እናም ከእኛ ጋር ያለው ቃል ኪዳን "የማይጠፋ፣ የማይጣስ እና ዘላቂ" ነው ያሉ ሲሆን "እንደ ምድር ጨው፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ቃል ኪዳን በደስታ እና በምስጋና እንድንመሰክር ተጠርተናል..." በማለት ተናግረዋል።

ጥሩ ሰብዓዊ ግንኙነቶችን መገንባት "የክፋትን ብልሹነት፣ የመከፋፈል በሽታን፣ የተጭበረበረ የንግድ ሥራን እና የፍትሕ መጓደልን ለመቅረፍ ቁልፍ ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጠቁመዋል።

"ዛሬ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፣ ምክንያቱም በዚህች ሀገር ውስጥ የምድር ጨው ስለሆናችሁ" ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው  እናም ትንሽ እና አቅመ ቢስ ስሜት እንዳይሰማን አንዳንድ ጊዜ "ጥቃት የጥላቻ መርዝ ሲጨምር" እና " የፍትሕ መጓደል ድህነትንና ድህነትን ሲያስከትል” ሰላማዊ በሆነ መንገድ መቃወም ያስፈልጋል ብለዋል።

በጥቃቅን ነገሮች እንጀምር

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለደቡብ ሱዳናውያን አማኞች “ጥቃቅን እና ደካሞች ብንሆንም ከችግራችን ብዛትና ከጭፍን የጥቃት ቁጣ በፊት ኃይላችን ደካማ በሚመስልበት ጊዜ እንኳን እኛ ክርስቲያኖች ለለውጥ ወሳኝ አስተዋፅዖ ማድረግ እና ታሪክን መለወጥ እንችላለን” ብለዋል።

ኢየሱስ ልክ እንደ ጨው እንድንሆን ይፈልጋል፣ ምክንያቱም “ያቺ ትንሽ በእጅጃችን ቆንጥረን የምናነሳት ጨው” ከሌለ “ያለ እኛ ትንሽ ትብብር ጣዕመ ቢስ ትሆናለች” ብለዋል።

“ከጥቃቅን ነገሮች፣ ከዋና ዋና ነገሮች እንጀምር” ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በታሪክ መጽሐፍት ውስጥ ከሚታዩት ሳይሆን ታሪክን ከሚለውጠው ነገር እንጀምር ሲሉ አክለው የተናገሩ ሲሆን "በኢየሱስ እና በተራራ ላይ ባደረግው ስብከት ስም፣ የጸሎት እና የፍቅር ግንኙነታችንን ለማዳበር የጥላቻ እና የበቀል መሳሪያዎችን እናስቀምጥ" ሲሉ ተማጽነዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ " ሥር የሰደዱ " እና "ጎሳ እና ዘርን ባማከለ መለኩ እርስ በርስ የሚያጋጩትን" ጥላቻ እና ግጭቶችን እንዲያሸንፉ ጥሪ አቅርበዋል።

"በቁስላችን ላይ የይቅርታን ጨው መተግበርን እንማር፤ ጨው ያቃጥላል ነገር ግን ይፈውሳል" በማለት ልባቸው እየደማ እንኳን ክፋትን በክፉ ለመመለስ ፈቃደኞች እንደይሆኑ ተመጽነዋል።

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" ሲሉ ኢየሱስ ወደተጠቀመበት ሁለተኛው ምስል ማለትም ብርሃን  ወደ ሚለው ሐሳብ ስብከታቸውን ዞር አድርገዋል።

እግዚአብሔር ልጁን ላከ፣ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ “ለሰውና ለሕዝብ ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን” በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እንደ ተናገረ ሁሉ እነርሱ ደግሞ የዓለም ብርሃን መሆን እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናግሯቸው እንደ ነበረ አክለው ገልጸዋል።

"ይህ ማለት የክርስቶስን ብርሃን ስንቀበል ክርስቶስ የሆነውን ብርሃን ስንቀበል "ብርሀን" እንሆናለን፤ የእግዚአብሔርን ብርሃን እናበራለን” ስሉ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ኢየሱስ “በተራራ ላይ የተሠራች ከተማ ልትደበቅ አትችልም” ሲል መናገሩን አስታውሰው መብራት አብርቶ ዕንቅብ የሚደፋበት ሰው የለም፥ በመቅረዙ ላይ ለሁሉም እንዲያበራ ያስቀምጣል እንጂ ሲሉ ተናግረዋል።

በተራራ ላይ እንዳለች ከተማ አብሩ

ኢየሱስ የዓለም ብርሃን እንድንሆን ሲጠይቀን “እኛ ደቀ መዛሙርቱ የሆንን፣ በኮረብታ ላይ እንዳለች ከተማ፣ እሳቱም እንደማይጠፋ መብራት እንድንሆን ተጠርተናል" ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዙሪያችን ስላለው ጨለማ ከመጨነቅ በፊት ለከተማችን፣ ለመንደሮቻችን፣ ለመኖሪያ ቤቶቻችን፣ ለምናውቃቸው እና ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ ብርሃን እንድንሰጥ ተጠርተናል ብለዋል።

"ጌታ ኃይልን ይሰጠናል በእርሱ ብርሃን ውስጥ እንድንሆን ጥንካሬን ይሰጠናል" በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አበረታተዋል "እንግዲህ ሁሉም ሰው የእኛን መልካም ሥራ እንዲያይ እና እርሱን በማየት ኢየሱስን እያስታውሱ በእግዚአብሔር ደስ ይላቸዋል እና ክብርን ይሰጡታል" ማለታቸው ተገልጿል።

ብርሃንህ እንዲጠፋ ፈጽሞ አትፍቀድ

አንድ ጊዜ በምድር ላይ እንደ ወንድ ልጆች እና ሴቶች ልጆች ወይም ወንድሞች እና እህቶች ስንኖር አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ሰዎች ሁላችንም በሰማይ ያለ አባት እንዳለን ያውቃሉ” በማለት አበረታተዋል።

"እንግዲያውስ በፍቅር እንድንቃጠል፣ ብርሃናችን እንዳይጠፋ እንጠንቀቅ” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

ሊቀነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “ይህች አገር፣ በጣም የተዋበች፣ ነገር ግን በዓመፅ የተመሰቃቀለች፣ እያንዳንዳችሁ ያላችሁ ብርሃን ወይም የተሻለ፣ እያንዳንዳችሁ ያላችሁን ብርሃን ትፈልጋለች” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ደቡብ ሱዳንን በወንድማማችነት የወንጌል ጣዕም የምትዘረጋ፣ የምትሟሟ እና የምትቀምም ጨው ትሆናላችሁ” በማለት በጸሎት ደምድመዋል።

"በኮረብታ ላይ እንደተገነቡ ከተሞች ሁሉ የመልካምነትን ብርሃን እንዲያበሩ እና በልግስና እና እራስን በመስጠት መኖር ውብ እና የሚቻል መሆኑን ያሳዩ ዘንድ የክርስቲያን ማህበረሰቦቻችሁ በደመቀ ሁኔታ ይብራ። የታረቀ የወደፊት ሁኔታን ለመገንባት" እግዚአብሔር ይርዳችሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 

05 February 2023, 19:55