ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደቡብ ሱዳን ጁባ እያደረጉት የሚገኘው ሐዋርያዊ ጉብኝት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደቡብ ሱዳን ጁባ እያደረጉት የሚገኘው ሐዋርያዊ ጉብኝት  

የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ታሪክ በአጭሩ!

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዲሞክራትክ ሪፖብሊክ ኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን የሚያደርጉትን 40ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በጥር 23/2015 ዓ.ም መጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በኮንጎ የነበራቸውን የሦስት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው በዛሬው እለት ማለትም በጥር 23/2015 ዓ.ም ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ማቅናታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በማስከተል የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የሆነችውን የጁባን ከተማ አጠቃላይ ይዘት እንደሚከተለው በምናብ አናስቃኛችኋልን እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

ጁባ 525,953 ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ ስትሆን የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ዋና ከተማ፣ በጁቤክ የፌዴራል ግዛት ውስጥ ትገኛለች፣ ይህ ግዛት በ14 አውራጃዎች የተከፈለ ነው። ከተማዋ በነጭ አባይ ምዕራባዊ ዳርቻ ላይ ትገኛለች እና የግዛቷ አካል ከ16,000 ካሬ ኪ.ሜ በላይ የሆነ ጥበቃ ያለው የባንዲጊሎ ብሔራዊ ፓርክን ይመሰርታል ። የንግድ ማእከል እና በርካታ ወንዞች የሚገኙበት ግዛት ሲሆን የአገሪቷ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በዚያው ስፍራ ይገኛል፣ በ 1975 ዓ.ም የተገነባው የጁባ ዩኒቨርሲቲ በዚያ ስፍራ እንደ ሚገኝ ይታወቃል። ጁባ የተነሰረተችው በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ምንም እንኳን በክልሉ ውስጥ ትልቁ ከተማ ባትሆንም እና በጎንዶኮሮ ከተማ ጥላ ውስጥ ብትኖርም ፣ በሰሜን በኩል ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምትገኝ ፣ ለአንግሎ-ግብፃውያን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ቦታ በመሆኗ የተነሳ በወቅቱ ቅኝ ገዢ በሆነችው በብሪታንያ መሠረት ሆና ተመርጣለች። በዓባይ ምንጮች ምርምር ላይ የተሰማሩ ጉዞዎች የሚደረጉበት ስፍራ ያላት ሲሆን ። እ.አ.አ. በ1947 ዓ.ም ሱዳን አሁንም በእንግሊዝ እና በግብፅ የጋራ አስተዳደር ስር በነበረችበት ወቅት ከተማዋ የጁባ ኮንፈረንስ አዘጋጅታለች ፣በዚህም የሰሜን እና የደቡብ ሱዳን ተወካዮች በሀገሪቱ ውህደት ላይ ተስማምተዋል። ብዙ የደቡብ ሱዳን ነዋሪዎች ይህንን ውሳኔ ይቃወማሉ፣ ይህም ተከታታይ አለመረጋጋት እና ግጭቶችን አስነስቷል። እ.ኤ.አ. በ1955 ሱዳን ከታላቋ ብሪታንያ ነፃ ከመውጣቷ አንድ አመት ቀደም ብሎ፣ የመጀመሪያው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በቅኝ ግዛት ሥር በነበረችበት ወቅት ግጭቱ የተጀመረ ሲሆን ይህ ግጭት እ.አ.አ. እስከ 1972 ዓ.ም ድረስ እልባት አላገኘም ነበር። ከዚያም በ1983 እንደገና ቀጠለ እናም እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም አጠቃላይ የሰላም ስምምነት ተፈራረመ። ለደቡብ ሱዳን ክልል የራስ ገዝ አስተዳደር ይሰጣል። ከስምምነቱ በኋላ ጁባ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ሲሆን የክልል ዋና ከተማ ተብላለች። ደቡብ ሱዳን እ.አ.አ ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ደቡብ ሱዳን 54ኛው የአፍሪካ ሀገር ሆና በይፋ ስትመሰረት ጁባ የአዲሲቷ ነጻ አገር ዋና ከተማ ሆነች። ከተማዋ የተመረጠችው በባሪ ኢኳቶሪያል ህዝቦች እንጂ በዋና ዋና ብሄረሰቦች (ዲንቃ፣ ኑዌር፣ ሽሉክ) ስላልነበረ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ህዝቦች ከመጥቀም ተቆጥባለች። ጦርነቱ ያስከተለው ጠባሳ አሁንም በጣም ጥልቅ ነው፣ ህብረተሰቡ አሁንም በጣም ኋላቀር እና የወንጀል መጠኑ ከፍተኛ ነው፣ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም ላይ ትንሿ ዋና ከተማ ትልቅ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች። ይህም ነጋዴዎችን እና ባለሀብቶችን ከጎረቤት ሀገሮች እና  በውጭ አገር እና እ.አ.አ ከጥቅምት 2010 ጀምሮ በርካታ ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በግዛቷ ውስጥ እራሳቸውን አቋቁመዋል ። ዋና ከተማዋ ከአንዳንድ የክርስቲያን የአምልኮ ቦታዎች እና ከአንዳንድ የቅኝ ግዛት ዘመን ህንጻዎች ውጪ ከሥነ ሕንፃ አንፃር የተለየ ሀውልት ወይም ሕንጻ የላትም። ፍላጎቱ በከባቢ አየር ውስጥ ፣ በቀለማት ያሸበረቁ ገበያዎች ፣ በዋና ከተማው ውስጥ ዋናውን ኮንዮ ኮንዮን የሚባለውን ሥፍራ ጨምሮ እና በነጭ አባይ ዳርቻዎች ላይ በሚያየው አስደናቂ የተፈጥሮ ገጽታ ላይ ያተኮረ ነው። ከዋና ከተማዋ ተምሳሌታዊ ስፍራዎች መካከል የሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጪ ጦር መሪ እና የቀድሞ ምክትል ፕሬዚደንት የ"ጆን ጋራንግ" መካነ መቃብር እና የሊቀ ጳጳሱ መቀመጫ የቅድስት ቴሬዛ ካቶሊካዊ ካቴድራል ይገኙበታል።

እ.አ.አ በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም መንግስት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ከጁባ ወደ ራምሲኤል በሀይቅ ግዛት ውስጥ ወደምትገኘው እና የሀገሪቱ ጂኦግራፊያዊ ማእከል እንደምትሆን አስታውቋል። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ዝውውሩ ተግባራዊ አልሆነም። የጁባ ሀገረ ስብከት (እ.አ.አ ታኅሣሥ 12 ቀን 1974) የተመሰረተ ሲሆን  የቀድሞ ሐዋርያዊ አገረ ስብከት (እ.አ.አ በግንቦት 26 ቀን 1961 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን)፣ ከእዚያ ቀደም ደግሞ የቀድሞ የባሕር ኤል-ገብብል ሐዋርያዊ ግዛት (እ.አ.አ በመጋቢት 12 ቀን 1951 ሆኖ የተመሰረተ) እንደ ነበረ ከታሪክ መረዳት ይቻላል።

ይህ የጁባ አገረ ስብከት 25,137 ካሬ ኪ.ሜ ስፋት ያለው ሲሆን፣ 1,101,750 ነዋሪዎች በአገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ ይኖራሉ፥ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 849,000 የሚሆኑ ሕዝቦች የካቶሊክ እመነት ተከታዮች ሲሆኑ 16 ደብሮች ወይም ቁምስናዎች፣ 2 አብያተ ክርስቲያናት፣ 47 የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 26 መደበኛ የሀገረ ስብከት ካህናት፣ 12 የፍልስፍና እና የሥነ-መለኮት ተማሪዎች፣ 41 ገዳማዊያን፣ 71 ገዳማዊያት፣ 32 የትምህርት ተቋማት፣ 15 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚገኙበት ሀገረ ስብከት ሲሆን እ.አ.አ በ2017 ዓ.ም 11,746 ሰዎች ምስጢረ ጥምቀት የተቀበሉ እንደ ሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። 

03 February 2023, 14:25