ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከኮቦኒ ማሕበር አባላት ተወካዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከኮቦኒ ማሕበር አባላት ተወካዮች ጋር በተገናኙበት ወቅት   (Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለኮምቦኒያውያን ማሕበር አባላት ያለ ኢየሱስ ምንም ማድረግ አንችልም ማለታቸው ተገለጸ!

የኮምቦኒ ሚስዮናውያንን በዓለም አቀፋዊ አገልግሎታቸው ሲያበረታቱ ከጌታ ጋር የተዋሃዱ ሚስዮናውያን "የእግዚአብሔር ፍቅር መንገዶች ናቸው" በማለት ፍሬ ማፍራት የምንችለው በኢየሱስ እና በመንፈስ ቅዱስ ስንመራ ብቻ ነው በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መናገራቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እኛ የምናደርገው በክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ ነው፣ ያለ እግዚአብሔር ምንም ማድረግ አንችልምና በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህንን ማሳሰቢያ ለኮምቦኒ ሚሲዮናዊያን በቫቲካን ቅዳሜ በሰኔ 11/2014 ዓ.ም  የአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ስብሰባ በሮም አድርገው ካጠናቀቁ በኋላ ከቅዱስነታቸው ጋር በተገናኙበት ወቅት ነው።

እ.አ.አ በ1867 ዓ.ም በቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ የተመሰረተው የኮምቦኒ ሚሲዮናዊያን የአለምን ድሆች እና በጣም የተተዉ ሰዎችን ለማገልገል የሚሰራ አለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የሚተዳደር መንፈሳዊ ማሕበር ነው፣ ብዙ ጊዜ ባልተረጋጋ የፖለቲካ ድባብ ውስጥ እና በከፋ ድህነት ውስጥ ከሚሰቃዩ ሰዎች ጋር በመሥራት ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲወጡ የሚሰራ ማሕበር ሲሆን በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ ወደ 3,500 የሚጠጉ የኮምቦኒ ሚስዮናውያን በ41 አገሮች ውስጥ ይሠራሉ።

"ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም"

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ ሚስዮናውያንን አመስግነው የዓለም አቀፍ ስብሰባቸው  ጭብጥ እና መሪ ቃል አስታውሰዋል፡ "እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ" የሚለው እንደ ሆነ ያወሱት ቅዱስነታቸው ከቅዱስ ከኮምቦኒ ጋር በክርስቶስ ሥር ስደዱ ማለታቸው ተገልጿል።

መሪ ቃሉን በማንፀባረቅ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተልእኮ ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን እና የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ላይ ጥገኛ መሆንን እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ኢየሱስ ለሐዋርያቱ እንዲህ ሲል አጥብቆ እንደተናገረ አሳስቧቸው፡- ‘ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም (ዮሐንስ 15፡5) ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር አብራችሁ ካልተጓዛችሁ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትገባላችሁ ብለዋል።

"ትንሽ ልታደርግ ትችላለህ" አላለም። "ምንም ማድረግ አትችሉም" ነው ያለው። በምን መልኩ? ብዙ ነገሮችን ማድረግ እንችላለን፡ ተነሳሽነቶች፣ ፕሮግራሞች፣ ዘመቻዎች... ብዙ ነገሮችን፤ ነገር ግን በእርሱ ከሌለን መንፈሱም በእኛ ውስጥ የማያልፍ ከሆነ የምናደርገው ሁሉ በፊቱ ምንም አይደለም፤ ይኸውም ለእግዚአብሔር መንግሥት ምንም አይጠቅምም።

እኛ ይልቁንም በወይኑ ተክል ላይ በደንብ እንደተጣበቁ ቅርንጫፎች ከሆንን አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "የመንፈስ ቅዱስ ምንጭ ከክርስቶስ ወደ እኛ ውስጥ ይፈሳል፣ የምናደርገውም ሁሉ ፍሬ ያፈራል" ምክንያቱም የክርስቶስ ፍቅር በእኛ በኩል ስለሚሰራ ነው ብለዋል።

በክርስቶስ ልብ የተነዱ ታላላቅ ሚስዮናውያን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንዳስታወቁት፣ “እጆቻቸው፣ አእምሯቸው እና ልባቸው “የክርስቶስ ፍቅር መንገዶች” ከመሆናቸው የተነሳ ከጌታቸው ጋር አንድ ሆነዋል ብሏል።

“ለዚህም ነው እንደ ቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ ያሉ አንዳንድ ታላላቅ ሚስዮናውያን፣ ነገር ግን ለምሳሌ እናት ካባራኒ ተልእኳቸውን በክርስቶስ ልብ ተነድተው እና 'ተገፋፍተው' የኖሩት በዚሁ ምክንያት ነው። እናም ይህ 'በክርስቶስ ልብ መነዳት እንዲወጡ እና እንዲሄዱ አስችሏቸዋል፡ ከአገራቸው ወሰን እና ድንበር አልፈው ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በፊት ከገደባቸው በላይ መጓዝ የቻሉት በክርስቶስ ፍቅር ስለተነዱ ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “የመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት እራሳችንን እንድንተው፣ እንድንዘጋ፣ እራሳችንን እንድንጠቁም የሚያደርገን እና ወደ ሌሎች እንድንሄድ የሚያደርገን የወንጌል ጥማት ከፍተኛ ወደ ሆነበት ዳርቻ ይመራናል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያስታወሱት የክርስቶስ ልብ አስፈላጊ ባህሪያት ምሕረት፣ ርኅራኄ እና ፍቅር ናቸው። “ድንበር የማያውቅ ሁለንተናዊ ቋንቋ” እንደፈጠሩ ተናግሯል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦች የቅናት፣ የስልጣን ሽኩቻ እና የመተዳደሪያ ስፍራ እንደሚሆኑ፣ ፍቅር የሚጎድልባቸው ቦታዎች እንደሆኑ ገልጸው፣ ማህበረሰቡን እና ተቋማትን ለማደስ የሚረዳ የግለሰብ ህሊና እንዲለወጥ ጠይቀዋል።

20 June 2022, 13:25