ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ‘ኢየሱስ በመከራችን፣ በችግራችን፣ በልቅሶዋችን ወቅት በውስጣችን በማለፍ ይደግፈናል’ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘውተር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰብሰሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደርገ አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም ባደረጉት አስተንትኖ “በመከራችን፣ በችግራችን፣ በልቅሶዋችን፣ በውስጣችን በማለፍ ከሁሉም በላይ ይደግፈናል” ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

በእለቱ የተነበበው የቅዱስ ወንጌል ምንባብብ

“በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፤ እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም። እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም። እኔና አብ አንድ ነን” (ዮሐንስ 10. 27-30)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእለቱ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል በጌታ እና በእያንዳንዳችን መካከል ስላለው ትስስር ይነግረናል (ዮሐ. 10፡27-30)። ኢየሱስ ይህን ሲያደርግ ከበጎቹ ጋር የሚኖረውን እረኛ በሚያሳየው ርኅራኄና ውብ መልክ ተጠቅሟል። በሦስት ግሦችም ያብራራዋል፡- “በጎቼ”፣ ከእዚያም በመቀጠል “ድምፄን ይሰማሉ፣ እኔም አውቃቸዋለሁ እና  እነርሱም ይከተሉኛል” (ቁ. 27) በማለት ይናገራል። ይሰማሉ፣ ያውቃሉ፣ ይከተላሉ። እስቲ እነዚህን ሦስት ግሦች እንመልከት።

በመጀመሪያ በጎቹ የእረኛውን ድምፅ ይሰማሉ። ተነሳሽነት የሚመጣው ሁል ጊዜ ከጌታ ነው። ሁሉም የሚመጣው ከጸጋው ነው፤ ከእርሱ ጋር እንድንተባበር የጠራን እርሱ ነው። ግን ይህ ሕብረት የሚመጣው ራሳችንን ከፍተን እርሱን ለመሰማት ስንዘጋጅ ነው። ማዳመጥ መገኘትን፣ መቻልን እና ለውይይት የተሰጠ ጊዜን ያመለክታል። ዛሬ ሁል ጊዜ የምንናገረው ወይም የምንናግረው ነገር እንዲኖረን በቃላት እና በአጣዳፊ ነገሮች ተሞልተናል። በቤተሰባችን፣ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ እንኳን እርስ በርስ መደማመጥ ምንኛ ከባድ ነው! ለጌታ ግን በመጀመሪያ ማዳመጥን እና ለማዳመጥ ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል። እርሱ የአብ ቃል ነው፣ ክርስቲያኑ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ ለመኖር የተጠራ ሰሚ ልጅ ነው። ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ቦታ እና ትኩረት ከሰጠን ለእግዚአብሔር ቃል ጊዜ ካገኘን እንደ ልጆቹ ሆነን እየሰማን እንደሆነ ራሳችንን እንጠይቅ። ሌሎችን የሚያዳምጡ ጌታንም ያዳምጣሉ እና በተቃራኒው ሌሎችን የሚያዳምጡ ጌታን ያዳምጣሉ። እናም አንድ በጣም የሚያምር ነገር አጋጥሟቸዋል፣ ማለትም ጌታ ራሱ ይሰማል - ስንጠራው እርሱን ስንመሰክር ወደ እርሱ ስንጸልይ ያዳምጠናል።

ኢየሱስን ማዳመጥ እርሱ እንደሚያውቀን የምናውቅበት መንገድ ይሆናል። መልካሙን እረኛን የሚመለከት ሁለተኛው ግሥ ይህ ነው። በጎቹን ያውቃል። ይህ ማለት ግን ስለ እኛ ብዙ ነገሮችን ያውቃል ማለት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መልኩ ማወቅ ከፍቅር ጋር ተመሳሳይ ነው። ጌታ "ውስጣዊ ማንነታችንን ሲያነብ" ይወደናል ማለት ነው። እርሱን ከሰማነው ይህንን እናስተውላለን - ጌታ እንደሚወደን እንገነዘባለን። በመሆኑም ከእሱ ጋር ያለን ዝምድና ግላዊ፣ ሞቅ ያለ እና በግንባር ቀደምትነት ከእርሱ ጋር የምናደርገው ግንኙነት ነው። ኢየሱስ ሞቅ ያለ ጓደኝነትን፣ መተማመንን እና መቀራረብን እየፈለገ ነው። አዲስ እና አስደናቂ ግንዛቤ ሊሰጠን ይፈልጋል - ሁል ጊዜ በእርሱ እንደምንወደድ ማወቅ እና ስለዚህ እኛ በራሳችን ብቻ እንዳልተወን ማወቅ ያስፈልጋል። ከመልካሙ እረኛ ጋር መሆናችን መዝሙረ ዳዊት የተናገረውን ተሞክሮ እንድንኖር ያስችለናል፡- “በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ክፉን አልፈራም። አንተ ከእኔ ጋር ነህና” (መዝ 23፡4)። በመከራችን፣ በችግራችን፣ በልቅሶዋችን፣ በውስጣችን በማለፍ ከሁሉም በላይ ይደግፈናል። እናም፣ በተለይ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ነው፣ በጌታ እንደምንታወቅ እና እንደተወደድን ልናገነዘብ የምንችለው በዚሁ መልኩ ነው። እንግዲያው፣ እራሳችንን እንጠይቅ፡ ጌታ እንዲያውቅኝ አደርጋለሁ ወይ? በህይወቴ ውስጥ ለእሱ ቦታ እሰጠዋለሁ ወይ? ኑሮዬን ለእርሱ እሰጠዋለው ወይ? እና የእሱን ቅርበት፣ ርህራሄ፣ ቸርነት ካገኘሁት ከብዙ ጊዜ በኋላ ስለ እሱ ምን ሀሳብ አለኝ? አሁንም እርሱን እንደ ሩቅ እና ከእኔ ሕይወት ርቆ ነው የሚገኘው ብዬ ነው አምላክን የማስበው ፣ በእርሱ ላይ ያለኝን የግድየለሽነት መንፈስ እንዴት ነው የማስወግደው? ወይም ይልቁንም እርሱ የሚያውቀኝ እና የሚወደኝ እንደ ጥሩ እረኛዬ አድርጌ ነው የምመለከተው?

በመጨረሻ፣ ሦስተኛው ግሥ፡- የሚሰሙትና የሚያውቁት በጎች እረኛቸውን እንደሚከተሉ ይታወቃል። ክርስቶስን የሚከተሉ ምን ያደርጋሉ? ወደሚሄድበት፣ በአንድ መንገድ፣ በአንድ አቅጣጫ ይሄዳሉ። የጠፉትን ሊፈልጉ ይሄዳሉ (ሉቃ. 15፡4)። በሩቅ ያሉትን ያስባሉ፣ የሚሰቃዩትንም ሁኔታ ያስተውላል፣ ከሚያለቅሱትም ጋር እንዴት ማልቀስ እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ እና እጁን ወደ ጎረቤቱ ዘርግቶ በትከሻው ተሸክሞ ይሄዳል። እና እኔ በዚህ ረገድ ምን ማድረግ እችላለሁ? ኢየሱስ እንዲወደኝ ብቻ ነው የምፈቅደው ወይስ ከመውደድ ባሻገር ከእርሱ ጋር ግንኙነት አለኝ? ክርስቶስን ሰምተን ዘወትር እንድናውቀው እና በአገልግሎት መንገድ እንድንከተለው ቅድስት ድንግል ማርያም ሁላችንንም ትርዳን።

08 May 2022, 12:18