ፈልግ

በዩክሬይን እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ብዙ ሰዎች እየሸሹ ከአገራቸው ወጥተው እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚያሳይ ምስል በዩክሬይን እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ብዙ ሰዎች እየሸሹ ከአገራቸው ወጥተው እየተሰደዱ መሆናቸውን የሚያሳይ ምስል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጦር መሣሪያዎች አማካይነት ለማይገኘው የሰላም ዓይነት እንጸልይ ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጦርነት በተጠቁ አገሮች ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን በድጋሚ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን እናም የጦር መሳሪያ ሰላም እንደማያመጣ ለሚያውቁት ሁሉም አማኞች ለህዝቦቻቸው ሰላም እንዲመኙ እና እንዲጸልዩ መጠየቃቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህ አሁን የምንገኝበት ወር የግንቦት ወር እንደ ሆነ ይታወቃል። ይህ የግንቦት ወር በወር ደረጃ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ “የማርያም ወር” በመባል የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ የግንቦት ወር ውስጥ የክርስቶስ፣ የቤተክርስቲያን፣ የእግዚአብሔር እና የምዕመናን እናት ለሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለየት ባለ መልኩ ጸሎት የሚደርግበት፣ አማልጅነቷን የምንማጸንበት፣ በተለይም ደግሞ በልባችን፣ በቤተሰባችን፣ በማኅበረሰባችን፣ በአገራችን እና በአጠቃላይ በዓለም ውስጥ የጥል እና የክርክር ግድግዳ ተደርምሶ በአንጻሩ የሰላም እና የብልጽግና መንፈስ ይወርድ ዘንድ በእርሷ አማላጅነት ወደ ልጇ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመማጸኛ ጸሎት እንድታቀርብልን እርሷን በተለየ ሁኔታ በመቁጠሪያ ጸሎት የምንማጸንበት ወር ነው የግንቦት ወር።

በዚህም መሰረት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” (ይህ ‘የሰማይ ንግሥት ደስ ይበልሽ’ የተሰኘው መዝሙር ከሌሎች ዐራት የማርያም መዝሙሮች ማለትም የአዳኛችን እናት፣ የሰማይ ንግሥትና፣  ጸጋን የተሞላሽ ከሚሉት ጸሎቶች ጋር የማርያም መዝሙር በመባል ይታወቃል። እ.አ.አ ማለትም በ 1742 ዓ.ም በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በኔዴክቶስ 14ኛ ባወጁት መሰረት ይህ “የሰማይ ንግሥት ሆይ ደስ ይበልሽ” የተሰኘው ጸሎት ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን በማስመልከት “የእግዚኣብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን ጸሎት ተክቶ ከበዓለ ፋሲካ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ድረስ ተቁሞ እንዲደገም ባዘዙት መሰረት የሚደገም ጸሎት ነው) ከተሰኘው ጸሎት በኋላ እንደ ተለመደው ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት ለእመቤታችን ጸሎታቸውን አደራ በመስጠት በድጋሚ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

“በመንፈስ በድንግል ፊት ተንበርክካለሁ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ የብዙ ሰዎች ሰላም እንዲሰፍን ልባዊ ፍላጎት እንዲኖራት አደራ እላታለሁ፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩት ትርጉም የለሽ የጦርነት ጥፋት እንዲቀር እርሷን እማጸናታለሁ” በማለት ተናግሯል።

"ለቅድስት ድንግል" ማርያም ልብ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት "በተለይ የዩክሬን ህዝብ ስቃይ እና እንባ አቀርባለሁ" ማለታቸው ተገልጿል። አሁን ባለንበት “በጦርነት እብደት ውስጥ፣ እባካችሁ፣ በየእለቱ ለሰላም የመቁጠሪያ ጸሎት መጸለይን እንቀጥል” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን "ሰላም ለሚፈልጉ ህዝቦቻቸው 'ስሜታቸውን' እንዳያጡ እና የጦር መሳሪያ በጭራሽ ሰላምን እንደማያመጣላቸው በደንብ እንዲያውቁ” መጸለይ ይኖርብናል ብለዋል።

የጦር መሳሪያ መግዛት ለማንኛውም ግጭት መፍትሄ አይሆንም

እ.ኤ.አ. የካቲት 24/2014 ዓ.ም ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለጦርነቱ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲገኝ ደጋግመው ጠይቀዋል።

እ.አ.አ በመጋቢት 23/2022 ዓ.ም ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት በዩክሬን ውስጥ ያለው ጦርነት የሰው ልጅ  "ራስን ማጥፋት" እንግዳ የሆነ ውስጣዊ ስሜትን ማፍሰስ እንደነበረበት እና ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን መግዛት ለማንኛውም ግጭት የመጨረሻ መፍትሄ እንዳልሆነ መናገራቸው ይታወሳል።

ጳጳሱ በጦርነቱ ሰለባ የሆኑትን ሁሉ ማለትም ሙታንን፣ “በአንድ ወገን ወይም በሌላ በኩል የወደቁ ወታደሮች” የቆሰሉትን፣ ቤት የሌላቸውን እና ስደተኞችን በጸሎት እንዲያስታውሱ ምዕመናንን የጠየቁ ሲሆን “ይህን እንድንረዳ ጌታ መንፈሱን ይላክልን። ጦርነት የሰው ልጅ ሽንፈት ነው" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሳምንታዊ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

08 May 2022, 13:51