ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዩክሬን ጦርነት የኃያላን አገራት አመክንዮ እውን እየሆነ ነው ማለታቸው ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አከባቢ ላይ መጋቢት 24 እና 25/2014 ዓ.ም ላይ ማለት ነው በማልታ ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገው እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ በጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እርሳቸው ዘወትር ረቡዕ እለት የሚያደርጓቸውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለመከታተል በመጋቢት 28/2014 ዓ.ም ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባደርጉት አስተምህሮ ላይ ቀደም ሲል ለመጠቀስ እንደሞከርነው በማልታ አድርገውት ሰለነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት መናገራቸው ተገልጿል። በወቅቱ ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት በአሁን ወቅት በዮክሬይን እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት በተመለከተ ሲናገሩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃይል እየተዳከመ በመምጣቱ የተነሳ በድርጅቱ ውስጥ የሚጸባረቀው “ዋናዎቹ አመክንዮዎች በጣም ኃያላን አገሮች ጥቅሞቻቸውን የሚያረጋግጡ ስልቶች በመተግበር ላይ ናቸው” በማለት በምሬት መናገራቸው ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ረቡዕ እለት ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዩክሬን ያለውን ጦርነት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አቅም ማጣትን በመቃወም ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ጥረቶች ቢደረጉም በታላላቅ ኃያላን በሚባሉ አገራት መካከል ያለው "የቀድሞው ታሪክ" ውድድር እንዴት እንደቀጠለ ያሳየናል ብለዋል።

መከባበር እና ለሰላም መስራት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ባለፈው ሣምን መጨረሻ ላይ በማልታ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ ያተኮሩ ሲሆን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሰላምን ለማስፈን ቢሞከርም በታላላቅ ኃያላን አገራት መካከል ያለው ፉክክር እንዴት እንደቀጠለ አስምረውበታል።

በዛሬው ጊዜ በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቅመ ቢስነት” እንድንመሰክር አድርጎናል ብለዋል። "በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለም አቀፍ ድርጅቶች አቅመ ቢስ መሆናቸውን እናያለን" ብለዋል።

ይህንን ቅዱስነታቸው የተናገሩት በማልታ በአውሮፓ እና በአፍሪካ መካከል እና በኤዥያ አቅራቢያ በምትገኝ እስትራቴጂያዊ ቦታ ላይ እንዴት እንደሚገኝ እና ከአለም ዙሪያ ያሉ ህዝቦች የሚገናኙበት ቦታ እንዳደረገው በገለጹበት አውድ ውስጥ ነው።

እናም በታሪክ እና በስልጣኔ የበለፀገችው ማልታ ዓለማችንን በመከባበር፣ በነጻነት እና በሰላም አብሮነት መግለጽ ያለበትን አስተሳሰብ የሚወክል ቢሆንም፣ የበላይ የሆነው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ዛሬም የበላይ እየሆነ መቀጠሉ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው ብለዋል።

"በተለመደ ደግነት" አቀባበል አድርገውልናል

ሐዋርያው ​​ቅዱስ ጳውሎስ በማልታ ደሴት አከባቢ በደርሰበት ወቅት በዚያ መርከቡ ከተሰበረ በኋላ “ባልተለመደ ደግነት” ነዋሪዎቹ እርሱን እና ጓደኞቹን እንዴት እንደ ተቀበሉ በሚተርከው ከሐዋርያት ሥራ ላይ በተወሰደው የማልታ ጉዞ መሪ ቃል በማስታወስ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ እነዚያን ቃላት “ባልተለመደ ደግነት” የሚለውን መሪ ቃል በመምረጥ እኛም ክርስቲያኖች በዚህ መንገድ መጓዝ ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል።

ይህም ስደተኞችን ብቻ ሳይሆን የበለጠ ወንድማማችነትን የሚፈጥር፣ ለኑሮ ምቹ የሆነ ዓለም የሚፈጥር ደግነት፣ ሁላችንም “በተመሳሳይ ጀልባ ውስጥ ስለሆንን” ሁላችንም ሊያጋጥመን ከሚችለው “የመሰበር አደጋ” የሚያድነን መሆኑን ገልጿል። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የማልታ ነዋሪዎች ላደረጉላቸው መልካም አቀባበል ሕዝቡን እና የአገሪቷን ባለ ሥልጣናትን አመስግነዋል።

ስደተኞችን መቀበል እና መረዳት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማልታ የሚገኘውን ስደትን አስመልክቶ ሁለተኛው ቁልፍ ጭብጥ ላይ ሐሳባቸውን ያደረጉት በዮሐንስ 23ኛ የስደተኞች መቀበያ ማእከል ብዙ አሰቃቂ የባህር ጉዞዎችን ተከትሎ ወደዚያ ደርሰው በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙትን ስደተኞች መጎብኘታቸውን ተናግረዋል። ይህንን ክስተት በመገናኛ ብዙሃን ከቀረበው የተዛባ እይታ ባሻገር በመሄድ ሁሌም ታሪካቸውን ለመስማት ክፍት መሆን እንዳለብን አሳስበዋል።

እያንዳንዱ ሰው ታሪክ አለው፣ ቁስሉን ይሸከማል፣ ሥር መሰረት እና ባህል አለው፣ ሁሉም የሰው ክብር ያለው፣ “እያንዳንዳቸው መቀበል ከሚያስከትላቸው ችግሮች እጅግ የላቀ ሀብት ተሸካሚ ነው” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተለይ “የሰላም ቤተ-ሙከራ” ተብሎ የሚጠራው የዮሐንስ 23ኛ ማእከልን የመሰረቱትን የ91 አመቱን አባ ዳዮኒሲየስ ሚንቶፍ እጅግ በጣም ያመሰገኑ ሲሆን ስደተኞችን በመቀበል እና በመርዳት፣ በወንድማማችነት፣ በመተሳሰብ እና በፍቅር የመገናኘትን እና የሰላም ባህልን በመፍጠር ስራቸውን በመቀጠላቸው ቅዱስነታቸው አመስግነዋል።

ቀጣይነት ያለው የወንጌል ትሩፋት

በማጠቃለያው ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ብዙ ካህናት፣ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት እና ምእመናን በዓለም ዙሪያ ክርስቲያናዊ ምሥክርነታቸውን የሰጡበት የማልታ ቁልፍ ሚና ለወንጌል መስበክ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የቅዱስ ጳውሎስን ፈለግ በመከተል የጉብኝቱን ጉዞ ከማስታወስ በተጨማሪ፣ በጎዞ በሚገኘው የታፒኑ ብሔራዊ የማርያም ቤተመቅደስ በጉብኙበት ወቅት ማርያም ከእርሳቸው ጋር አብራ እንደ ነበረች እንደ ተሰማቸው አክለው ገልጸዋል፣ ማርያምን እጅግ በጣም አምስግነዋል ብለዋል።

06 April 2022, 12:06