ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማልታ ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና ጋር ሆነው የሚያሳይ ምስል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማልታ ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና ጋር ሆነው የሚያሳይ ምስል   (Vatican Media)

ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና ‘ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በማልታ ጉብኝት ላይ በእርግጠኝነት ያስደንቁናል' ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ላይ ማለትም ከመጋቢት 24-25/2014 ዓ.ም በማልታ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ሊቀ ጳጳስ ቻርለስ ሺክሉና የሐዋርያዊ ጉዞውን ዋና መሪ ሃሳቦች አጉልተው ገልጸው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በድንገት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉንም ሰው እንደሚያስደንቅ ተናግረዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በማልታ የሚገኙ ካቶሊካዊያን ከመጪው መጋቢት 24-25/2014 ዓ.ም በሜዲትራኒያን ደሴት ላይ የሚጎበኟቸውን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን መምጣት በጉጉት እየተጠባበቁ ነው።

ከሐዋርያዊ ጉዞ በፊት የማልታ ሊቀ ጳጳስ ቻርለስ ሺክሉና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

"ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁልጊዜ በሚያደርጋቸው ድንገተኛ ምልክቶች ያስደንቁናል፣ እናም ከሐዋርያዊ ጉብኝቱ በኋላ፣ 'አሁን ይህ በፕሮግራሙ ውስጥ አልነበረም፣ ግን ያ በእኔ ዘንድ ይኖራል' ማለት እንችላለን” ብለዋል።

በዩክሬን ጦርነት መካከል እርቅ

የማልታ ሊቀ ጳጳስ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ በተፈጠረው ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸው ምናልባትም ለዓለም የሰላም እና የእርቅ መልእክት እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እሁድ እለት በፍሎሪያና ከተማ መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ የቤተክርስቲያኗ የአምልኮ ሥርዓት ኢየሱስ በዝሙት ከተያዘች ሴት ጋር የተገናኘበትን ሁኔታ በሚገልጽ የቅዱስ ወንጌል ታሪክ ላይ ያተኮረ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና አክለው እንደ ተናገሩት ከሆነ ይህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል የሴቲቱ ምስኪን ሁኔታ በኢየሱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ምሕረት እንዴት ሙሉ እንደሚሆን፣ በዚህ ቀውስ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የራሳችንን ፍላጎት ምልክት ነው ብለዋል።

"ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእኛ የማልታ ሰዎች እና ለዓለም በማልታ ሆነው ይሰብኩናል፣ ዓለም ሁሉ ይህንን ስለእርቅ የሚናገረውን ቅዱስ  ወንጌል ሊሰማ በሚፈልገው አውድ ውስጥ፣ ለማይኮንነው ነገር ግን በአዲስ መልክ እንድንጀምር የሚገፋፋንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስታውስ ነው” ማለታቸው ተገልጿል።

ትንቢታዊ ድምፅ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በሚያዚያ 2010 ዓ.ም ማልታ በወቅቱ ጎብኝተው ከነበሩት ከእርሳቸው በፊት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ቤኔዲክት 16ኛን ፈለግ በመከተል ማልታን የሚጎበኙ ሲሆን ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና በማልታ የሚገኘው ቤተክርስቲያን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አስተምህሮ እና አዳዲስ መመሪያዎችን በተጠረጠሩ የመብት ጥሰት ጉዳዮች ላይ በጥንቃቄ በመተግበር ላይ ትገኛለች ብለዋል።

"ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ በቃላቸው፣ በምልክታቸው፣ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እና በሁኔታዎች የእርቅ መንገድን ያመላክታሉ ብዬ አስባለሁ ብለዋል።

ነገር ግን ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና አክለው እንደገለጹት ከሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት "ይህን በራሳቸው ብቻ ማድረግ አይችልም፣ ምክንያቱም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱስ አባታችንን አመራር ማዳመጥ እና እንዲሁም አሁን በጣም ግልጽ የሆኑትን መመሪያዎች በመከተል በመሬት ላይ መተግበር አለባቸው” ብለዋል።

በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሞላ

ሊቀ ጳጳሱ ወደ ማልታ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ድምቀት ምን እንደሚሆን የተጠየቁት ሊቀ ጳጳስ ሺክሉና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ አከባበር ሁል ጊዜ የጳጳሱ ጉዞ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ ገልጸዋል።

ነገር ግን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማንኛውም በጹሑፍ ከተደረጉ አስተያየቶች ወይም ድርጊቶች በበለጠ በኃይል በሚናገሩ ድንገተኛ ምልክቶች ይታወቃሉ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁል ጊዜ በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሞሉ ናቸው፡- “ስለዚህ ይህ ሁሉ ካለፈ በኋላ ሰኞ ምን ማለት እንደምንችል አስባለሁ፣ እና መልካም እንዲሆን እንጸልይ” ማለታቸው ተገልጿል።

01 April 2022, 15:57