ፈልግ

ደቡብ ኮሪያ የዓለም የውሃ ቀን አስመልክቶ የአከባቢ ጽዳት ሲደረግ የሚያሳይ ምስል ደቡብ ኮሪያ የዓለም የውሃ ቀን አስመልክቶ የአከባቢ ጽዳት ሲደረግ የሚያሳይ ምስል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለጦር መሣሪያ ግዢ ገንዘብ ማውጣት 'ሰብአዊነትን ያበላሻል' ማለታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን የሚያስተዋውቁ ለበጎ ፈቃደኞች ድርጅት ንግግር ካደረጉ በኋላ ሀገራት በሀብቶች ላይ የሚነሱ ግጭቶችን ወደ ጎን በመተው ይልቁንም ሁለንተናዊ ችግሮችን ለመጋፈጥ እንዲተባበሩ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከተመሰረተ አሥር ዓመታት በኋላ ሰኞ መጋቢት 12/2014 ዓ.ም “ተጠማሁ” በሚል መጠሪያ የተሰየመው የበጎ ፈቃደኞች ማኅበር አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ንግግር ባደረጉበት ወቅት አባላቱን “ግልጽ እና አጣዳፊ ዓላማቸው፡ የመጠጥ ውኃ ለሌላቸው ሰዎች ለማምጣት መጣር በመሆኑ” አመስግነዋል ብለዋል።

ንፁህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የውሃ አቅርቦት በተለይም ንጹህ የመጠጥ ውሃ "ለፕላኔቷ ህይወት እና በህዝቦች መካከል ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው" በማለት ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት።

ምንም እንኳን ሁላችንንም የሚያሳስበን ጉዳይ ቢሆንም፣ በአለም እና በተለይም በአፍሪካ፣ "ይህን ቀዳሚ ጥቅም ማግኘት ባለመቻላቸው ከሌሎች በበለጠ የሚሰቃዩ ህዝቦች አሉ" ብለዋል።

ለዚህም ነው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “በአፍሪካ፣ በብዙ አገሮች፣ በተለያዩ የአህጉሪቱ ክልሎች ሰብዓዊ ፕሮጀክቶቻችሁን አከናውናችኋል” በማለት ሥራቸው “ሚስዮናውያን እና በአካባቢው ያሉ የቤተ ክርስቲያን ማህበረሰቦች ጋር ሁልጊዜም ከአገር ውስጥ ሠራተኞች ጋር በመተባበር የሚሠራ ነው” ብለዋል።

ውሃ ሕይወት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የቡድኑን ስም በመጥቀስ “ተጠማሁ” በማለት ኢየሱስ የተናገረውን በመጥቀስ “ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት፣ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል” (ማቴ 25:35, 40) በማለት መናገራቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

“ብዙ የሚጠጣ ውሃ በማይኖርበት ወቅት ጥማት አይጎዳም። ነገር ግን ከጎደለ እና ለረጅም ጊዜ የሚጎድል ከሆነ ጥማት ሊቋቋሙት የማይችሉት እንደሚሆን እናውቃለን። በምድር ላይ ያለው ሕይወት በውሃ ላይ የተመሰረተ ነው፤ እኛ ሰዎችም ውሃ ያስፈልገናል። ለመኖር ሁላችንም እህት ውሃ እንፈልጋለን!

ለምን ጦርነት አስፈለገ?

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህን በማሰብ ከመተባበር ይልቅ አንዳንድ ጊዜ ግጭት ለምን በውኃ አቅርቦት ላይ እንደሚከሰት ጥያቄ አቅርበዋል።

"እርስ በርሳችን በመነጋገር መፍታት በሚገባን ግጭቶች ላይ መነጋገር ስንችል እርስ በእርሳችን ለምን ጦርነት እንከፍታለን? በምትኩ ለምን ኃይላችንን እና ሐብታችንን አናስተባብርም? እውነተኛ ስልጣኔ ጦርነቶችን፣ ረሃብንና ጥማትን፣ በሽታን መዋጋት ነው። ከጦርነት፤ ከድህነት እና ከዘመናዊ ባርነት ጋር የሚደረገው ትግል፤ ለምን አስፈለገ?፣ የሰው ልጆችን ሕይወት ለመታደግ ነው” ሲሉ ጳጳሱ በድጋሚ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጦር መሣሪያን በተመለከተ ሲናገሩ ንቃተ-ህሊና የመፍጠር አስፈላጊነትን አጉልተው ደጋግመው የተናገሩ ሲሆን “ነፍስን ያቆሽሻል ፣ ልብን ያቆሽሻል ፣ የሰውን ልጅ ያቆሽሻል” ብለዋል ።

አንዳንድ ምርጫዎች ገለልተኛ እንዳልሆኑ፣ ለምሳሌ ከፍተኛ ወጪን ለጦር መሳሪያ ግዢ መመደብ፣ በመጨረሻም ይህ ማለት ደግሞ "ለሌላ ሰላማዊ አገልግሎት ከሚውል ገንዘብ ላይ መውሰድ ማለት ነው፣ ይህም ማለት የሚያስፈልጉንን ነገሮች በማጉደል ገንዘቡን ለሌላ ማለትም ለጦር መሳሪያ ግዢ ማዋል ማለት ነው” ብለዋል።

"ሁሉንም ነገር እና ሁሉንም ወደ ኋላ የሚወስድ እና የሚጎትት ጦርነት እያለ፣ በድህነት ላይ፣ በረሃብ ላይ፣ በፕላኔቷ ላይ ያለውን ውድመት በመቃወም ሁላችንም በአለም አቀፍ ደረጃ በአንድነት መዝመታችን ምን ጥቅም አለው?” ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

ትንሽ ግን ፍሬያማ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን ባጠቃለሉበት ወቅት ለአባላቱ አጽንኦት ሰጥተው እንደ ገለጹት በእነዚህ ታላላቅ ችግሮች ፊት ይህ ድርጅት በእርግጠኝነት ትንሽ ነው፣ “ነገር ግን ወሳኝ በሆነ ነጥብ ላይ እየሰራ ነው፣ እናም በትክክለኛው መንገድ በጥሩ ሁኔታ እየሰራ ነው፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣ በጣሊያን እና በዓለም ውስጥ ሌሎች የበጎ ፈቃድ ድርጅቶች ለሚያከናውኗቸው ተግባራት አመሰግናለሁ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

23 March 2022, 11:12