ፈልግ

የቅዱስ አጉስጢኖስ ቀኖናዎች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ የቅዱስ አጉስጢኖስ ቀኖናዎች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ በሕመም እና በብቸኝነት ለሚሰቃዩ ወጣቶች እንክብካቤ እንዲደረግላቸው አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ያካሄዱት የቅዱስ አጉስጢኖስ ቀኖናዎች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር አባላትን በቫቲካን ተቀብለዋቸዋል። ቅዱስነታቸው ለአዲሱ ትውልድ የሚቀርቡ ትምህርቶች ማጠናከርን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር፣ በተለይ በጤና ቀውስ ምክንያት የስነ ልቦና ችግር ለደረሰባቸው እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወጣቶች ልዩ ትኩረት እንዲደረግላቸው አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የፍጆታ አቅርቦት በበዛበት ዓለም፣ አዲሱ ትውልድ ልብን በሚሰብር ብቸኝነት፣ በሐሰተኛ ደስታ ፍለጋ እና ከኅሊና መነጠል በሚመነጨ ብቸኝነትን እየተሰቃየ እንደሚገኝ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። የሰውን ልጅ ከዚህ ፈተና የሚወጣበትን መንገድ ማስተማር መፍትሄ መሆኑን አስረድተዋል።

በሁሉም ረገድ ትውልዶችን ለማስተማር እና ለማሰልጠን የወሰኑ የቅዱስ አጉስጢኖስ ቀኖናዎች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር አባላት ተልዕኮ፣ በተለያዩ እውነታዎች ውስጥ ሆነው በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው አማካይነት እምነትን ማወጅ፣ በጋራ ሕይወት መሳተፍ እና ከተለያዩ ባሕሎች ጋር መገናኘት መሆኑ ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለማኅበሩ ደናግል ባቀረቡት የማበረታቻ መልዕክታቸው ደናግሉ በብጹዕ አቡነ ሂፖና አስተምህሮች ላይ በመመሥረት የሚያቀርቡት ትምህርቶች፣ እምነት፣ ፍትህ፣ ዕድገት እና ከድሆች ጋር መሆንን በማስተማር “ሚሲዮናዊ ደቀ መዛሙርት፣ የተስፋ እና የደስታ መልዕክተኞች እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ወጣቶችን ለማግኘት አዳዲስ መንገዶችን መፈለግ

"የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር የትምህርት ስምምነት" የሚለውን የጠቅላላ ጉባኤ መሪ ርዕሥ ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የማኅበሩ አባላት ለወጣቶች አጠቃላይ እድገት አስተዋፅዖ ለማድረግ እና የዕለት ተዕለት እውነታቸውን ለመድረስ በሚያስችሉ አዳዲስ መንገዶች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው፣ የማኅበሩ አባላት ወጣቶች አስጊ በሆኑ ፈተናዎች እና አደጋዎች ውስጥ በሚገኙበት ጊዜ፣ ጥረታቸው ከቅዱስ ወንጌል በሚያገኙት ኃይል መነሳሳትን በማግኘት ማኅበረሰብንበየመገንባት ምኞታቸውን እንደሚያሳኩ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

የተጎዱትን መንከባከብ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የቅዱስ አጉስጢኖስ ቀኖናዎች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር ቁርጠኝነት እና ምስክርነት ደካሞችን እና ለጉዳት የተጋለጡትን ወደ ጎን ለሚል ዓለም ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ መሆኑን ተገንዝበው፣ የማኅበሩ ደናግል ተልእኳቸውን በፍሬያማነት ለመቀጠል ኃይላቸውን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በወረርሽኙ ምክንያት ተስፋ የቆረጡትን መጎብኘት

“አዳዲስ አድማሶችን መክፈት እና ለወንድማማችነት ቦታ መስጠት”፣ የቅዱስ አጉስጢኖስ ቀኖናዎች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅበር ለዓለም የሚያበረክተው አገልግሎት መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ ማኅበሩ "እያንዳንዱ ሰው የክርስቶስን ፍቅር እንዲያውቅ ለማድረግ ያለመ" መሆኑንም አስታውሰዋል። በመጨረሻም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለማኅበሩ ደናግል ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ከብዙ ገጽታዎቹ መካከል በተለይም በትምህርቱ ዓለም እና በወጣቶች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረበት ጊዜ ነው” ብለው፣ ደናግሉ በአገልግሎታቸው ከማኅበሩ የተገለሉትን፣ ያዘኑትን እና ተስፋ የቆረጡትን ሰዎች እንዲጎበኟቸው አደራ ብለዋል።

26 January 2022, 13:57