ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሊቀ ጳጳስ ኤሮኔይሞስ 2ኛ ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሊቀ ጳጳስ ኤሮኔይሞስ 2ኛ ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከሊቀ ጳጳስ ኤሮኔይሞስ 2ኛ ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ።

የኦርቶዶክስ ዋና ሊቀ ጳጳስ ኢሮኒሞስ 2ኛ የአቴንስ እና የመላው ግሪክ ሊቀ ጳጳስ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በአቴንስ በሚገኘው የቅድስት መንበር ቋሚ ጽሕፈት ቤት ውስጥ መገናኘታቸው ተገልስጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ብፁዕ አቡነ ኢሮኒሞስ 2ኛ የአቴንስ እና የመላው ግሪክ ሊቀ ጳጳስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ ሮም በሚመለሱበት እለት ዋዜማ እሁድ አመሻሽ ላይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በአገሪቷ በሚገኘው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ግቢ ውስጥ መገናኘታቸው የተገለጸ ሲህን የግሪክ የኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከግብረ አበሮቻቸው ጋር የተደረገው ውይይት በጽሕፈት ቤቱ ዋና ክፍል ውስጥ የተካሄደ ሲሆን 30 ደቂቃ የፈጀ እንደ ነበረም ተገልጿል።

በስብሰባው ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እና ሊቀ ጳጳሱ ሁለቱም የክብር መዝገብ ላይ ፊርማቸውን ያሳረፉ ሲሆን ሊቀ ጳጳስ ኢሮኒሞስ 2ኛ እንዲህ ሲሉ የክብር መዝገቡ ላይ አስፍረዋል፡- “በዛሬው ቀን፣ ታኅሣሥ 5/2021 ዓ.ም (እ.አ.አ.) የቅዱስ ሳባስ በዓል በምናከብርበት ወቅት እኔና አጃቢዎቼ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከሮም የመጡት ቅዱስ የሆኑት ወንድማችን ፍራንቸስኮስ ወደ ግሪክ ስላደረጉት ጉብኝት ለማመስገን መጥተናል። መልካም  የመልስ ጉዞ እንዲሆን እንመኝሎታለን። ቅዱስ አምላክ እርሶን ይባርክ” የሚል ጽሑፍ በክብር መዘገቡ ላይ ማሳረፋቸው ተገልጿል።

በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡- “ከደስታና ሰላም ጋር የምወደው ወንድሜን ኢሮኒሞስ ዳግማዊ አገኘዋቸው። ስለ ወንድማዊ ቸርነታቸው፣ ስለ ገርነታቸው፣ ለትዕግሥታቸው አመሰግናለሁ። የወንድማማችነት እና የሰላም መንገዳችንን እንድንቀጥል ጌታ ጸጋውን ይስጠን። አብረን እንድንራመድ ስለረዱን ብፁዕ አቡነ ኢሮኒሞስ ዳግማዊ አመሰግናለው። ጌታ ሁለቱን እህታማማቾች የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስተ ቅዱሳን የሆንቸው የእግዚአብሔር እናት እንድትረዳቸው እጸልያለሁ" በማለት ጹሁፋቸውን አስፍረዋል።

በስጦታ ልውውጥ ወቅት ብፁዕነታቸው ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሁለት መጽሐፎችን የሰጡ ሲሆን አንደኛው በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በትንሿ እስያ ግሪኮች ያሳለፉትን አሳዛኝ ታሪክ የሚገልጽ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በግሪክ አብዮት ወቅት ስለሞቱት ሰዎች የሚያወሳ መጽሐፍ እንደ ሆነ ተገልጿል። እንዲሁም በአንድ ካህን ስም ለጳጳሱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሕጻኑ ኢየሱስ ጋር አብረው የሚያሳይ ምስል ያለበት መዳሊያ አበርክተውላቸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በበኩላቸው ለዚህ ጉዞ የተዘጋጀን ሜዳልያ እና በተጨማሪም “Statio Orbis” በሚል አርእስት እ.አ.አ በመጋቢት 27/2020 ዓ.ም የታተመውን መጽሐፍ በስጦታ መልክ ማበርከታቸው ተገልጿል።

05 December 2021, 14:42