ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ወጣቶች በእያንዳንዱ የህይወት ደረጃ ውስጥ ኢየሱስን ማግኘት እፈለጋለሁ ማለት አታቋርጡ አሉ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ አመታዊ በዓል በሕዳር 12/2014 ዓ.ም ተክብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተክብሮ ማለፉ ተገልጿል። ከዚህ በዓል ጋር መሳ ለመሳ በሆነ መልኩ በሀገረ ስብከት ደረጃ የሚከበረው አለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተክብሮ ማለፉም ተገልጿል። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት ወጣቶች በልባቸው ከኢየሱስ ጋር አብረው ማለም እና ወጣቶች በእያንዳንዱ የህይወት ደረጃ ውስጥ ኢየሱስን ማግኘት እፈለጋለሁ ማለት አታቋርጡ ማለታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

ከሰማናቸው የእግዚአብሔር ቃል የተውጣጡ ሁለት ምስሎች ወደ ኢየሱስ የዓለም ንጉሥ እንድንቀርብ ይረዱናል። የመጀመሪያው፣ ከራእይ መጽሐፍ የተወሰደውና በመጀመሪያው ንባብ በነቢዩ ዳንኤል በጣላነት የተመሰለው “ከደመና ጋር ይመጣል” በሚለው ቃል ተገልጸዋል (ራእ. 1፡7፤ ዳን 7፡13)። ማጣቀሻው በታሪክ መጨረሻ ላይ ኢየሱስ ጌታ ሆኖ በክብር በድጋሚ መምጣቱን ያመለክታል። ሁለተኛው ምስል ከቅዱስ ወንጌል የተወሰደ ነው፡- ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት ቆሞ “እኔ ንጉሥ ነኝ” ያለውን (ዮሐ. 18፡37) እንመለከታለን። ውድ ወጣቶች (እ.አ.አ) 2023 ዓ.ም የአለም ወጣቶች ቀን ለማክበር ወደ ሌዝቦን (ፖርቱጋል) ጉዟችንን ለመጀመር ስንዘጋጅ ስለእነዚህ ሁለት የኢየሱስ ምስሎች ቆም ብለን ማሰብ ጥሩ ነው።

እስቲ በመጀመሪያው ምስል ላይ እናሰላስል፡ ከደመና ጋር የሚመጣውን የኢየሱስን ምስል እንመልከት። ምስሉ በጊዜ ፍጻሜ ላይ የክርስቶስን በክብር መምጣትን ያሳያል፣ በሕይወታችን ላይ የመጨረሻው ቃል የእኛ ሳይሆን የኢየሱስ እንደሚሆን እንድንገነዘብ ያደርገናል። እርሱ ነው - ስለዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል - “በደመና ላይ የሚጋልበው” (መዝ 68፡5)፣ ኃይሉ በሰማይ ነው (መዝሙር 68፡ 34)። እርሱ ጌታ ነው፣ ​​ከላይ የወጣች ፀሀይ አትጠልቅም፣ ሌሎች ሁሉ ሲያልፉ የሚፀና፣የእኛ አስተማማኝ እና የዘላለም ተስፋ እርሱ ነው። እርሱ ጌታ ነው። ይህ የተስፋ ትንቢት ሌሊቶቻችንን ያበራል። እግዚአብሔር በእርግጥም እየመጣ መሆኑን ይነግረናል፣ አሁን እና በስራ ላይ እንዳለ፣ ታሪካችንን ወደ ራሱ፣ ወደ በጎነት ሁሉ እየመራ ነው። እኛን ለማረጋጋት “ከደመና ጋር” ይመጣል። “በሕይወታችሁ ላይ ማዕበል ሲነሳ ብቻችሁን አልተዋችሁም። እኔ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። የመጣሁት ብሩህ ሰማይን ለመመለስ ነው" ይለናል።

ነቢዩ ዳንኤል ደግሞ “በሌሊት ራእይ ሲያይ” (ዳን 7፡13) ጌታ ከደመና ጋር ሲመጣ እንዳየ ይነግረናል። የሌሊት ራእዮች፡- እግዚአብሔርም በሌሊት ይመጣል፣ በህይወታችን ላይ ብዙን ጊዜ በሚያንዣብቡ ጥቁር ደመናዎች መካከል እርሱ ይመጣል። ሁላችንም እንደዚህ አይነት ጊዜዎችን እናውቃለን፣ እርሱን ልንገነዘበው፣ ከሌሊቱ ማዶ ማየት፣ በጨለማው ውስጥ ለማየት ዓይኖቻችንን ማንሳት መቻል አለብን።

የተወደዳችሁ ወጣቶች፣ እናንተም “በሌሊት ራእዮችን እንድትመለከቱ” እፈልጋለሁ! ይህ ምን ማለት ነው? በጨለማ ውስጥም ቢሆን ዓይኖችህ ብሩህ ሆነው እንዲቆዩ ማድረግ ማለት ነው። በልባችን ውስጥ ልንሸከም ወይም በዙሪያችን ማየት በምንችለው ጨለማ ውስጥ ብርሃን መፈለግን አታቋርጡ። ዓይናችሁን ከምድር ወደ ሰማይ አንሱ ለመሸሽ ሳይሆን በፍርሃታችን ታስረን የመቆየት ፈተናን ለመቋቋም ቀና ብለን ማየት ይኖርብናል፣ ሁሌም ፍርሃታችንን ሊያባዛ የሚችል አደጋ አለና። ለራሳችን እና ለቅሬታዎቻችን ዝግ እንዳትሆኑ። ዓይንህን አንሳ! ተነሳ! ይህ ጌታ የሚናገረን የማበረታቻ ቃል ነው፣ ዓይኖቻችንን እንድናነሳ፣ እንድንነሳ ግብዣው ነው፣ እናም ለዚህ አመት አብሮን ይጓዝ ዘንድ ከዚህ ቀደም ያስተላለፍኩትን መልእክቴን መድገም እፈልጋለሁ። አንድ አስደሳች ነገር፣ ግን ፈታኝ ስራ ተሰጥቷችዋል። በዙሪያችን ያለው ነገር ሁሉ እየፈራረሰ እያለ ቀጥ ብሎ መቆም፣ በሌሊት ራእዮች ብርሃንን ለማየት የተዘጋጁ መልእክተኞች መሆን፣ በዛሬው ዓለም ብዙ ፍርስራሾች መካከል ግንበኞች መሆን፣ ማለም መቻል ያስፈልጋል። ይህ ወሳኝ ነገር ነው-አንድ ወጣት ህልም ማለም የማይችል ከሆነ ከዘመኑ በፊት በሚያሳዝን ሁኔታ አርጅቷል ማለት ይቻላል። ማለም መቻል ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም ህልም ያላቸው ሰዎች የሚያደርጉት ይህንን ነው ፣ በጨለማ ውስጥ አይቀሩም ፣ ግን ሻማቸውን ያበሩታል ፣ የንጋትን መምጣት የሚያበስር የተስፋ ነበልባል ያነግባሉ። አልም፣ ፍጠን እና በድፍረት የወደፊቱን ተመልከት።

አንድ ነገር ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፣ እኛ ሁላችንም እናንተ ህልም ስታልሙ እጅግ እንደሰታለን። " ግን ይህ እውነት ነው? ወጣቶች ሲያልሙ አንዳንድ ጊዜ ሁካታ ይፈጥራሉ…። ሁከት የሕልምህ ፍሬ ነውና መጮኽ አለባችሁ።ኢየሱስን የሕይወታችሁን ህልም ስታደርጉት እና በደስታ እና ተላላፊ ጉጉት ስትቀበሉት በሌሊት መኖር አትፈልጉም ማለት ነው። ይህ ይጠቅመናል! ህልሞቻችሁን እውን ለማድረግ በድፍረት ስትሰሩ፣ በጨለማ ጊዜም ቢሆን በብርሃን ማመን በምትቀጥሉበት፣ አለማችንን የበለጠ ቆንጆ እና ሰብአዊነት የሰፈነባት ለማድረግ እራሳችሁን በጋለ ስሜት ውስጥ በምታስገቡበት ጊዜያት ሁሉ እናመሰግናለን። የወንድማማችነትን ህልም ለምታሳድጉበት፣ የፈጣሪን ፍጥረት ቁስሎች ለመፈወስ ስትሰሩ፣ የተጎጂዎችን ክብር ለማረጋገጥ ስትታገሉ እና የመተሳሰብና የመጋራትን መንፈስ ለምታሳድጉባቸው ጊዜያት ሁሉ እናመሰግናለን። ከምንም በላይ አመሰግናለው፣ ምክንያቱም አሁን ያለውን ጥቅም ብቻ በሚያስብ፣ ታላላቅ ሀሳቦችን ወደ ማፈን በሚያቀናው አለም፣ በዚህ አለም ውስጥ የማለም አቅም አላጣህችሁምና በርቱ! ህይወቶቻችሁን በጭንቀት ወይም በእንቅልፍ አትኑሩ። ይልቁንስ አልሙ እና ኑሩ። ይህ ለእኛ አዋቂዎች፣ እና ለቤተክርስቲያኗም ይጠቅማል። አዎን፣ እንደ ቤተ ክርስቲያንም ሁልጊዜ ወጣት ለሆነው አምላክ ምስክሮች እንድንሆን ማለም ጥሩ ነው፣ የወጣትነት ጉጉት ያስፈልገናል!

ሌላ ነገር ልንገራችሁ፣ ብዙዎቹ ህልሞቻችሁ ከቅዱስ ወንጌል ጋር አንድ ናቸው። ወንድማማችነት፣ አንድነት፣ ፍትህ፣ ሰላም፡ እነዚህ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ያላማቸው የራሱ ህልሞች ናቸው። ኢየሱስን ለመገናኘት አትፍሩ፣ ህልማችሁን ይወዳል እና እነርሱን እውን ለማድረግ ይረዳችኋል። ካርዲናል ማርቲኒ ቤተክርስቲያን እና ማህበረሰቡ “ለመንፈስ ቅዱስ ድንቆች ሁል ጊዜ ክፍት ሆነው የሚቆዩ ህልም አላሚዎች ያስፈልጋቸዋል” ይሉ ነበር። ለመንፈስ ቅዱስ ድንቆች ክፍት የሚያደርጉን ህልም አላሚዎች መሆን አለባችሁ። ይህ ቆንጆ ነገር ነው! ከእነዚህ ህልም አላሚዎች አንዱ እንድትሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ እና እጸልያለሁ!

አሁን ደግሞ ወደ ሁለተኛው ምስል ደርሰናል፡ ወደ ኢየሱስ፤ ጲላጦስን፡ “እኔ ንጉሥ ነኝ” አለው። ኢየሱስ ባደረገው ቁርጠኝነት፣ ድፍረቱና ከሁሉ የላቀ ነፃነቱ ተደምመናል። ኢየሱስ ተይዞ፣ ወደ ጲላጦስ ተወሰደ፣ ሞት እንዲፈርድበት ስልጣን ያላቸው ሰዎች ጠየቁት። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እራሱን ለመከላከል ሙሉ መብት ነበረው፣ አልፎ ተርፎም ወደ ስምምነት በመምጣት "ማደራጀት" ይችል ነበር። ከዚህ ይልቅ ኢየሱስ ማንነቱን አልደበቀም፣ ዓላማውን አልደበቀም ወይም ጲላጦስ እንኳ የተወለትን ማምለጫ አልተጠቀመም። ከእውነት በመወለድ በድፍረት “እኔ ንጉሥ ነኝ” ሲል መለሰ። ለገዛ ህይወቱ ሀላፊነቱን ወስዷል፣ ተልእኮ አለኝ እና እሱን ወደ ፍፃሜው እሸጋገራለሁ የአባቴን መንግስት ለመመስከር ነው የመጣሁት አለ። “ስለዚህ የተወለድኩት እና ወደ እዚህ ምድር የመጣውት ለእውነት ልመሰክር ነው” (ዮሐ 18፡37) በማለት ይመልሳል። መንግሥቱ ከዓለም መንግሥታት የተለየች እንደ ሆነች በሕይወቱ ሊሰብክ ሁለት ዓይነት ሐሳብ ሳይዝ ያለ ጥርጥር የመጣው ኢየሱስ ነው። እግዚአብሔር ኃይሉን ለመጨመር እና ሌሎችን ለመጨፍለቅ እንደማይነግሥ፣ በጦር ሃይል እንደ ማይነግሥ ያሳያል። የፍቅር መንግሥት የእርሱ ነው “እኔ ንጉሥ ነኝ” ነገር ግን የዚህ የፍቅር መንግሥት፣ ለሌሎች መዳን ሲሉ ሕይወታቸውን ለሚሰጡ ሰዎች መንግሥት “እኔ ንጉሥ ነኝ” ይለናል።

ውድ ወጣቶች የኢየሱስ ነፃነት ወደ ውስጥ ያስገባናል። በውስጣችን እንዲሰማ፣ እንዲሞግተን፣ ከእውነት የተወለደ ድፍረት እንዲያነቃን እንፍቀድ። እስቲ ራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቅ፣ በጲላጦስ ቦታ ራሳችንን እንሳቀምጥና የኢየሱስን አይን እያየየን የምናፍርበት ነገር ምን አለን? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። ከኢየሱስ እውነት ጋር ፊት ለፊት እየተጋፈጠ፣ እውነት የሆነው ኢየሱስ፣ የማታለል ወይም የማጭበርበር፣ እሱን የማስከፋት መንገዶች የትኞቹ ናቸው? እያንዳንዳችን እንደዚህ አይነት መንገዶችን እናገኛለን። አጥበቀን መፈለግ ይኖርብናል። መስቀሉ እንዳይጠፋ ሁላችንም እነዚህ ድብልቆች፣ እነዚህ መስማማቶች "ነገሮችን ማስተካከል" አለብን። ከቅዠታችን ነፃ ለመውጣት እውነት በሆነው በኢየሱስ ፊት መቆም መልካም ነው። ኢየሱስን ማምለክ ጥሩ ነው፣ በውጤቱም፣ ከውስጥ ነፃ መሆን፣ ህይወትን እንዳለች ማየት፣ እና በዚህ ዘመን ፋሽን እና በሚያደናግር ነገር፣ ግን በሞት በሚያሳጣው የፍጆታ ማሳያዎች አለመታለል ያስፈልጋል። ወዳጆች፣ እዚህ የደረስነው በአለም ድምጾች ለመማረክ ሳይሆን ህይወታችንን በእጃችን ለመውሰድ፣ “ከህይወት ንክሻ ወስደን” በሙላት እንድንኖር ነው!

በዚህ መንገድ፣ ከኢየሱስ ነፃነት ጋር፣ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ለመዋኘት የሚያስፈልገንን ድፍረት እናገኛለን። ይህንን አፅንዖት መስጠት እፈልጋለሁ፣ ከእርሱ ጋር መዋኘት፣ ከእርሱ ጋር መጓዝ ድፍረትን ማግኘት ያስፈልጋል። በሌሎች ሰዎች ላይ ለመዋኘት የሚደረገው የዕለት ተዕለት ፈተና አይደለም፣ ልክ እንደ እነዚያ ዘላለማዊ ተጎጂዎች እና የሴራ ጠበብት ሁል ጊዜ ሌሎችን ተወቃሽ ያደርጋሉ። ይልቁንም ጤናማ ያልሆነው የራሳችን ራስ ወዳድነት፣ ዝግ አስተሳሰብ እና ግትርነት፣ ብዙውን ጊዜ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸውን ቡድኖችን ለማትረፍ ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር መተባበር እንወዳለን። ይህ ሳይሆን ኢየሱስን ለመምሰል ከማዕበሉ ጋር መዋኘት ነው። ክፉን እንድንገናኝ የሚያስተምረን በየዋህና በትሕትና በበጎ ኃይል ብቻ ነው። ያለ አቋራጭ፣ ያለ ማጭበርበር፣ ሁለት ዓይነት ሕይወት ባለመኖር። በብዙ ክፉ ነገሮች የተከበበች ዓለማችን፣ እንደ ማዕበል ወደ ኋላና ወደ ፊት የሚራመዱ ሰዎች - ነፋሱ በነፈሰበት፣ የራሳቸው ፍላጎት ወደ ወሰደበት - ወይም ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ የሚወዛወዙ ሰዎች ከዚህ በኋላ አሻሚ ስምምነት አያስፈልጋትም። በጣም ምቹ የሆነው "በአጥር ላይ የተቀመጡ" ናቸው። እንደዚህ ያለ ክርስቲያን ከክርስቲያን የበለጠ “ሚዛናዊ” ይመስላል። ሁልጊዜ የሚዛናዊነት ተግባርን የሚያከናውኑ ሰዎች ህይወታቸውን ላለማበላሸት፣ ህይወትን በቁም ነገር ላለመውሰድ፣ እጃቸውን እንዳይቆሽሹ መንገዶችን ይፈልጋሉ። እባካችሁ እንደዚህ አይነት ወጣቶች መሆንን ፍሩ። ይልቁንስ ነፃ እና ትክክለኛ ሁኑ ፣ የህብረተሰቡ ወሳኝ ህሊና ሁኑ ። ለመተቸት አትፍሩ! የእናንተን ትችት እንፈልጋለን። ብዙዎቻችሁ ለምሳሌ የአካባቢ ብክለት ተችዎች ነበራችሁ። ይህንን እንፈልጋለን! ከመተቸት አትባዝኑ። ለእውነት ፍቅር ይኑርህ፣ ስለዚህ፣ በህልምህ፣ “ህይወቴ በአለም አስተሳሰብ የተማረከ አይደለም፣ እኔ ነፃ ነኝ፣ ምክንያቱም ከኢየሱስ ጋር ለፍትህ፣ ለፍቅር እና ለሰላም ስለነገስኩ!” ማለት ትችላለህ። ውድ ወጣቶች፣ እያንዳንዳችሁ በደስታ “ከኢየሱስ ጋር፣ እኔም ንጉሥ ነኝ” እንድትሉ ተስፋዬና ጸሎቴ ነው። እኔም ነግሼአለሁ፡ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የርኅራኄው እና የምሕረቱ ሕያው ምልክት መሆን ፈልጋለሁ በሉ። እኔ ህልም አላሚ ነኝ፣ በወንጌል ብርሃን ተደንቄ፣ እና በሌሊት ራእዮች በተስፋ እመለከታለሁ። እናም በምወድቅበት ጊዜ፣ መዋጋትን ለመቀጠል እና ተስፋ ለማድረግ፣ ህልም የመቀጠል ድፍረትን በኢየሱስ ውስጥ እንደ አዲስ አገኘሁ። በእያንዳንዱ የህይወት ደረጃ ውስጥ ኢየሱስን ማግኘት እፈለጋለሁ ማለት አታቋርጡ።

21 November 2021, 12:00