ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ዋና ተዋናይ እንዲሆኑ አበረታቱ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በኅዳር 12/2014 ዓ.ም ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ በዓል ተክብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ከዚህ በዓል ጋር በተያያዝ መልኩ በአገረስብከት ደረጃ የዓለም የወጣቶች ቀን ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል። በዚህ አለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እነዚህን በዓላት ምክንያት  በማደረግ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ሰዎች ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ወጣቶች ቤተክርስቲያን በምታከናውናቸው ተግባሮች ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ዋና ተዋኒያን እንዲሆን ማበረታታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ወጣቶች ቤተክርስቲያን እንደ ቤታቸው ሆና እንዲሰማቸው እና ዛሬ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ዋና ተዋናዮች እንዲሆኑ የቤተክርስቲያንን የመኖር ተልእኮዋን በመርዳት እና በህይወታችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ እንዲችሉ ወጣቶችን አበረታተዋል።

እሁድ ኅዳር 12/2014 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዓለም ዙሪያ ላሉ ወጣቶች ክርስቶስ የአለም ንጉሥ በዓልን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ወጣቶች ተስፋ እንዳይቆርጡ፣ ይልቁንስ ተስፋቸውን እንዲያሳድዱ እና ሕልማቸውን እውን ለማደረግ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወጣቶች ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ቤታቸው ሆኖ እንዲሰማቸው እና ዛሬ ዋና ተዋናዮች እንዲሆኑ፣ የምሥራቹን ቃል የመስበክ ተልዕኮ ዋነኛ አካል እንዲሆኑ አበረታተዋል። በዚህ ክርስቶስ የአለም ንጉሥ በዓል ላይ እንዲያስታውሱት በማበረታታት "ልባዊ" ሰላምታቸውን ለሁሉም ወጣቶች አቅርቧል፣ "መንገሥ ማለት ማገልገል ማለት ነው" ያሉ ሲሆን ሁሉም ሰው እነዚህን ቃላት እንዲደግሙ አበረታቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ እንደ ተናገሩት በእለቱ የዓለም የዓሳ አስጋሪዎች ቀን እየተከበረ መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን በተለይም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አልፎ ተርፎም በግዳጅ የጉልበት ሥራ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ ትኩረታቸውን አድርገዋል። ለሁሉም በባህር ላይ በተለያየ መልኩ በመርከቦች እና በጀልባዎች ላይ ለሚሰሩ ሰዎች ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚሰጥ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ኤጀንሲ ስቴላ ማሪስ ላበረከቱት መንፈሳዊ አገልግሎት ክብር ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸው ሲቀጥሉ በዛሬው እለትም የአለም የመንገድ ትራፊክ ተጎጂዎች መታሰቢያ ቀን ሲከበር፣ በመንገድ ላይ በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ እና አደጋውን ለመከላከል ለሚሰሩ ሰዎች ጸሎት እንዲደረግ አሳስበዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦር መሳሪያ ንግዱን የበለጠ ለመቆጣጠር በሚደረጉ ጅምሮች ላይ ማበረታቻ ከሰጡ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

21 November 2021, 12:10