ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ከሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በተመለሱ ጊዜ ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናቸው አቀረቡ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ከሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በተመለሱ ጊዜ ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናቸው አቀረቡ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ከሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በተመለሱ ጊዜ ለቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናቸውን አቀረቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ከመስከረም 2 - 5/2014 ዓ. ም. ድረስ ወደ ሁለቱ የመካከለኛው አውሮፓ አገራት ሃንጋሪ እና ስሎቫኪያ ያደረጉትን 34ኛ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው በሰላም ወደ ሮም በተመለሱ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ላደረገችላቸው ጥበቃ እና ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍሉ አክሎም ቅዱስነታቸው የምስጋና ጸሎታቸውን ካቀረቡ በኋላ በመንበረ ታቦት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው በቫቲካን ውስጥ ወደሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው መመለሳቸውን አስታውቋል።    

በ “ሳንታ ማርያ ማጆሬ ባዚሊካ” ውስጥ የሚገኝ ጥንታዊው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል፣ የሮም ከተማ ሕዝብ በሽታ ተይዞ በሚሰቃይበት ወቅት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘንድ ባቀረበው ልመና የእርሷን እርዳታ ያገኘበት እንደሆነ የሚታመን ሲሆን፣ የእመቤታችን ቅድስት ማርያም ቅዱስ ምስሉ በባዚሊካው ውስጥ በክብር እንዲቀመጥ፣ ወደ 590 ዓ. ም. አካባቢ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ግሬጎሪ ታላቁ ማዘዛቸው ይታወሳል።

16 September 2021, 16:50