ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሰዎች የኮቪድ -19 ክትባት እንዲወስዱ ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የፍቅር ድርጊት” ብለው የሰየሙትን ሰዎች ውጤታማነታቸው የተረጋገጠ የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዲከተቡ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሰዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመዋጋት ያስችል ዘንድ ለማበረታታት በሰሜን እና በደቡብ አሜሪካ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት እያቀረቡ የሚገኘውን ጥሪ ቅዱስነታቸውም ተቀላቅለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ረቡዕ ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በማምረትላይ የሚገኙትን የተመራማሪዎችን እና የሳይንስ ባለሙያዎችን ሥራ አድንቀዋል።

ረቡዕ በተለቀቀው ቪዲዮ ላይ “ለአምላክ ጸጋ እና ለብዙዎች ምስጋና ይግባው እኛ አሁን ከክቮድ -19 ቫይረስ ወረርሽኝ የሚታደገን ክትባቶች አሉን” ብለዋል።

አክለውም ክትባቶች “ወረርሽኙን ለማስቆም ለሚደርገው ጥረት ተስፋ እንድናደርግ ይረዱናል፣ ነገር ግን ይህ እውን የሚሆነው ሁላችንም ከተባበርን ብቻ ነው” ብለዋል።

ክትባት የፍቅር ተግባር ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመቀጠል “በሚመለከታቸው ባለሥልጣናት የተፈቀደ” ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዳውን ክታባት መቀበል በራሱ “የፍቅር ድርጊት” ነው ብለዋል።

ሌሎች ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ መርዳት እንዲሁ የፍቅር ተግባር ነው ያሉት ቅዱስነታቸው “ለራስ ፍቅር ፣ ለቤተሰቦቻችን እና ለጓደኞቻችን ፍቅር እና ለሁሉም ህዝቦች ያለንን ፍቅር የምንገልጽበት ነው። ፍቅር ማህበራዊ እና ፖለቲካዊም እንድምታ አለው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፍቅር የሚገነባው “ማህበረሰቦችን ለመለወጥ እና ለማሻሻል በሚችሉ አነስተኛ እና ግለሰባዊ ምልክቶችን ጭምር በመጠቀም” ነው ያሉ ሲሆን “ክትባት መውሰድ እርስ በእርስ ፣ በተለይም በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ለመንከባከብ ቀላል የሆነ መንገድ፣ ሆኖም ጥልቅ የሆነ ምልክት ነው” ብለዋል።

ከዚያ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አክለው እንደ ገለጹት ከሆነ “እያንዳንዳችን የየራሳችንን ትንሽ የፍቅር ምልክት ማድረግ እንድንችል” ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ይኖርብናል ያሉ ሲሆን “ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን ፍቅር ሁል ጊዜ ታላቅ ነው” ብለዋል፣ የተሻለ የወደፊት ጊዜን ለመገንባት ትንንሽ የፍቅር መገለጫ የሆኑ ምልክቶች ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

'የእምነት ጥንካሬ'

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ላይ በመላ አሜሪካ የሚገኙ በርካታ ካርዲናሎች እና ሊቀ ጳጳሳት እያቀረቡ የሚገኘውን ድምጽ የተካተተበት ሲሆን የሰሜን አሜሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት እና የሎስ አንጀለስ ሊቀ ጳጳስ ጆሴ ጎሜዝ ወረርሽኙ በዓለም ዙሪያ ስላስከሰተው ሥቃይና ሞት ማዘናቸውን መግለጻቸው ተመላክቷል።

ሁሉም “ክትባት ማግኘት እንድችል” ክትባት ለሁሉም ተደራሽ መሆኑን በማረጋገጥ እግዚአብሔር በእምነት ጥንካሬ የመጋፈጥን ጸጋ እንዲሰጠን መጸለይ ይኖርብናል” በማለት በመልእክታቸው የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የሜክሲኮው ካርዲናል ካርሎስ አጉያር ሬትስ በበኩላቸው ደግሞ የኮቪድ -19 ክትባቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው ከሁሉም የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ጋር አገናኝቷል፣ ካርዲናሉ አክለውም “ከሰሜን እስከ ደቡብ አሜሪካ ለሁሉም ሰዎች ክትባቱ ተደራሽ ይሆን ዘንድ የሚደርገውን ጥረት እንደግፋለን” ብለዋል።

አስተማማኝ ፣ ውጤታማ ክትባቶች

የሆንዱራስ ካርዲናል ሮድሪጌዝ ማራዲያጋ ዓለም ከኮሮና ቫይረስ ብዙ መማር አለባት ያሉ ሲሆን “ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነው - ፈቃድ ያገኙ ክትባቶች ውጤታማ ናቸው ፣ እናም እዚህ ሰዎችን ለመታደግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው” ብለዋል። እነሱ የግል እና ሁለንተናዊ የፈውስ ጎዳና ላይ ለመራመድ ቁልፍ ሚና አላቸው ብለዋል።

ብራዚላዊው ካርዲናል ክላውዲዮ ሁምስ “ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ” የኮቪድ 19 ክትባቶችን በማዘጋጀት ላይ የተሰማሩትን የጤና ባለሙያዎች “የጀግንነት ጥረቶች” አመስግነዋል። በተጨማሪም “መከተብ የፍቅር ድርጊት ነው” የሚለውን የጳጳሱን ማረጋገጫ ደግሟል።

የሳልቫዶር ካርዲናል ግሪጎሪዮ ሮዛ ቻቬዝ በበኩላቸው ክትባት በጣም ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም “ክትባት ለመውሰድ ያለን ምርጫ በሌሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል” ብለዋል፣ እሱ የሞራል ኃላፊነት ነው ብለዋል።

የመላው አሜሪካ አንድነት

የፔሩ ሊቀ ጳጳስ ሚጌል ካብሬጆስ በቪዲዮው ውስጥ የተካተቱትን ምስክርነቶች ከግምት ባስገባ መልኩ ሕዝቡ አንድ ይሆን ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን በተመለከተ ሲናገሩ “እኛ አንድ ነን - ሰሜን ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ አሜሪካ እና ካሪቢያን - ክትባትን ለሁሉም ለማስተዋወቅ እና ተደራሽነቱን ለመደገፍ” ሁሉም ሰው “እንደ ታላቁ ሰብአዊ ቤተሰብ አባላት ፣ የእኛን ጤና በመፈለግ እና በመጠበቅ በኃላፊነት እንዲሠራ” ማበረታታት ሁለንተናዊ የሆነ የጤና አጠባበቅ እንዲረጋገጥ እና እንዲኖር ያደርጋል ማለታቸው ተገልጿል።

18 August 2021, 11:01