ፈልግ

ሳይንስ ለሰላም ግንባታ ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽዖን የሚያበረክት መሆኑ ሳይንስ ለሰላም ግንባታ ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽዖን የሚያበረክት መሆኑ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ሳይንስ ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽዖን የሚያደርግ መሆኑን ገለጹ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በጣሊያን አብሩዞ ሀገረ ስብከት ውስጥ በመካሄድ ላይ ላለው የሳይንስ ሊቃውንት ጉባኤው መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው ሳይንስ ለሰላም ግንባታ ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽዖን የሚያበረክት መሆኑን ገልጸው፣ የሊቃውንቱ የተግባር ድርሻ በዓለማችን ሰላምን የሚገነቡ አዲስ ትውልድ ማፍራት መሆኑን ካስረዱ በኋላ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በሳይንስ እና ኅብረተሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት በሚገባ ለማወቅ ዕድል ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከሳይንስ ሊቃውንት ጋር መገናኘት መቻል ለሰብዓዊ ፍጥረት ተስፋን የሚሰጥ ስጦታ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ ዛሬ የደረስንበት ጊዜ ማኅበረሰባችንን ያጋጠሙ ችግሮችን ለማቃለል የምርምር ሥራዎች ከምን ጊዜም በበለጠ እንዲካሄድ የሚጠቅ መሆኑን አስረድተዋል። ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው፣ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ የሚገኘውን የመመራመር እና የማወቅ ፍላጎት ለማሳደግ ሳይንሳዊ ምርምሮች በጋራ አገልግሎታቸውን ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በእምነት እና በሳይንስ መካከል ቅራኔ የለም

“ሳይንስ ለሰላም” በሚል ርዕሥ በጣሊያን ቴራሞ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚገኝ የኑክሌር ፊዚክስ ብሔራዊ የምርምር ማዕከል የተረገው የሳይንስ ሊቃውንት ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ጥረት መዘጋጀቱ ያስደሰታቸው መሆኑን ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ገልጸው፣ በእምነት እና በሳይንስ መካከል ቅራኔ ሊኖር አይገባም ብለዋል።

በጤና እና በቤተሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት እንደገና ማጤን

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሳይንስ ሊቃውንት በላኩት መልዕክት የሳይንስ እድገት የሕይወትን ፣ የኅብረተሰብን እና የዓለምን አንድ ገጽታ ለመገንዘብ ብቸኛው አማራጭ ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት ገልጸው፣ ወረርሽኙ ምክንያት በሳይንስ እና በኅብረተሰብ መካከል አዲስ ግንኙነት መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ማንኛውም ሳይንሳዊ ዕውቀት እራስን በመቻል ብቻውን መራመድ የለበትም ብለው ታሪካዊ እውነታው ሳይንሳዊ ብዝሃነት ሌሎችን በዕውቀት ማገልገል ያስፈልጋል ብለዋል። ይህም በልዩነታቸው ውስጥ የእያንዳንዱን ወንድና ሴት ክብር እና እድገት በማጎልበት ህብረተሰቡን ለመገንባት የሚያስችል አዲስ ባህል እንዲዳብር አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።

አዲስ ትውልድን መፍጠር

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በሳይንሳዊ ምርምር ሥራ ላይ የተካፈሉትን በሙሉ አመስግነው፣ በውይይቱ ወቅት የተሸለሙ ጣሊያናዊ ፕሮፌሰር ክቡር አቶ አንቶኒዮ ዚኪኪን አስታውሰዋል። ለተመራማሪው ባቀረቡት መልዕክት ለሳይንስ ልማት እና ለአዳዲስ ትውልዶች ምስረታ የሚያደርጉትን ጥረት መቀጠል እንዳለባቸው ጠይቀው፣ የምርምር ሥራቸው ለሳይንስ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ ማህበራዊ ትስስር መፍጠር

ሳይንስ ሰላምን ለመገንባት የሚያስችል ትልቅ ሀብት መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው አዳዲስ ማህበራዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ሳይንሳዊ ምርምር ማድረግ ሁሉንም ማህበረሰብ ለማቀራረብ፣ ከአከባቢ እስከ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትን በመፍጠር ማንኛውንም ግጭት ማሸነፍ የሚቻል መሆኑን ገልጸዋል።

03 July 2021, 16:45