ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለሊባኖስ ባቀረቡት ጸሎት-በሰላም ህልም ውስጥ ሥሮቻችንን እንዘራጋ ማለታቸው ተገለጸ!

በሰኔ 24/2013 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሊባኖስ ጸሎት የተደረገበት እለት እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ምክንያት የሊባኖስ የክርስቲያን ማሕበርሰብ መሪዎች በቫቲካን ከርዕሰ ሊቀነ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ ጋር ተገናኝተው ሰለ ወቅታዊው የሊባኖስ ሁኔታ መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ለሊባኖስ ሰላም እና መረጋጋት ጸሎት ማደረጋቸው ተወስቷል። ሊባኖስ በተከሰተው የፖሌቲካ ቀውስ እና ግጭት የተነሳ ከፈተኛ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ አገር እንደ ሆነች የሚታወቅ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተፈጠረው ግጭት ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ጸሎት በማድረግ የሊባኖስ ህዝብ ወደ ነበረበት ሥር መሰረቱ እንዲመለስ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አክለው ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ለሊባኖስ የተደርገውን የጸሎት ቀን ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግር ሲያደርጉ በዚህ ቀን “በቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች ጸሎት የተደገፈው ይህንን የጨለማ ሁኔታ በተጋፈጥን ጊዜ እኛ የቤተክርስቲያን አባቶች በጋራ በመሆን በእግዚአብሔር ብርሃን መመራት ” ይኖርብናል ማለታቸው ተገልጿል። ከዚህ አንጻር ሲታይ ሰለሁኔታው ግልፅነት ማነስ አይታያል ያሉት ሲሆን የተሰሩ ብዙ ስህተቶች እንዳሉም ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል። ለዚህ እኛም ለሰራነው ስህተት በሙሉ ይቅርታ መጠይቅ ይኖርባንል፣ በተጸጸተ ልብ ጌታ ሆይ ማረን በማለት ልንጸልይ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ወደ 10 የሚሆኑ የተለያዩ የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ አመራሮች እና የሊባኖስ ማህበረሰቦች ከልዑካኖቻቸው ጋር በቫቲካን ተገኝተው በችግር ላይ ስለሚገኘው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር ወቅታዊ ሁኔታ እና ስለወደፊቱ ሁኔታ ተወያይተው ጸሎት ማደረጋቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቀጥለው ከጢሮስ እና ከሲዶን አካባቢ የመጣችው አንዲት ሴት የተናገረችሁን በመጥቀስ  በዚህ ተመሳሳይ ልመና ኢየሱስን በጽኑ ስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች “ጌታ ሆይ ፣ እርዳቸው” ብላ መለመኗን አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዛሬ የዚህች ሴት ልመና የመላው ህዝብ ፣ ተስፋ የቆረጠ እና የደከመው የሊባኖስ ህዝብ ልመና ሆኖ እንደ ቀጠለ የገለጹ ሲሆን ይህ ሕዝብ እርግጠኛ የሆነ “ተስፋ እና ሰላም ይፈልጋል” ብሏል። የሊባኖስ ህዝብ በዚህ ልመና ላይ እኛ የሰው ልጆች በምድር ላይ ለመገንባት በጣም ያዳገተንን እና አስቸጋሪ የሆነብንን የእግዚአብሔር መንግሥት ለመገንባት ከወትሮ በበለጠ ሁኔታ ልመናችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ያሉ ሲሆን ይህንን ልመና ያለ መሰልቸት እና መታከት አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።

በዕለቱ የተነበቡትን ቅዱሳን መጻሕፍትን በመጥቀስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አክለው እንደ ገለጹት “ጌታ ለሰላም እንጂ ለጣላቻ ቦታ የለውም” በሚለው አጭር ሐረግ ላይ አተኩረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእነዚህ አስጨናቂ ጊዜያት “ሊባኖስ ስለሟ የተረጋገጠ ይሆን ዘንድ የሰላም እቅድ ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፣ ይህንንም በሙሉ ኃይላችን ማረጋገጥ እንፈልጋለን” ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለው እንደ ገለጹት ሊባኖስ “የመቻቻል እና የብዙሃነት ምድር ፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች እና እምነቶች የሚገኙበት የወንድማማችነት መናኸሪያ ፣ የተለያዩ ማህበረሰቦች አብረው የሚኖሩበት ፣ የጋራ ጥቅሞችን ከግለሰባዊነት ያስቀደመ” መሆን እንደ ሚኖርበት ገልጸዋል። በመቀጠልም “በሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ በቆራጥነት ለግል ጥቅማቸው ሳይሆን ለእውነተኛ ሰላም መሥራት” ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት እንዳለባቸው አጥብቀው ተናግረዋል።

ለደካሞች እና ለኃያላን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሊባኖስ ህዝብ ባደረጉት ንግግር “በብቃታችሁ እና በታታሪነታችሁ እራሳችሁን ከተቀረው አለም የተሻለ ብቃት እንዳላችሁ አሳይታችኳል” ያሉ ሲሆን በልዩነት ውስጥ መሰናክሎችን ሳይሆን ዕድሎችን የተመለከቱ እና የተለመዱ መሠረቶችን ሊገነቡ በሚችሉ “ከእናተ በፊት” የነበሩትን የአባቶቻችሁን ፈለግ መከተል ይኖርባችኋል ብለዋል። በሰላም ህልማችሁ ውስጥ ሥር መሰረታችሁን መዘርጋት እንዳትዘነጉ ያሉት ቅዱስነታቸው የሀገሪቷን የፖሌቲካ መሪዎች በተመለከተ ባደረጉት ንግግር “በተሰጣችሁ ኃላፊነት መሰረት እና የተጣለባችሁን ግዴታ በማሰብ ሰላም ይረጋገጥ ዘንድ አሁን ላለው ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄዎችን እንድታስገኙ” እጠይቃለሁ ብለዋል።

እኛ ክርስቲያኖች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል እንደ ክርስትያኖች ምኞታችን “የወደፊቱን አብሮ ለመገንባት ቁርጠኝነታችንን ማደስ ነው” ብለዋል። መፃኢ ዕድላችን ሰላማዊ የሚሆነው በጋራ ከተጋራነው ብቻ ነው ሲሉ አብራርተዋል። የሰዎች ግንኙነቶች በፓርቲዎች ፍላጎቶች ፣ መብቶች እና ጥቅሞች ላይ ሊመረኮዙ አይችሉም” ያሉ ሲሆን “እኛ ክርስቲያኖች የተጠራነው የሰላም ዘሮችን ለመዝራት እና የወንድማማችነት መንፈስ ገንቢዎች እንድንሆን ነው ፣ ያለፉትን ቂሞች እና ጸጸቶችን በመርሳት፣ የአሁኑን ሀላፊነቶቻችን በመወጣት፣ ይልቁንም ለወደፊቱ ተስፋ በማድረግ እንድንመለከት” እኛ ክርስቲያኖች ተጠርተናል ያሉ ሲሆን እኛ እግዚአብሔር አንድ መንገድ አሳይቶናል ብለን እናምናለን ይህም መንገድ የሰላም መንገድ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለቅኔውን ጂብራን በመጥቀስ እንደ ተናገሩት እኛ “ሌሊቱን የግዴታ ካላለፍን በቀር ወደ ንጋት መምጣት የሚያስችል ሌላ መንገድ እንደሌለ እንገንዘብ። እናም በችግር ምሽት ሁላችንም አንድ ሆነን መቀጠል ያስፈልገናል” ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸው ሲቀጥሉ “በአንድነት ፣ በሐቀኛ ውይይት እና በንጹህ ዓላማዎች “ጨለማ ባለበት ቦታ ብርሃን ማምጣት እንችላለን” በማለት የተናገሩ ሲሆን እያንዳንዱን ጥረት እና ቁርጠኝነት የሰላም ልዑል ለሆነው ለክርስቶስ በአደራ እንስጥ ፣ ስለሆነም “የግጭቶች ምሽት በአዲስ የተስፋ ጎህ እንዲተካ፣ ጠብ እንዲቆም፣ አለመግባባቶች በሰላም እንዲፈቱ እና በሊባኖስ የሰላም ብራሃን እንዲበራ” እያደረግነው የምንገኘውን ጸሎት አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

02 July 2021, 11:57