ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጄሜሊ የሕፃናት የካንሰር ሕክምና መስጫ መዕከል ጎበኙ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጄሜሊ የሕፃናት የካንሰር ሕክምና መስጫ መዕከል ጎበኙ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጄሜሊ የሕፃናት የካንሰር ሕክምና መስጫ መዕከል ጎበኙ!

በሐምሌ 06/2013 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እርሳቸው በአሁኑ ወቅት የሕክምና አገልግሎት እያገኙበት በሚገኘው በጄሜሊ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘውን የካንሰር በሽታ የሚሰቃዩ ሕጻናት የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ማዕከል መጎብኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በማዕከሉ የሕክምና አገልግሎት እያገኙ የሚገኙትን ሕጻናት እና ቤተሰቦቻቸውን መጎብኘታቸው እና ማጽናናታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዚህ የሕጻናት የካንሰር ሕክምና ተቋም ውስጥ በርካታ ሕጻናት የሕክምና አገልግሎት እያገኙ እንደ ሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ እነዚህን ሕጽናት የሚንከባከቡ ቤተሰቦቻቸው በልጆቻቸው ስቃይ ምክንያት ለከፍተኛ ስቃይ እና ጭንቀት በመዳረጋቸው የተነሳ ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያደረጉት ጉብኝት ለእነዚህ ሕጻናት ቤተሰብ መጽናናት እና ተስፋቸው በድጋሚ እንዲያለመልም ያደረገ ክስተት እነደ ነበረ ተገለጿል።

14 July 2021, 09:21