ፈልግ

መጠልያ የሌለው አንድ ድሃ ሰው መጠልያ የሌለው አንድ ድሃ ሰው 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በድሆች እና በተገለሉ ሰዎች ውስጥ ያለውን ክርስቶስን ለሚያገለግሉ ምስጋና አቅረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በአርጀንቲና የማር ዴል ፕላታ ሀገረ ስብከት ሁለት በጎ አድራጎት ድርጅቶች ችግረኞችን እና ድሆችን በመፈለግ መጽናኛ እና እንክብካቤን እንዲያገኙ እያደረጉ የሚገኙትን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ማመስገናቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአገራቸው አርጀንቲና ውስጥ ሁለት የበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚሰጡ በጎ ፈቃደኞች በጎዳና ላይ ለሚሰቃዩ እና እጅግ በጣም ድሃ የሆኑ ሰዎችን ፍለጋ ለሚወጡ እና ምቾት እና እንክብካቤ ለማምጣት ፈቃደኛ ለሆኑት ሰዎች ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። “የበጎ አድራጎት ምሽት እና የናዝሬት ቤት የተሰኙትን ሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ አገልጋዮች ቤት ለሌላቸው ሰዎች ትኩረት በመስጠታቸው በልዩ ሁኔታ ሰላምታዬን አቅርብላቸዋለሁኝ” ያሉ ሲሆን እያከናወኑ ለሚገኙት መልካም ነገር ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁኝ በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባቀረቡት አጭር የቪዲዮ መልእክት ተናግረዋል።

በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ባለው በአርጀንቲና ከሰኔ እስከ ነሐሴ ያሉት የክረምት ወራት ናቸው። ከአርጀንቲና ዋና ከተማ ከቦነስ አይረስ በስተደቡብ 415 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በማር ዴል ፕላታ ውስጥ የሊቀ ጳጳሱ የትውልድ ከተማ የቀን ሙቀt መለስተኛ ቢሆኑም ሌሊት ግን እጅግ በጣም ቀዝቃዛ ነው።

ኖቼ ዴ ካሪዳድ (የምሽት በጎ አድራጎት)

የምሽት በጎ አድርጎት የተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት በአትላንቲክ ዳርቻ በሚገኘው ማር ዴል ፕላታ በአርጀንቲና ሀገረ ስብከት ውስጥ ከተለያዩ አጥቢያዎች የተውጣጡ የተወሰኑ ሰዎች የሚሰጡት የበጎ አድራጎት አገልግሎት ምስጫ ማሕበር ነው። በጎዳናዎች ላይ ለሚኖሩ ሰዎች የምግብ አቅርቦት የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም አስቸጋሪ ሁኔታ ቢያጋጥማቸውም እንደተወደዱ እንዲሰማቸው የፍቅር እና የተስፋ መልእክትም ለችግረኞች ያደርሳሉ። የበጎ ፈቃድ አግልግሎት ሰጪ የሆኑ ሰዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን ምግብ ለማጓጓዝ እና እንዲሁም አልባሳትን፣ ብርድ ልብስ የመሳሰሉ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የራሳቸውን መኪኖች ይጠቀማሉ።

ሆጋር ደ ናዝሬት (የናዝሬት ቤት)

የናዝሬት ቤት የተሰኘው እና ማር ዴል ፕላታ (የምሽት የበጎ አድርጎት ድርጅት) ስር የሚሠራው የናዝሬት ቤት ቤት ለሌላቸው ሰዎች የሌሊት መጠለያ አገልግሎት በመስጠት በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ከማር ዴል ፕላታ በስተምዕራብ 51 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በባልካርሴ የሚገኘው የናዝሬት ማዕከል ፣ መክሰስ ፣ እራት እና ቁርስ ፣ ሙቅ ሻወር ፣ የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች እና ንፁህ ልብሶችን እና ከሁሉም በላይ ንጹህ እና የተመቻቸ የመኝታ ቤቶችን ለድሆች አገልግሎት የሚያቀርብ ሲሆን ወደ 50 የሚሆኑ ወንዶችና 10 ሴቶች ይህንን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የበጎ ፈቃደኞች በዓመት ውስጥ እያንዳንዱን ቀን ለመርዳት ይመጣሉ። የናዝሬት ቤት ምግብና መጠለያ ከመስጠት በተጨማሪ ለድሆች የግል ሰነዶችን የማግኘት መብቶችን ለምሳሌ የጡረታ አበል ፣ የሥራ ማሠልጠኛ ትምህርቶችን ማመቻቸት እና የትምህርት (CV) ሰነዶችን ማዘጋጀት እና መልሶ ማቋቋም ቤተሰቦቻቸው እና የጤና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ አንድ ባለሙያ ማህበራዊ ሰራተኛ እና የስነ-ልቦና ባለሙያ ለማዕከሉ ነፃ አገልግሎት ይሰጣሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ በቪዲዮ መልእክታቸው የማር ዴል ፕላታ ጳጳስ ገብርኤል አንቶኒዮ መስትሬ “በማር ዴል ፕላታ ጠረፍ አስቸጋሪ እና እርጥብ በሆነ የክረምት ወቅት ለሁሉም ሰው የሚሆን ተጨማሪ ቦታ እንዲኖራቸው 2 ሆቴሎችን ተከራይተዋል” በማለት መናገራቸው ተገልጿል።

ድሆች የቅዱስ ወንጌል ማዕከል ናቸው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሀገረ ስብከቱን ካቶሊኮች ለበጎ አድራጎት ተግባራት ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ያበረታቱ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለውም “በጣም ድሃ እና በጣም የተገለሉ ወንድሞች እና እህቶች ፊት ክርስቶስን ለመገናኘት እየጣሩ የሚገኙትን ምእመናን ፣ ቀሳውስት፣ የቤተክርስቲያኗ በጎ አድራጊዎች እና ሁሉም ዘርፎች ምስጋናዬ ይድረሳቸው፣ ክርስቶስ እዚያ አለ፣ ድሆች የቅዱስ ወንጌል ማዕከል ናቸው” በማለት አፅንዖት በመስጠት ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ አመሰኛለሁኝ ብለዋል።

25 June 2021, 11:49