ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ኢየሱስ ስለ እኛ መጸለይ ፈጽሞ እንደ ማያቆ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት ከቫቲካን ሆነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በግንቦት 25/2013 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም በጸሎት ዙሪያ ላይ ጀምረው ከነበረው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “ኢየሱስ ስለ እኛ መጸለይ ፈጽሞ እንደ ማያቆ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል” ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን። 

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በኢየሱስ እና በደቀ መዛሙርቱ መካከል ባለው ግንኙነት ውስጥ ፀሎት እንዴት መሠረታዊ የሆነ ነገር እንደነበረ ቅዱስ ወንጌል ያሳየናል። ይህ ማን ሐዋርያ መሆን እናዳለበት በተደርገው ምርጫ ውስጥ አስቀድሞ ይታያል። ቅዱስ ሉቃስ ምርጫቸውን በትክክለኛው የጸሎት ሁኔታ ውስጥ ያስቀምጣቸዋል እንደዚህም ይላል “ከእነዚያም ቀናት በአንዱ ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ። ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ ከእነርሱ ዐሥራ ሁለቱን መረጠ፤ እነዚህንም ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው”(ሉቃስ 6፡ 12-13) ። በዚህ ምርጫ ውስጥ ከጸሎት ፣ ከአብ ጋር ከመነጋገር ውጭ መስፈርት ያለ አይመስልም። እነዚያ ሰዎች ምን ዓይነት ጠባይ ማሳየት እንዳለባቸው በተመለከተ በተደረገው ግምገማ ላይ ምርጫው የተሻለው እንዳልሆነ የሚያሳይ ሲሆን ነገር ግን በትክክል ይሆነው ይህ ነው ፣ በተለይም የወደፊቱ ከሃዲ የሆነው ይሁዳ መገኘቱ እነዚያ ስሞች በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ እንደተጻፉ ያሳያል።

በጓደኞቻችን ስም የሚደረግ ጸሎት በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ያለማቋረጥ ይገለጣል። ሐዋርያቱ አንዳንድ ጊዜ ለእሱ የስጋት መንስኤ ይሆናሉ ፣ ነገር ግን ኢየሱስ ፣ ከአብ እንደተቀበላቸው የሚያውቅ በመሆኑ የተነሳ ስለሆነም በወደቁበት ጊዜም እንኳ በስህተቶቻቸው ውስጥ እንኳን በልቡ ውስጥ ያስቀምጣቸዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ኢየሱስ ደቀመዝሙሩ እስኪለወጥ በትዕግስት ለመጠበቅ ሁል ጊዜ ፈቃደኛ እና አስተማሪም ወዳጅም ሆኖ እናገኘዋለን። የዚህ በተዕግስት የመጠበቅ ሂደት ውስጥ ያለው ከፍተኛው ነጥብ ኢየሱስ በጴጥሮስ ዙሪያ ላይ የሸመነው የፍቅር “ድር” ተጠቃሽ ነው። በመጨረሻው እራት ላይ ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ስምዖን፣ ስምዖን ሆይ፤ እነሆ፣ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ጸለይሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።” (ሉቃስ 22፡31-32)። በዚያ ወቅት ፣ በድካም ጊዜ ፣ ​​የኢየሱስ ፍቅር እንደማያቆም ፣ ይልቁንም የበለጠ እየጠነከረ እንደሚሄድ ማወቅ በጣም የሚያስደንቅ ነው እናም እኛ በጸሎቱ መሃል ላይ ነን!

የኢየሱስ ጸሎት በደቀ መዛሙርቱ እምነት ማረጋገጫ በሆነው በጉዞው ውስጥ በጣም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ውስጥ በሰዓቱ ይመለሳል። ወንጌላዊውን ሉቃስን እንደገና እናዳምጥ “ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ እኔን ማን ነው ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞ ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቶአል ይላሉ” አሉት። እርሱም፣ “እናንተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም፣ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ ነህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው”(ሉቃስ 9፡ 18-21)። የኢየሱስ ተልእኮ ታላቅ የማዞሪያ ነጥቦች ሁል ጊዜ በጠንካራ ፣በተራዘመ ጸሎት ይታጀባል። ይህ የእምነት ፈተና ግብ ይመስላል ፣ ነገር ግን ይልቁኑ ለደቀመዛሙርቱ የታደሰ መነሻ ነው ፣ ምክንያቱም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ በተልእኮው ውስጥ አዲስ ቃና እንደያዘ ፣ ስለ ስቃዩ ፣ ስለ ሞቱ እና ስለትንሳኤው በግልፅ ከእነሱ ጋር እንደሚናገር እናያለን።

በዚህ ተስፋ ፣ በደቀ መዛሙርትም ሕይወት ሆነ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ባነበብነው መሰረት በደቀመዛሙርቱ ሕይወት ውስጥ ጸሎት ብቸኛው የብርሃን እና የኃይል ምንጭ እንደ ሆነ እንመለከታለን። መንገዱ ወደ ላይ አቀበት በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ በርትቶ መጸለይ አስፈላጊ ነው።

እናም በእውነቱ በኢየሩሳሌም ምን እንደሚያጋጥመው ለደቀ መዛሙርቱ ካወጀ በኋላ ነበር በታቦር ተራራ ላይ መልኩ የተለወጠበት ሁኔታ የተፈጠረው። “ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ሊጸልይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ። በመጸለይ ላይ እንዳለም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ ነጭ ሆነ። እነሆ፤ ሁለት ሰዎች፣ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር” (ሉቃስ 9፡28-31። ስለሆነም ይህ የተጠበቀው የኢየሱስ ክብር መገለጫ በጸሎት የተከናወነ ሲሆን ወልድ ግን ከአብ ጋር ህብረት ውስጥ በመግባት እና የእርሱን የፍቃድ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለደኅንነታችን እቅድ ሲፈቅድ ነበር። ከዚያም በዚህ ጸሎት ውስጥ ለተሳተፉት ሦስቱ ደቀ መዛሙርት “ይህ እኔ የመረጥኩት ልጄ ነው፣ እርሱን ስሙት” የሚል ግልጽ የሆነ ድምጽ የተሰማው (ሉቃስ 9፡35)።

ከዚህ ፈጣን ጉዞ በወንጌል በኩል ፣ ኢየሱስ እርሱ በጸለየበት መልኩ እንድንጸልይ ብቻ እንደማይፈልግ እንገነዘባለን ፣ ነገር ግን በጸሎት የምናደርጋቸው ሙከራዎች ሙሉ በሙሉ ከንቱ እና ውጤታማ ባይሆኑም እንኳን ሁል ጊዜ በጸሎቱ ላይ መተማመን እንዳለብን ያረጋግጥልናል። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ይህንን በተመለከተ እንዲህ ይላል: - “የኢየሱስ ጸሎት የክርስቲያንን ተሎት ውጤታማ ያደርገዋል። አርአያውም እርሱ ነው፣ እርሱ በእኛ ውስጥ ከእኛም ጋር ሆኖ ይጸልያል”(የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቁ. 2740)። እናም ጥቂት ሄድ ብሎ ደግሞ እንዲህ ይላል “ኢየሱስ በእኛ ቦታ ሆኖ በእኛ ስም ስለእኛ ይጸልያል። ልመናዎቻችን ሁሉ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተጠቃለው የቀረቡት ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ በጮኸበት ጊዜ እና በትንሳኤው በአብ ተሰምቷል። ለዚህም ነው ከአብ ጋር ስለ እኛ መማለዱን የማያቋርጥ” (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቁ. 2741)።

ጸሎቶቻችን የመንተባተብ ብቻ ቢሆኑም እንኳ ፣ ጽኑ ባልሆነ እምነት ላይ ያልተመሰረተ ቢሆንም እንኳን፣ በእርሱ ከመታመን ፈጽሞ ማቆም የለብንም። በኢየሱስ ጸሎት የተደገፈ ፣ ዓይናፋር ጸሎታችን በንስር ክንፎች ላይ ሆነው ወደ ሰማይ ከፍ ማለታቸውን ይቀጥላሉ።

02 June 2021, 10:59