ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የወንጀል ቅጣቶችን አሻሻሉ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የወንጀል ቅጣቶችን አሻሻሉ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የወንጀል ቅጣቶችን አሻሻሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ በላቲን ቋንቋ “Pascite Gregem Dei” (መንጋውን ይመግቡ) በሚል አርዕስት በቅርቡ ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ሕግጋት በቤተክርስቲያን ሕገ ቀኖና መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን ስድስተኛውን ሕግ እንዲሻሻል ያደረጉ ሲሆን ከእርሳቸው በፊት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በነዴክቶስ 16 ኛ ተጀምሮ የነበረውን ማሻሻያ በመቀጠል እና ለተጨማሪ የወንጀል ጥፋቶች የቅጣት ማዕቀቦችን ተግባራዊ ማደረግ የሚችል ሕግ እንዲሻሻል ያደረጉ ሲሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የወንጀል ቅጣቶችን መሻሻል ይኖርባቸው፣ ምህረት እርማት ይፈልጋልገዋል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በቅርቡ በላቲን ቋንቋ “Pascite Gregem Dei” (መንጋውን ይመግቡ) በሚል አርዕስት በቅርቡ ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ ሕግጋት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚከሰቱ ወንጀሎችን ይበልጥ ለመከላከል እና ጥፋተኞችን ለእርማት ለማብቃት የበለጠ ቀልጣፋ መሣሪያ እንደ ሚሆን ከወዲሁ የተነገረ ሲሆን እሱም “ከበድ ያሉ ክፋቶችን ለማስወገድ እና በሰው ልጆች ድክመት ምክንያት የሚከሰቱ ቁስሎችን ለማስታገስ” በፍጥነት የሚተገበር ሕግ እንደ ሆነም ተገልጿል።

“በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን” (1 ጴጥ 5፡2) በሚለው የሐዋርያው ጴጥሮስ መልእክት ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የቅጣት ማዕቀቦችን በተመለከተ የቀኖና ሕግ ቁጥር 6 እንዲሻሻል ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን የሐዋርያዊው ሕግ በላቲን ቋንቋ “Pascite Gregem Dei”  የሚል አርእስት ተሰጥቶታል፣ በእነዚህም ከደም ሲል የተጠቀሰው የሐዋርያው ​​ጴጥሮስ ቃላት ላይ መሰረቱን ያደረገ ነው። ማክሰኞ ግንቦት 24/2013 ዓ.ም ዕለት በቅድስት መንበር ፕሬስ ጽሕፈት ቤት የቀረበው አዲሱ ሐዋርያዊ ሕግ እ.አ.አ ከሚቀጥለው አመት ታህሳስ 8/2021 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንደ ሚውል ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በዓለም ዙሪያ ባሉት አብያተክርስቲያናት ፍላጎቶች በቂ ምላሽ ለመስጠት ፣ እ.አ.አ በጥር 25/1983 ዓ.ም በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ II የተላለፈው የቅጣት ሥነ ሥርዓት መሻሻል እንዳለበት አስፈላጊ እንደ ሆእን ይመስለኛል፣ የቤተክርስቲያን እረኞች ወይም አገልጋዮች ይበልጥ ቀልጣፋ የሆነ የማዳን እና የማረሚያ መሳሪያ አድርገው እንዲጠቀሙበት በሚያስችል መንገድ ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ ፣ በፍጥነት እና በሐዋርያዊ አገልግሎት የበጎ አድራጎት ድርጊቶችን ለማቀላጠፍ እና በሰው ድክመት ምክንያት የሚከሰቱ ቁስሎችን ለማስታገስ ይቻል ዘንድ ማሻሻያው አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

የቀድሞ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት በነዴክቶስ 16 ኛ ይህንን ማሻሻያ የጀመሩት እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም ሲሆን ይህም በዓለም ዙሪያ ካሉ የቤተክርስቲያን ቀኖና የሕግ ባለሙያዎች እንዲሁም ከብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች ፣ ከኃይማኖት ተቋማት ዋና ዋና ኃላፊዎች ጋር “በመተባበር እና በትብብር መንፈስ” የተደርገው ሂደት ውጤት ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ጳጳሳዊ ምክርቤቶች ተስትፎዋቸው የጎላ ነበር፣ በመጨረሻም የተገኘው ኃይለኛ እና ውስብስብ ጽሑፍ እ.አ.አ በየካቲት ወር 2020 ዓ.ም ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከቀረበ በኋላ ነበር አሁን በይፋ ማሻሻያ ተደርጎበት የቀረበው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሐዋርያዊ ሕግጋት ውስጥ እንደገለጹት ባለፉት መቶ ዘመናት ቤተክርስቲያኗ “የእግዚአብሔርን ህዝብ አንድ የሚያደርጋቸው እና ጳጳሳቱን የማክበር ኃላፊነት ያለባቸው” የስነምግባር ህጎችን አውጥታ እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም “ምጽዋት እና ምህረት አንዳንድ ጊዜ ጠማማ የሆነውን ነገር ለማቅናት ራሱን የሚሰጥ አባት ይጠይቃሉ” ሲል አጥብቆ ያሳስባል።

ይህ ተግባራዊ ሊሆን የሚገባው ጉዳይ ነው በማለት ስለሁኔታው ያብራሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ለቤተክርስቲያን ፣ ለክርስቲያን ማህበረሰብ እና ለተጎጂዎች ብቻ ሳይሆን ምህረትም ሆነ እርማት ለሚሹ እና ወንጀል ለሚፈጽሙ ሰዎች ተጨባጭ እና ምሕረትን ከግምት ባስገባ መስፈርት መከናወን አለበት።  ቀደም ባሉት ጊዜያት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የምሕረት ተግባር እና ፍትህ መካከል ያለው ልዩነት እና ግንኙነት ተጣርቶ በለመቀመጡ የተነሳ እና ግንዛቤ ባለመኖሩ ብዙ ጉዳት ደርሷል። ይህ አካሄድ “ብዙውን ጊዜ በምእመናን እና በቤተክርስቲያን መካከል እንዲከሰት እና ግራ መጋባት እንዲፈጥር የሚያደርግ በመሆኑ የተነሳ እንደየሁኔታው በምሕረት እና በፍትህ መካከል ያለው ልዩነት በሚገባ መገንዘብ ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገልጿል።

ስለሆነም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አክለው እንደ ገለጹት “አንድ የቤተክርስቲያን እረኛ በእነዚህ በምሕረት እና በፍትህ መካከል ያለውን ልዩነት ከግምት ሳያስገባ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጠሩትን ወንጀሎች ለመቅጣት የተቀመጡትን የመቅጫ ሕጎች ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ ይህ ስህተት እረኛ ቸልተኛ መሆኑን፣ ተግባሩን በትክክል እና በታማኝነት አለመፈጸሙን ያሳያል” ብለዋል።

በእውነቱ “ምሕረት በቤተክርስቲያኑ ማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን ሶስት ዓላማዎችን ማለትም የፍትህ ጥያቄዎችን መመለስ ፣ የወንጀለኛው ለውጥ እንዲያሳይ መርዳት እና ለፈጸመው በድለ ካስ እንዲከፍል ማድረግን” ያካትታል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “አዲሱ ጽሑፍ በአሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ ላይ የተለያዩ ለውጦችን የሚያስተዋውቅ ሲሆን በአንዳንድ አዳዲስ ጥፋቶች ላይም ማዕቀብ ይጥላል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አክለው እንደ ገለጹት ስድስተኛው ሕግ “ከመዋቅራዊ እይታ በተለይም እንደ የወንጀል ህግ መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም ራስን የመከላከል መብት፣ የወንጀል ድርጊት ውስንነት ደንብ ፣ እና ትክክለኛ የቅጣት ውሳኔን በተመለከተ” መሻሻሉን ልብ ልንል ይገባል፣ የቅጣት አተገባበርን አስመልክቶ ሥነ-ሥርዓታዊ አንድነት እንዲደግፍ እና “በተጨባጭ ጉዳይ ላይ ተግባራዊ ሊሆን ስለሚገባው ማዕቀብ ተገቢውን ግንዛቤ ይዞ በመለየት ተጨባጭ መመዘኛዎችን በመጠቀም በተለይም በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት እና በደል የሚያደርሱ ጥፋቶችን” ተገቢ በሆነ መልኩ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

02 June 2021, 13:21