ፈልግ

VAX Live በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የኮቪቭ -19 ክትባቶችን ያገኙ ዘንድ ለማበረታታት በማሰብ በበይነ መረብ አማካይነት የሚደረግ ኮንሰርት VAX Live በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የኮቪቭ -19 ክትባቶችን ያገኙ ዘንድ ለማበረታታት በማሰብ በበይነ መረብ አማካይነት የሚደረግ ኮንሰርት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለዓለማችን “ብርሃን እና ተስፋ ፣ የፈውስ እና የደህንነት ጎዳናዎች ያስፈልጓታል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ቅዳሜ ዕለት ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል VAX Live (በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ዜጎች ሁሉ ዓለምን እንደገና አንድ ላይ በማሰባሰብ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የኮቪቭ -19 ክትባቶችን ያገኙ ዘንድ ለማበረታታት በማሰብ በበይነ መረብ አማካይነት የሚደረግ ኮንሰርት ነው) ተሳታፊዎች በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ከኮቭድ -19 ቫይረስ ተጽኖዎች እና የግለሰባዊነት እና ዝግ የሆነ  ብሄራዊ ጥልቅ ስሜት የመፈወስ አስፈላጊነት ላይ አጥብቀው ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “እንደ እናንተ የማይጨፍር ወይም የማይዘፍን ነገር ግን እንደ እናንተ የሚያስብ እና የሚያምን በተለይም ደግሞ ክፉ ነገሮችን ለማሸነፍ እና ፍታዊነት በዓለም ዙሪያ ይሰፍን ዘንድ እንደ እናንተ ምኞት እና ፍላጎት ካለው ከአንድ የድሜ ባለጸጋ ሰላምታ ይድረሳችሁ” ብለዋል። “VAX Live: የተሰኘው ኮንሰርት በእዚህ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ተለያይታ የነበረች ዓለማችንን በድጋሚ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ በበይነ መረብ አማካይነት የሚደረግ አለም አቀፍ ኮንሰርት ነው።

ቅዳሜ እለት የተካሄደው ይህ ዝግጅት ኮቪድ -19 ክትባቶች በዓለም ዙሪያ ላሉት ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች መዳረስ አለበት የሚለውን ተስፋ መልሶ ለማንሰራራት ያለመ ኮንሰርት ነው። በተጨማሪም ክትባቶቹን በስፋት እና በፍትሃዊነት ለማሰራጨት የሚፈልጉ ድምፆች በስፋት እንዲሰሙ እያደረግ የሚገኝ ተቋም ነው።

ከስር መሰረት የመፈወስ ፍላጎት

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ የሚገኘው ወረርሽኝ በተፈጠረው “ጨለማ እና አለመተማመን” መካከል “ብርሃን እና ተስፋ ያስፈልገናል። የፈውስና የመዳን መንገዶች ያስፈልጉናል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመልእክታቸው ተጨማሪ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደ ገለጹት “የክፉውን ነገር መንስኤ የሚፈውስ እና በምልክቶቹ ብቻ የማይገደብ ከሥር መሰረቱ ይህንን ክፉ ነገር የሚያስወግድ ፈውስ ያስፈልገናል” ብለዋል።

ስለሆነም “የሁሉም ሰው ሕይወትን የሚነካ ሞትንና መከራን ያስከትላል” በተባለ በእዚህ ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳይሆን ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያደርግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኮንሰሩን ተካፋዮች ያበረታቱ ሲሆን እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን ማህበራዊና አካባቢያዊ ቀውሶች እንዲባባሱ ከሚያደርጉ ተግባራት ሁላችንም መቆጠብ እንደ ሚገባን ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ግለሰባዊነት ለሌሎች ስቃይ ግድየለሾች ያደርገናል

ልንፈውሳቸው ከሚገባን ሕመሞች መካከል አንዳንዶቹን በምሳሌ ሲያስረዱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት “በእነዚህ የታመሙ ሥሮች ውስጥ የግለሰባዊነት ቫይረስ እናገኛለን ፣ ይህም እኛ የበለጠ ነፃ ወይም የበለጠ እኩል ፣ ወይም ከዚያ በላይ ወንድማማቾች እንድንሆን አያደርገንም” ይልቁንም እኛን ግድየለሾች እንድንሆን ያደርገናል፣ የሌሎችን መከራ ችላ እንድንል ያደርገናል ብለዋል።

ሌሎች የዚህ የባህላዊ ቫይረስ ዓይነቶች እንዳሉ የገለጹት ቅዱስነታቸው ክትባቶችን ማጋራት የሚያግድ የተዘጋ ብሔርተኝነት እና የገበያ ወይም የአዕምሯዊ ንብረት ህጎችን ከፍቅር ህጎች እና ከሌሎች ጤናዎች በላይ ማድረግ ናቸው ያሉት ቅዱስነታቸው እንደዚሁም ሌላ ዓይነት የታመመ ኢኮኖሚ አለ “በጣም ሀብታም የሆኑ ጥቂቶች ከሌላው የሰው ልጅ ሁሉ የበለጠ ሐብታም እንዲሆኑ ያስቻላቸው የታመመ ኢኮኖሚ፣ እንዲሁም የምርት እና የፍጆታ ሞዴሎች ፕላኔታችንን‘ የጋራ ቤታችን ’ሊያጠፉ ነው” ስለዚህ የእዚህ ዓይነቱ ተግባር ሊገታ ይገባዋል ብለዋል።

ሁሉም ነገር የተገናኘ እና የተሰላሰለ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሁሉም ነገር ትስስር አጉልተው በማሳየት በተፈጥሮ እና በሰባዊነት አንድ እንደሆኑ ጠቁመዋል ፣ ስለሆነም በሰብዓዊነት ላይ የሚደርሰው እያንዳንዱ ማህበራዊ ኢ-ፍትሃዊነት እና ድርጊት እንዲሁ በአከባቢው ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክሎም እግዚአብሔር የጋራን ጥቅም ለማሳደግ ግለሰባዊነትን መተው የሚያስችለንን አዲስ እና ለጋስ መንፈስ በልባችን ውስጥ ይተክላል ብለዋል።

የክትባት ሁለንተናዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች በጊዜያዊነት እንዲታገዱ ማደረግ በራሱ እኛን የሚያነቃቃ የፍትህ መንፈስ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው የተለየ ፣ ሁሉን ያካተተ ፣ ፍትሐዊ ፣ ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ሞዴል ለማመንጨት የሚያስችለን የኅብረት መንፈስ ነው ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

ከወረርሽኝ በኋላ የሚመጣ የተሻለ ህብረተሰብ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “እኛ ከገባንበት ቀውስ ውስጥ ስንወጣ የተለየ ሰው እንሆናለን፣ በተሻለ ወይም በከፋ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ነው የምንወጣው” በማለት ለሁሉም ለተሳታፊዎች የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሆኖም በወረርሽኙ ሳቢያ እያጋጠመን ያለውን ችግር ለመቋቋም በምናደርገው ጥረት “ችግሩ የተሻሉ መንገዶችን ለመፈለግ የፈጠራ ችሎታችንን ማዳበር ይኖርብናል” ብለዋል።

ስለሆነም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ የሚገኙትን እንዲያጽናና የሞቱትን ወደ መንግስቱ እንዲቀበል ልንጸልይ ይገባል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በምድር ላይ ላሉት ምዕመናን “አዲስ የወንድማማችነት ስጦታ ፣ ዓለም አቀፋዊ አንድነት” እንዲሰጠን ጌታችንን መለመን ይገባል ብለው በእያንዳንዳችን ውስጥ የተዘራውን መልካም ዘር እና ውበት እንድንገነዘብ ፣ የአንድነት ትስስርን ለማጠንከር፣ የጋራ እቅዶቻችንን እና የጋራ ተስፋዎቻችንን” ከፍ ለማደረግ በጸሎት መበርታት ይኖርብናል ያሉ ሲሆን ቅዱስ አባታችን የቪዲዮ መልእክታቸውን ያጠናቀቁት ተሳታፊዎች ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና በማቅረብ እና ለእርሳቸው ለራሳቸው ፀሎት እንዲያደርጉ በመጠየቅ እንደ ነበረም ተገልጿል።

08 May 2021, 12:12