ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የቅድስት ሥላሴ ሕያው ምልክት ፍቅር ነው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ በሚነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በግንቦት 22/2013 ዓ.ም ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በእለቱ የተከበረውን የቅድስት ሥላሴ በዓል ምክንያት በማድረግ ከማቴዎስ ወንጌል ላይ ተወስዶ በተነበበውና ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ታላቁን ተልዕኮ የሰጠበት “ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (28፡16-20 ) በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን  የቅድስት ሥላሴ ሕያው ምልክት ፍቅር ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

እግዚአብሔርን በምናከብርበት በዚህ በዓል ላይ-የአንድ አምላክ ምስጢር ምን እንደ ሆነ እንረዳለን። እናም ይህ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ነው። ሦስት አካላት ግን እግዚአብሔር አንድ ነው! አብ እግዚአብሔር ነው፣ ወልድ እግዚአብሔር ነው፣ መንፈስ እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን እነሱ ሶስት አማላክ አይደሉም፣ በሶስት አካላት የሚገለጽ አንድ አምላክ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ የገለጠልን ምስጢር ነው-ቅድስት ሥላሴ። ዛሬ እኛ ይህንን ምስጢር ለማክበር ቆመናል ፣ ምክንያቱም እነዚህ አካላት የእግዚአብሔር ቅፅሎች አይደሉም ፣ በፍጹም አይደሉም። እነሱ እውነተኛ ፣ የተለያዩ ፣ ራሳቸውን የቻሉ አካላት ናቸው። እነሱ አንድ ፈላስፋ እንደ ተናገረው ‘ከእግዚአብሔር የወጡ አይደለም’  እነሱ ራሳቸውን የቻሉ አካላት ናቸው። ከአባታችን ጋር ሆነን የምጸልየው አባታችን የሚለው ጽሎት አለን፣ ቤዛነትን ፣ ጽድቅን የሰጠን ወልድ አለ። በእኛ የሚኖር በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አለ። እናም ይህ ስለ ልባችን ይናገራል ምክንያቱም ያንን ራእይ ሁሉ ጠቅለል አድርጎ በሚጠቅሰው በዚያ በቅዱስ ዮሐንስ አገላለጽ የተካተተ ሆኖ እናገኘዋለን (1 ዮሐ 4፡8፣ 16) አብ ፍቅር ነው፣ ወልድ ፍቅር ነው መንፈስ ቅዱስ ፍቅር ነው። እናም እርሱ ፍቅር ስለሆነ ፣ እግዚአብሔር አንድ ብቻ ሆኖ ሳለ በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ህብረት እንጂ ልዩነት የለም። ምክንያቱም ፍቅር በመሠረቱ ራስን አሳልፎ መስጠት ስለሆነ ከመጀመሪያው አንስቶ አስከ መጨረሻው ድረስ እውነተኛ በሆነ መልኩ ልጁን ለእኛ አሳልፎ የሰጠው ራሱ አብ ሲሆን እሱም ራሱን ለአባቱ ይሰጣል ፣ እናም የእነሱ ፍቅር ግንኙነት የተሳሰረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው። ይህንን አንድነት ለመረዳት ቀላል አይደለም ፣ ነገር ግን ይህንን ምስጢር መኖር እንችላለን ፣ ሁላችንም ፣በእዚህ መልኩ መኖር እንችላለን።

ይህ የቅድስት ሥላሴ ምስጢር በኢየሱስ ራሱ ተገለጠልን። የእግዚአብሔርን ፊት እንደ መሐሪ አባት አሳየን፣ እርሱ እውነተኛውን ሰው ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እና የአብ ቃል ፣ እርሱ ለእኛ ሲል ሕይወቱን እንደሚሰጥ አዳኝ አድርጎ አሳይቷል። እናም እርሱ ከአብ እና ከወልድ ስለሚወጣው ስለ መንፈስ ቅዱስ ፣ የእውነት መንፈስ ስለሆነው ስለጰራቅሊጦስ መንፈስ ተናገረ - ባለፈው እሁድ ስለዚህ ቃል ማለትም ‘ጴራቅሊጦስ’ የተናገረው ኢየሱስ አጽናኝ እና ጠበቃችን አንደ ሆነ አድርጎ ነው። እናም ኢየሱስ ከትንሳኤ በኋላ ለሐዋርያት በተገለጠ ጊዜ ኢየሱስ “አሕዛብን ሁሉ በአብ ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው የእኔ ደቀመዛሙርት አድርጓቸው” በማለት ይልካቸውኋል (ማቴ 28፡19)።

ስለዚህ የዛሬው በዓል እኛ ወደ መጣንበት እና ወደ ምድራዊ ጉዙዋችን ወደ ሚመራው ይህን አስደናቂ የፍቅር እና የብርሃን ምስጢር እንድናሰላስል ያደርገናል።

በቅዱስ ወንጌል መልእክት እና በሁሉም የክርስቲያን ተልእኮዎች ውስጥ አንድ ሰው ፣ ኢየሱስ በመካከላችን ያለውን የአብ ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስን አንድነት በመከተል ይህን አንድነት ችላ ማለት አይችልም-አንድ ሰው ይህንን አንድነት ችላ ማለት አይችልም። የቅዱስ ወንጌል ውበት እንድንኖር የሚጠይቀን አንድነት እና በጣም የተለያዩ በሆኑ መልኩ በመካከላችን ባለው ስምምነት የተረጋገጠ እንዲሆን ነው! እናም ይህ አንድነት ለክርስቲያኖች አስፈላጊ ነው ለማለት እደፍራለሁ-ይህ አመለካከት ፣ የመናገር አይነት አይደለም ፣ነገር ግን አስፈላጊ ነው ፣ ምክንያቱም ከፍቅር ፣ ከእግዚአብሄር ምህረት ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ መጽደቅ እና በልባችን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከመገኘቱ የተወለደው አንድነት ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በየዋህነቷ እና በትህትናዋ ፣ ኢየሱስን በሕይወቷ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ስለተቀበለችው ፣ የቅድስት ሥላሴን አምላክ ውበት አንጸባርቃላች። እምነታችንን እርሷ ታጽና፣ የእግዚአብሔር አምላኪዎች፣ የወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አገልጋዮች እንድንሆን እርሷ ትርዳን።

30 May 2021, 13:05