ፈልግ

ር.ሊ. ጳጳሳት ፖለቲካን ለሰዎች ብቻ ሳይሆን ከሰዎች ጋር ሆናችሁ በጋራ አራምዱ ማለታቸው ተገልጸ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በሕዝብ ውስጥ ስር የሰደደ ፖለቲካ” በሚል ርዕስ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው ኮንፈረንስ ለተሳተፉ ሰዎች የቪዲዮ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደ ጥሩ እረኛ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ሁሉ በማስቀደም ፖሌቲካን ለሰዎች መናገር ብቻ ሳይሆን ፖሌቲካን ከሰዎች ጋር አብሮ፣ በጋራ እና በመመካከር ማራመድ ያስፈልጋል ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በሕዝብ ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ተሳታፊዎች በሚያዝያ 08/2013 ዓ.ም ያስተላለፉትን የቪድዮ መልእክታቸውን የጀመሩት በእዚህ ኮንፈረንስ ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ሰላምታን በማቅረብ ነበር።

ይህንን ኮንፈረንስ ያዘጋጁት ደግሞ በለንደን የሚገኘው የስነ መለኮት እና ማህበረሰብ ማዕከል ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በወቅቱ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት በተለይም በአሜሪካ የሚገኙ የድሃ ማህበረሰቦች በተገቢ ሁኔታ እንዲኖሩ በመርዳት ላይ የሚገኘው የካቶሊክ ዘመቻ ለሰው ልጅ ልማት የተሰኘው ማሕበር የ 50 ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል በወቅቱ እያከበረ ስለነበር በድሆች ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ውሳኔዎች ውስጥ ተሳትፎአቸውን ማሳደግ እንዴት እንደ ሚችላ የሚረዱ የተለያየ ዓይነት አስተዋጾ ድርጅቱ በማደረጉ የተነሳ ቅዱስነታቸው ለየት ባለ ሁኔት የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሊቃነ ጳጳሳቱ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ሌሎች ሁሉም ድርጅቶች “እንዲሁ በዚህ ልኬት ውስጥ ሆነው እንደሠሩ” ጥሪ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን ተልዕኳቸው “ሥራ ፣ ደመወዝ እና መኖሪያ ቤት” ለማረጋገጥ በሚደርገው ሰላማዊ ትግል ውስጥ ሕዝቡን ማጀብ እና መቼም ቢሆን ከጎናቸው መቆም እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን በተለይም ድሆች የተቃውሞ አመለካከቶች እና ንቀት ሲያጋጥማቸው ከእነርሱ ጎን መቆም ተገቢ እንደ ሆነ ገልጸው ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ሥራቸው እና ምስክርነታቸው "እጅግ በጣም አስቸኳይ እና አስፈላጊ" መሆኑን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አጽኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “የስብሰባው ዋና ዓላማ እውነተኛ ምላሽ በትክክል በግለሰባዊነት ላይ የተመረኮዘ ሳይሆን በተቃራኒው ነው ፤ በሕዝቦች ሕይወት ውስጥ የተመሰረተው የወንድማማችነት ፖለቲካ” በማለት የስብሰባውን አንድ ዓላማ ገልጸዋል።

ሕልም እንድናልም

ኮንፈረንሱ “ሕልም እናልም” በሚል አርእስት እንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ከሆነው አውስተን ኢቭሬይ ጋር በመተባበር በተፃፈው በቅርቡ በታተመው የቅዱስ አባታችን መጽሐፍ ላይ በተወያዩ ጭብጦች ላይ መሠረቱን ያደረገ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ “እኔ ይህንን በእንግሊዘኛ ቋንቋ በcapital P' ፊደል በሚጀምረው የፖሌቲካ ዓይነት ፖለቲካን እንደ አገልግሎት እጠራዋለሁ ፣ ይህም ህዝቡ ራሱን እንዲያደራጅ እና እራሱን እንዲገልፅ አዳዲስ መንገዶችን የሚከፍት ነው’ በማለት ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን የእዚህ ዓይነቱ ፖለቲካ “ለህዝቦች ብቻ ሳይሆን ከህዝቦች ጋር ፣ በማህበረሰቦቻቸው እና በእሴቶቻቸው ላይ የተመሠረተ” ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “ሰዎች ወደ ጎን ሲጣሉ ቁሳዊ የሆኑ ፍላጎቶቻቸውን ብቻ ሳይሆን የተነፈጉት፣ ስበዓዊ ክብራቸውን ጭምር ነው የሚገፈፉት፣ የራሳቸው እጣ ፈንታ እና ታሪክ ተዋናይ በመሆን ፣ እሴቶቻቸውን እና ባህሎቻቸውን ፣ የፈጠራ ችሎታቸውን መግለፅ እንዲችሉ ማገዝ ይገባል። ፍሬያማ መሆን ይችሉ ዘንድ ፖሌቲከኞች በተለይም አቅመ ደካማ የሚባሉ ሰዎችን ማገዝ ይኖርባቸዋል” በማለት ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ለቤተክርስቲያኗ የክብር ስሜት ምንጭ የሆኑትን መንፈሳዊ እሴቶችን የሚያካትቱ ማህበራዊ ፍትህ ማስፈን ከህዝቡ ባህል እና እሴቶች እውቅና ለመለየት  “የማይቻለው” በዚህ ምክንያት እንደሆነ አስረድተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል በእዚህ ኮንፈረንስ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ብዙዎች “ከሰዎች እንቅስቃሴ ጋር እየተራመዱ” ለብዙ ዓመታት እንዳሳለፉ ይናገራሉ፣ ይህ ተግባር በጣም “የፖለቲካ” ወይም “ሃይማኖትን ለመጫን በመሞከር” ከሚሰነዘሩ በርካታ ክሶች የተነሳ ብዙውን ጊዜ “የማይመች” እንደሆነ ገልፀዋል።

"ነገር ግን ሕዝብን ማክበር ማለት የሃይማኖቶቻቸውን ጨምሮ ለተቋሞቻቸው ክብር መስጠት ማለት እንደሆነ እናተ ተረድታችኋል፣ እናም የእነዚያን ተቋማት ሚና ከህዝብ ጋር ለመራመድ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ጫና ማስወገድ ማለት ነው፣ እናም ሁል ጊዜ ከፊት ለፊታችን የሚሄደውን የእግዚአብሔርን ፊት በማስታወስ፣ በእዚህ መልኩ ተግባሮቻችንን ማከናወን ይኖርብናል” ብለዋል።

እውነተኛ እረኛ በሁሉም ቦታ አለ

“እውነተኛው እረኛ”  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ እንደ ተናገሩት “ ከእዝቡ ፊት ለፊት፣ በሕዝቡ መካከል እና ከሕዝቡ በኋላ ሆኖ መራመድ ማለት ነው” በማለት የተናገሩ ሲሆን ወደ ፊት የሚመጣውን አንድ ነገር ለእነሱ ለመጠቆም ፣ በመካከላቸው መሆን ደግሞ የሕዝቡን ስሜቶች ለመረዳት እና ስህተት ላለመፈፀም፣ ከኋላቸው ሆኖ መጓዝ ደግሞ በችግር ላይ የሚገኙትን ለመርዳት እና ህዝቡ እነዚህን ነገሮች በራሱ አፍንጫ እንዲያሸታቸው እና የራሳቸውን ትክክለኛ የለውጥ መንገድ እንዲያገኙ ሕዝቡን መርዳት ማለት ነው” ብለዋል።

መንገዱን አብሩ

“በጣም ድሃ በሆኑት ማህበረሰቦቻችን ውስጥ ከሞት የተነሳውን ፣ የቆሰለውን ክርስቶስን ለመገናኘት የመውጣት ሚስዮናዊነታችንን እንዲያገግም ያደርጋል” እንደሚባለው ሁሉ ድሆችን ወደኋላ የሚተው ፖለቲካ “መቼም ቢሆን የጋራ ጥቅምን ማጎልበት አይችልም” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ የቪድዮ መልእክታቸውን ሲያጠናቅቁ “አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በሕዝቦች ውስጥ ሥር መሰረቱን ያደርገ እና ከእዝብ ጋር አንድነት የፈጠረ ፖለቲካ በመጪው ጊዜ የወደፊቱን መገንባት ያስችላል” ያሉ ሲሆን “ይህ ኮንፈረንስ በእዚህ መልኩ እንቀጥል ዘንድ መንገዱን ለማብራት እንዲረዳን” ምኞቴ ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

16 April 2021, 10:51