ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ዮሴፍ ሐውልት ሥር ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ዮሴፍ ሐውልት ሥር 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቅዱስ ዮሴፍ የታማኝ አገልጋይ ምሳሌ ነው አሉ!

የተለያዩ መንፈሳዊ የሆኑ አገልግሎቶችን የሚያከናውኑ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት እና ደናግላን ገዳማዊያት በቁጥር እና በጥራት በዝተው የተለያዩ የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ የሆኑ ተልዕኮዎችን እውን ያደርጉ ዘንድ ለእዚህ መንፈሳዊ የሆነ ጥሪ መልስ የሚሰጡ ሰዎች በቁጥር እና በጥራት ይበረክቱ ዘንድ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ምዕመናን ዘንድ የቅዱስ ዮሴፍ አመታዊ በዓል በሚከበርበት ቀን ላይ ከእዚህ በዓል ጋር ተያይዞ በመጪው ሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን ዝግጅት ይሆን ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክት እንደ ሚያስተላለፉ ይታወቃል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእዚህ መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጪው ሚያዚያ 17/2013 ዓ.ም ለሚከበረው ለዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን ቅድመ ዝግጅት ይሆን ዘንድ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ሁሉም ገዳማዊያን/ገዳማዊያት እና ቀሳውስት የእግዚአብሔርን የአገልግሎት ጥሪ በመቀበል ሕጻኑን እየሱስን እና እናቱን ማርያምን በታማኝነት ሲያገለግል የነበረውን የቅዱስ ዮሴፍ ምሳሌ እና አብነት እንዲከተሉ አሳስበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሁሉም ገዳማዊያን/ገዳማዊያት እና ቀሳውስት አርአያ የነበረ፣ የድንግል ማርያም እጮኛ እና የኢየሱስን አሳዳጊ አባት የነበረውን የቅዱስ ዮሴፍ ምሳሌ መከተል ተገቢ እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን በላቲን ቋንቋ “Patris corde” በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎን “የአብ ልብ” በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕዳር 29/2013 ዓ.ም ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ መልዕእክት ላይ መሰረታቸውን በማደረግ  “ለዚህ ታላቅ ቅዱስ፣ ቅዱስ ዮሴፍ  ያለንን ፍቅር ለማሳደግ” መጣር ይኖርብናል ብለዋል።

የአባት ልብ

ቅዱስ ዮሴፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት እጅግ አስገራሚ የሆነ ስብዕና የነበረው ሰው ነበር፣ በሚያስደንቅ ማራኪነት ወይም በልዩ ሁኔታ ምክንያት ሳይሆን ነገር ግን በዕለት ተዕለት ሕይወቱ ውስጥ አስደናቂ የአገልግሎት ተግባራትን ስላከናወነ ነው።

“እግዚአብሔር ልብን ይመለከታል” በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “በቅዱስ ዮሴፍ  ውስጥ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሕይወትን መስጠት እና ማመንጨት የሚችል የአባት ልብ የነበረው ቅዱስ ነበር” ብለዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም መንፈሳዊ ጥሪ የሌሎች ህይወት በአዲስ መልክ እንዲወለድ እና እንዲታደስ የማድረግ ተመሳሳይ ግብ አለው” ብለዋል። በተጨማሪም የክህነት እና የተቀደሰ ሕይወት “ታላቅ ተነሳሽነት ያላቸው ፣ ራሳቸውን ችለው የመለገስ ችሎታ ያላቸው ፣ የተጨነቁትን የሚያጽናኑ እና ተስፋን የሚያጠናክሩ ጽኑ ልብ ያላቸው ወንዶች እና ሴቶችን ይጠይቃል” ብለዋል።

ሕልምን ማሳደድ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ቅዱስ ዮሴፍ ለእያንዳንዱ ግለሰብ ጥሪ ማለትም በሕልም ፣ በአገልግሎት እና በታማኝነት በሚጠቁማቸው ሦስት ቁልፍ ቃላት ላይ አተኩረዋል።

የማቴዎስ ወንጌል እግዚአብሔር ቅዱስ ዮሴፍን በመንፈስ አነሳሽነት ያሳየባቸውን አራት ሕልሞች ይናገራል ፣ እያንዳንዳቸውም የእግዚአብሔርን ከባድ ጥሪ ይወክላሉ። “ቅዱስ ዮሴፍ ከእያንዳንዱ ሕልም በኋላ ሙሉ በሙሉ የታመነበትን የእግዚአብሔርን ምስጢራዊ ንድፈ ሐሳቦችን ለመከተል የራሱን እቅዶች መሥዋዕት በማድረግ እቅዶቹን መለወጥ እና አደጋ ላይ መውደቅ ነበረበት” ብለዋል።

ምንም እንኳን በሕልሞች ላይ ይህን ያህል እምነት የሚጥል መስሎ ቢታየንም ቅዱስ ዮሴፍ ግን ያለምንም ማመንታት ራሱን በእዚህ ሕልም እንዲመራ ይፈቅዳል። "ለምን?" በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የመደመም ስሜት በማሳየት ምልእክታቸውን ሲቀጥሉ ምክንያቱም ልቡ ወደ እግዚአብሔር ያቀና ነበርና፣ ቀድሞ ወደ እርሱ ያዘነበለ ነበር። በንቃት ለሚጠብቀው 'ውስጣዊ ጆሮው' የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመለየት የሚያስችል ትንሽ ማሳያ በቂ ነበር ብለዋል።

በነጻነታችን ላይ ጫና ሳያስቀምጥ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን የሚያቀርበው ጥሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደተናገሩት በተመሳሳይ ሁኔታ ይከሰታል ብለዋል። ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ሲቀጥሉ “እርሱ ማለትም እግዚአብሔር አንጸባራቂ በሚመስሉ ራእዮች አይሸፍነንም ነገር ግን በጸጥታ በልባችን ጥልቀት ውስጥ ይናገራል ፣ ወደ እኛ ይቀርባል እና በአስተሳሰባችን እና በስሜታችን ይናገራል ” ያሉ ሲሆን ሆኖም ቅዱስ ዮሴፍ እንደሚያሳየው የእግዚአብሔርን ጥሪ መቀበላችን በራሱ ተጨባጭ የሆነ ነገር ሊሆን አይችልም፣ ነገር ግን ወደ ፊት እንድንገፋ እና እራሳችንን ለእርሱ ጸጋ ክፍት በማድረግ አደጋዎችን መጋፈጥ ይጠይቃል” ብለዋል።

ማገልገል እና መጠበቅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ እንደ ተናገሩት ቅዱስ ዮሴፍ የተቀበለውን መንፈሳዊ ጥሪ ከአገልግሎት ጋር በማጣመር ተግብሮታል፣ ያሉት ቅዱስነታቸው “ቅዱስ ወንጌል ቅዱስ ዮሴፍ ለራሱ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ለሌሎች እንደ ኖረ ያሳየናል፣ ራስ ወዳድ ከሆነ ፍቅር ሁሉ ራሱን ነፃ በማድረግ የበለጠ ፍሬያማ የሆነ አገልግሎት ለማግኘት ራሱን ለእግዚአብሔር ጸጋ ክፍት አደረገ” ብለዋል። ገደብ የለሽ ከሆነው ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅሩ ቅዱስ ዮሴፍ ዕለት ተዕለት የሚገጥመውን ፈተና እና መስዋዕትነት በአሸናፊነት እንዲወጣ አስችሎታል” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ “ሕይወት መስመሯን በምትለውጥበት ወቅት ተስፋ የማይቆርጡ ሰዎች የሚከተሉትን ልዩ የሆነ መንገድ ቅዱስ ዮሴፍ ተከትሏል” ያሉ ሲሆን ለማገልገል ከሚኖሩት ሰዎች መካከል የሚመደብ ዓይነተኛ ፈቃደኝነት አሳይቷል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አክለውም ቅዱስ ዮሴፍ ለማገልገል ፈቃደኛ በመሆን የተሰጠውን ኃላፊነት በመወጣት ለተሰጠው ጥሪ ጥበቃ ማድረጉን የገለጹ ሲሆን በእዚህም አግባብ እርሱ “የጥሪዎች ሁሉ ጠባቂ” ነው ብለው ማሰብ እንደ ሚወዱ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል። “እንዲህ ያለው አሳቢነት የእውነተኛ ጥሪ ምልክት ነው በእግዚአብሔር ፍቅር የተነካ የሕይወት ምስክርነት” ነው ብለዋል።

ቀለል ባለ ሁኔታ በየቀኑ ታማኝ መሆን

ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ ታማኝ የሚለው ቃል መንፈሳዊ ጥሪ ተቀብለው ለሚኖሩ ቀሳውስት እና ገዳማዊያት ቅዱስ ዮሴፍ የሰጠው ሦስተኛው ገጽታ ወይም ምሳሌ ነው ብለዋል። እሱ ማለትም ቅዱስ ዮሴፍ ሁል ጊዜ በትዕግሥት ድርጊቱን ያሰላስል ነበር ፣ እናም “በህይወት ውስጥ ስኬታማነት የሚመሰረተው አስፈላጊ በሆኑ ውሳኔዎች ላይ የማያቋርጥ ታማኝነት ላይ እንደሆነ” ያውቅ ነበር ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ እንደ ተናገሩት እያንዳንዳችን ታማኘትን እንዴት ኮትኩተን ማሳደግ እንደ ሚገባን እግዚአብሔር ያስተምረናል ያሉ ሲሆን “ይህ ታማኝነት የደስታ ምስጢር ነው” ብለዋል። ይህ የዋዕ በመሆን የሚገኝ ደስታ ነው፣ በእውነት አስፈላጊ የሆኑትን የሚመለከቱ ሰዎች በየቀኑ የሚያገኙት ደስታ ለእግዚአብሔር እና ለባልንጀሮቻችን በታማኝነት መቀራረብ ነው” ብለዋል።

የደስታ ምሳሌ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጪው ሚያዚያ 17/2013 ዓ.ም ለሚከበረው ለዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን ዝግጅት ይሆን ዘንድ ያስተላለፉትን መልእክት ያጠናቀቁት የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች ቤታቸውን በዚህ ተመሳሳይ “ቀላል እና ብሩህ ፣ ልባም እና ተስፋ ሰጭ” ደስታ እንዲሞሉ በማሳሰብ ነበር።

“ወንድሞቼ እና እህቶቼ እርሱን በምታገለግሉበት ወቅት የዘለአለማዊ ምርጫዎች እና ስሜቶች ውስጥ ጠንካራ ምስክርነት መስጠት ትችሉ ዘንድ፣ በእዚህ ረገድ ተመሳሳይ ደስታ እንድታገኙ እፀልያለሁ፣ በተጨማሪም ደስታችው ዘላቂ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

19 March 2021, 19:46