ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከኢራቅ መልስ የምስጋና ጸሎት ሲያቀርቡ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ከኢራቅ መልስ የምስጋና ጸሎት ሲያቀርቡ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ወደ እመቤታችን ማርያም ዘንድ የምስጋና ጸሎት አቀረቡ

ርዕሠ  ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኢራቅ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ወደ ሮም መመለሳቸውን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል አስታወቀ። ቅዱስነታቸው ወደ ሮም ከደረሱ በኋላ ወደ ቅድስት መንበር ከመድረሳው በፊት በሮም ከተማ በሚገኝ ታላቁ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በመሄድ፣ በኢራቅ ላደረገችላቸው ጥበቃ እና እርዳታ የምስጋና ጸሎታቸውን አድርሰዋል። ቅዱስነታቸው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ፈጽመው ወደ ሮም ሲመለሱ “ሳንታ ማሪያ ማጆሬ” በመባል ወደሚታወቅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታላቁ ባዚሊካ በመሄድ የምስጋናን ጸሎት እንደሚያቀርቡ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው ከዚህም በተጨማሪ ከኢራቅ ይዘው የመጡትን የአበባ ጉንጉን በመንበረ ታቦት አጠገብ፣ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል ሥር አስቀምጠዋል።

ከዚህ አጭር ሥነ-ሥርዓት በኋላ፣ ቅዱስነታቸው በመካከለኛው ምሥራቅ አገር በሆነችው ኢራቅ ያደረጉትን የአራት ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰላም ፈጽመው በቫቲካን ውስጥ ወደሚገኝ ቅድስት ማርታ የር. ሊ. ጳጳሳት መኖሪያ ቤት መግባታቸውን የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል አስታውቋል።     

09 March 2021, 10:47