ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  በቅርቡ ኢራቅን ይጎበኛሉ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅርቡ ኢራቅን ይጎበኛሉ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢራቅ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የጉዞ መረሃ ግብር

ሐዋርያዊ ጉብኝቱ የሚከናወነው ከየካቲት 26-29 ዓ.ም ድረስ ነው።

ሐዋርያዊ ጉብኝቱ የሚከናወነው ከየካቲት 26-29 ዓ.ም ድረስ ነው።

አርብ የካቲት 26 ከሮም ወደ ኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ጉዞ ማደረግ ይጀምራሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 07:30 ከሮማ  ፉሚቺኖ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ተነስተው ወደ ኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የሚያደርጉትን ጉዞ ይጀምራሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 14:00 በባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 14:00 ይፋዊ አቀባበል በባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደረግላቸዋል።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 14፡10 በባግዳድ አየር ማረፊያ የቪአይፒ አዳራሽ ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር 15፡00 ይፋዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ሥነ ስርዓት በባግዳድ በፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግስት ውስጥ ይካሄዳል።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር 15፡15 በባግዳድ በሚገኘው የኢራቅ ሪፖብሊክ በፕሬዝዳንታዊው የግል ቢሮ ውስጥ ከሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ጋር ይገናኛሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር 15:45 በባግዳድ ውስጥ በፕሬዝዳንታዊው አዳራሽ ውስጥ ከባለስልጣናት ፣ ከሲቪል ማኅበራት እና ከዲፕሎማቲክ አካላት ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ ቅዱስነታቸው ንግግር ያደርጋሉ።

በሮም ሰዓት አቆጣጠር 16፡ 40 ከብጽዕን ጳጳሳት፣ ከካህናት ፣ ከገዳማዊያን/ገዳማዊያት፣ ከዘረዓ ክህነት ተማሪዎች፣ ካታኪስቶች ጋር “የመዳኛ እመቤታችን” ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራ  በሚባለው ቤተክርስቲያን ውስጥ ተገናኝተው ንግግር ያደርጋሉ።

 ቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም

በሮም የሰዓት አቆጣጠር 07:45 ናጃፍ በመባል ወደ ምትታወቀው ከተማ በአውሮፕላን          ይሄዳሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር 08:30 ናጃፍ አየር ማረፊያ ይደርሳሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር 09:00 ላይ ካታላቁ  አያቶላህ ሰይድ አሊ አል-ሁሰኒ አል-ሲስታኒ በናጃፍ ውስጥ የገናኛሉ።

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 10:00 ወደ ናሲሪያሪያ በአውሮፕላን ይጓዛሉ።

በሮም ሰዓት አቆጣጠር ረፋዱ ላይ 10፡50 ናሲሪያ አየር ማረፊያ ይደርሳሉ።

ከረፋዱ 11፡10 ከተለያዩ የአይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በዑር ተገናኝተው ይወያያሉ፣ በወቅቱ ቅዱስነታቸው ንግግር ያደርጋሉ።

ከቀኑ 12፡30 ወደ ባግዳድ በአውሮፕላን ይመለሳሉ።

ከሰዓት በኋላ 13፡20 ባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

አመሻሱ ላይ 18:00 ቅዱስ አባታችን በባግዳድ ውስጥ በ “ቅዱስ ዮሴፍ” የከለዳውያን ካቴድራል ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ።

እሑድ የካቲት 28/2013 ዓ.ም

በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 07:15 ወደ ኤርቢል በአውሮፕላን ይሄዳሉ።

ጥዋት 08፡20 በኤርቢል አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

ከጥዋቱ 08፡20 በኢራቂ ኩርዲስታን ሉዋላዊ ክልል ፕሬዝዳንት እና የክልሉ የሃይማኖት እና የሲቪል ባለስልጣናት በኤርቢል አውሮፕላን ማረፊያ ለቅዱስነታቸው አቀባበል ያደርጉላቸዋል።

ከጥዋቱ 08:30 ከኤርቢል አየር ማረፊያ በፕሬዝዳንታዊ የቪአይፒ ክፍል ውስጥ በኢራቂ ኩርዲስታን ሉዋላዊ ክልል ፕሬዝዳንት እና የክልሉ የሃይማኖት እና የሲቪል ባለስልጣናት ከኤርቢል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ስብሰባ ያደርጋሉ።

ጥዋት 09:00 ወደ ሞሱል በሄሊኮፕተር ይሄዳሉ።

ጥዋት 09፡35 በሞሱል አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

ጥዋት 10፡00 በጦርነቱ ለተጎዱት እና ከፍተኛ መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች ጸሎት ይደረጋል፣ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ በሆሹ አል ቢያአ (የቤተክርስቲያን አደባባይ) ላይ ጸሎት ያደርጋሉ።

ጥዋት 10:55 ወደ ቃራኮሽ በሄሊኮፕተር ይሄዳሉ

ጥዋት 11፡10 በቃራኮሽ የአውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

ረፋዱ ላይ 11፡30 የቃራኮሽ ማኅበረሰብ የሚጎበኙ ሲሆን በእዚያም “ያለ አዳም ኃጢአት የተጸነሰች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም” ቤተክርስቲያን ውስጥ ከምዕመኑ ጋር ይገናኛሉ።

ረፋዱ ላይ 12፡15 ወደ ኤርቢል ይሄዳሉ

ቅዱስ አባታችን በኤርቢል በሚገኘው “ፍራንሶ ሀሪሪ” ስታዲየም መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ ቅዱስነታቸው በመስዋዕተ ቅዳሴው ላይ ስብከት ያሰማሉ።

ማምሻው ላይ 18:10 ወደ ባግዳድ በአውሮፕላን ይመለሳሉ።

ማታ 19፡15 በባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

ሰኞ የካቲት 29/2013 ዓ.ም

ከባግዳድ ወደ ሮም

ከጥዋቱ 09፡20 የባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ለቅዱስነታቸው አሸኛኘት ይደረግላቸዋል።

ከጥዋቱ 09:40 ወደ ሮም በአውሮፕላን መመለስ ይጀምራሉ።

እኩለ ቀን ላይ 12:55 በሮም ከተማ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ቻፒኖ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደ ሚደርሱ ከወጣው የጉዞ መረሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

04 March 2021, 09:58