ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካንሰር በሽታ የሚሰቃዩ ሕፃናትን በጸሎታቸው እንደ ሚያስታውሱ ገለጹ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካንሰር በሽታ የሚሰቃዩ ሕፃናትን በጸሎታቸው እንደ ሚያስታውሱ ገለጹ። 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካንሰር በሽታ የሚሰቃዩ ሕፃናትን በጸሎታቸው እንደ ሚያስታውሱ ገለጹ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የካቲት 08/2013 ዓ.ም ተከብሮ ባለፈው ዓለም አቀፍ የካንሰር እመምተኞች ቀን ላይ ባስተላለፉት መልእክት በተለይም ደግሞ በካንሰር በሽታ የሚሰቃዩ ሕጻናት ልጆችን በጸሎታቸው እንደ ሚያስታውሱ ገልጸው እንደ ነበረ ይታወሳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በየካቲት 08/2013 ዓ.ም በትዊተር ገፃቸው በሰጡት መግለጫ በካንሰር በሽታ ከሚሰቃዩ ሕፃናት ጋር ያላቸውን ቅርበት የገለጹ ሲሆን ሁሉም ሰዎች እንዲረዷቸው እና በጣም ደካማውን መርዳት ቅድሚያ እንደሚሰጥ እርግጠኛ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

"ጌታ ለሚሰቃዩት በተለይም ለህፃናት እንዲቀርብ እና በጣም ደካማውን በማስቀደም ሁሉንም ሰው እንዲያነሳሳ የሕክምና ባለሙያዎች እና የታመሙትን ሁሉ በእናትነት ፍቅሯ እንድትጠብቃቸው ለድንግል ማርያም አደራ እላለሁ” በማለት መግለጻቸው ይታወሳል።

የካቲት 08/2013 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የልጆች የካንሰር ቀን በሚል መጠሪያ በእየ አመቱ የሚከበረው ዓመታዊው ቀን ሲሆን ስለ ሕፃናት ካንሰር ዘመቻ የማድረግና ግንዛቤ የማስጨበጥ ዓላማ ያነገበ ቀን ነው።

ቀኑ በበርካታ ፣ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ተነሳሽነት ለእነሱ ፣ በሕይወት ለተረፉ እና ለቤተሰቦቻቸው ድጋፍን እንዲደረግ የሚያበረታታ ቀን ሲሆን ትኩረት ከካንሰር ጋር ለሚታገሉ ሕፃናት ሁሉን አቀፍ ሕክምናዎችን ማግኘትና እንክብካቤ የማድረግ አስፈላጊነትም ትኩረት የሚሰጥ አለም አቀፍ ቀን ነው።

15 February 2021, 12:35