ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትዕግሥት በገዳም ሕይወት ውስጥ ለሚኖሩ ወንድ እና ሴቶች መለያ ምልክት ነው አሉ

በጥር 25/2013 ዓ.ም በሙሴ ሕግ መሠረት፣ የመንጻታቸው ወቅት በተፈፀመ ጊዜ፣ ዮሴፍና ማርያም ሕፃኑን ለጌታ ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት የሄዱበት፣ ሕፃኑን ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ የተወሰደበት፣ አረጋዊያኑ ስምዖን እና ነቢይት የነበረችው አና ሕፃኑን ኢየሱስ የተገናኙበት፣ “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣ አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣ማዳንህን አይተዋልና” በማለት አዛውንቱ ስምዖን ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀረበበት እለት ዓመታዊ በዓል ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ከእዚህ በዓል ጋር መሳ ለመሳ ሕይወታቸውን ለየት ባለ ሁኔታ በቅድስና ለመኖር ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርገው ያቀረቡ ገዳማዊያን/ገዳማዊያት በዓል ታስቦ መዋሉም ይታወቃል። 

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

ይህ በዓል በቫቲካን በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በወቅቱ ይህንን መስዋዕተ ቅዳሴ ለታደሙ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ትዕግሥት በገዳም ሕይወት ውስጥ ለሚኖሩ ወንድ እና ሴቶች መለያ ምልክት ነው ማለታቸው ተገልጿል። 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

ስምዖን “የእስራኤልን መጽናናት በተስፋ ይጠባበቅ ነበር” (ሉቃ 2፡25) በማለት ወንጌላዊው ሉቃስ ይነግረናል።  ማርያምና ዮሴፍ ኢየሱስን ወደ ቤተመቅደስ በወሰዱበት ወቅት ስምዖን መሲሁን ተቀብሎ አቀፈው። በአሕዛብ ላይ እንዲበራ የመጣው ብርሃን በዚያ ሕፃን ውስጥ የተገነዘበው የጌታን ተስፋዎች ፍጻሜ በትዕግሥት ይጠባበቅ የነበረ አንድ አዛውንት ሰው ነበር።

የስምዖን ትዕግሥት። እስቲ የዚያን አዛውንት ሰው ትዕግሥት ጠለቅ ብለን እንመርምር። በሕይወቱ ሁሉ በልቡ በትዕግሥት እየጠበቀ ነበር። ስምዖን በጸሎቱ ውስጥ እግዚአብሔር ባልተለመዱ ክስተቶች ውስጥ እንደማይመጣ ተገንዝቧል ፣ ነገር ግን በእለት ተዕለት ኑሯችን በሚታየው ብቸኝነት ፣ በሚከናወነው አሰልቺ እንቅስቃሴያችን ፣ በትጋት እና በትህትና እየሰራን ባለንበት ጥቃቅን ነገሮች ውስጥ ፈቃዱን ለመፈጸም በምናደርገው ጥረት ውስጥ ይሠራል። በትእግስት በመፅናት ጠበቀ እንጂ ስምዖን በጊዜ ሂደት አልደከመም። እሱ አሁን አዛውንት ነው፣ ነበልባሉም አሁንም በልቡ ውስጥ በደንብ እየነደደ ነበር። በረጅሙ ህይወቱ ውስጥ የተጎዳበት ፣ የተበሳጨበት ጊዜዎች ነበሩ ፣ ግን ተስፋ አልቆረጠም። እሱ በተስፋው ታምኖ ነበር ፣ እናም ላለፉት ጊዜያት በጸጸት ወይም በሕይወታችን በሚከሰቱ ጨለማዎች ውስጥ ስንገባ በሚመጣ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዲዋጥ አልፈቀደም። በመጨረሻ ላይ “ዓይኖቹ የተሰጠውን ተስፋ ማዳን እስኪያዩ ድረስ” ተስፋ ባይቆርጡም ምንም እንኳን ሁሉንም ነገር በትዕግስት ቢጠብቅም ይህንን ትዕግስቱን እለታዊ በሆነ ሕይወቱ ገልጿል። 

እኔ እራሴን እጠይቃለሁ-ስምዖን እንደዚህ ዓይነቱን ትዕግስት የተማረው የት ነው? እርሱ ትዕስግሥት የተወለደው ከጸሎት እና ከሕዝቦቹ ታሪክ ነው ፣ ይህም ሁል ጊዜ በጌታ ውስጥ “መሐሪና ቸር የሆነ ፣ ለቁጣ የዘገየ ፣ ጽኑ ፍቅርና ታማኝነቱ የበዛ” (ዘጸ 34፡6) አምላክ እንደ ሆነ ከሚሰማው እምነቱ የመነጨ ነው። እምቢታ እና ክህደት ቢኖርም እንኳ ፈጽሞ ተስፋ የማይቆርጠውን አባት እውቅና ሰጠው ነገር ግን “ለብዙ ዓመታት ታጋሽ” በመሆን  የመለወጥ እድልን ያለማቋረጥ በመያዝ ኑሮውን ቀጠለ።

ስለሆነም የስምዖን ትዕግሥት የእግዚአብሔር የራሱ ትዕግሥት መስታወት ነው። ስምዖን ከጸሎትና ከወገኖቹ ታሪክ እግዚአብሔር በእርግጥ ታጋሽ መሆኑን ተረድቷል። በዚያ ትዕግሥት ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ሚለው እግዚአብሔር “ወደ ንስሐ ይመራናል” ይለናል (ሮሜ 2 4)። ትዕግሥት ለድክመታችን ምላሽ ለመስጠት እና ለመለወጥ የሚያስፈልገንን ጊዜ የሚሰጠን የእግዚአብሔር መንገድ መሆኑን በአንድ ጊዜ የተመለከተውን ሮማኖ ጋሪዲኒን የተባለውን ሰው ማሰብ እፈልጋለሁ። ከማንም በላይ ስምዖን በእቅፉ የያዘው መሲሕ ኢየሱስ እርሱ እስከ መጨረሻው ሰዓታችን ድረስ የሚጠራን መሐሪ አባት የሆነውን የእግዚአብሔርን ትዕግሥት ያሳየናል። ፍጽምናን የማይፈልግ ፣ ግን ከልብ የመነጨ ቅንዓት ፣ ሁሉም የጠፋ ሲመስል አዳዲስ ዕድሎችን የሚከፍት ፣ በጠንካራ ልባችን ውስጥ ጥሶ ለመግባት የሚፈልግ ፣ እንክርዳዱን ሳይነቅል መልካም ዘር እንዲያድግ ማደረግ ያስችለዋል። ለተስፋችን ምክንያት ይህ ነው-እግዚአብሔር እኛን መጠበቁን አይታክትም። ዞር ስንል እርሱ እኛን ፍለጋ ይመጣል። ስንወድቅ በእግር እንድንቆም ያደርገናል፣ ከመንገዳችን ወጥተን በመሄድ በምንጠፋበት ወቅት ከእዚያ ከጠፋንበት ስፍራ ተመልሰን ወደ እርሱ በምንመጣበት ወቅት እርሱ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበለናል። ፍቅሩ በሰው ልጆች ሂሳባ ሊመዘን አይችልም፣ ነገር ግን ያለማቋረጥ እንደገና ለመጀመር ድፍረትን ይሰጠናል። ይህ ጥንካሬን ያስተምረናል ፣ ድፍረትን ሁል ጊዜ እንደገና ለመጀመር በየቀኑ እንድንነሳ ያደርገናል። ከወደቅን በኋላ እንደገና ለመጀመር እንችል ዘንድ ሁል ጊዜ እግዚአብሔር ይጠባበቀናል። እግዚአብሔር ታጋሽ ነው።

የእኛን ትዕግስ እንመልከት። የራሳችንን የገዳም ሕይወት ስንመለከት የእግዚአብሔርን ትዕግስት እና የስምዖንን ትዕግሥት እናያለን። ትዕግስት በእውነቱ ምን እንደሚጨምር እራሳችንን መጠየቅ እንችላለን። በእርግጠኝነት እሱ ችግሮችን ለመቋቋም ወይም በችግር ጊዜ ከባድ ውሳኔን ለማሳየት ብቻ አይደለም። ትዕግሥት የድክመት ምልክት አይደለም ፣ “ሸክሙን እንድንሸከም” ፣ እንድንፀና ፣ የግል እና የማህበረሰብ ችግሮች እንድንሸከም፣ ሌሎችን ከራሳችን የተለዩ አድርገን እንድንቀበል ፣ ሁሉም ሲበዛ በመልካም እንድንፀና የሚያስችለን የመንፈስ ጥንካሬ ነው። የጠፋን ሲመስለን እናም በድካም እና በእንዝላልነት ብሸነፍም እንኳን መሻሻላችን እንደማይቀር በማመን በትዕግስት መጠበቅ ይኖርባንል።

ትዕግሥት ተጨባጭ ሊሆን የሚችልባቸውን ሦስት “መቼቶች” ልጠቁም።

የመጀመሪያው የእኛ የግል ሕይወት ነው። ለጌታ ጥሪ ምላሽ የምንሰጥበት ጊዜ ነበር ፣ እናም በጋለ ስሜት እና በልግስና ሕይወታችንን ለእርሱ አቅርበናል። በሕይወት መንገዳችን ላይ ከመጽናናት ጋር አብሮ ተስፋ መቁረጥ እና ብስጭት እንደ ገጠመን ይታወቃል። አንዳንድ ጊዜ ጠንክረን መስራታችን የተፈለገውን ውጤት ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ ይሆናል። የምንዘራው ዘሮች በቂ ፍሬ የማያፈሩ ይመስላሉ፣ የጸሎታችን ግለት ይቀዘቅዛል እናም እኛ ሁሌም ከመንፈሳዊ ድርቀት ነፃ አይደለንም። የገዳም ሕይወት እንደ ሚኖሩ ወንዶች እና ሴቶች በሕይወታችን ውስጥ ባልተጠበቁ ተስፋዎች ምክንያት ተስፋው ቀስ እያለ እየደበዘዘ ሊመጣ ይችላል። እኛ ለራሳችን ታጋሽ መሆን እና በተስፋው ላይ ለዘላለም ታማኝ ሆኖ ስለሚኖር የእግዚአብሔርን የራሱ ጊዜና ስፍራዎች በተስፋ መጠበቅ አለብን። ይህ የመሠረት ድንጋይ ነው፣ እርሱ ለገባው ቃል ታማኝ ነው፣ የገባውን ቃል ይጠብቃል። ይህንን ማስታወሳችን ውስጣዊ ሀዘን እና ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እርምጃዎቻችንን እንደገና እንድንመለከት እና ህልሞቻችንን እንድናነቃ ይረዳናል። ወንድሞች እና እህቶች ፣ እኛ የገዳም ሕይወት ለምንኖር ወንዶች እና ሴቶች ውስጣዊ ሀዘን እንደ አንድ ትል ነው፣ በውስጣችን ያለውን ተስፋ የሚበላ ትል ነው። ከውስጣዊ ሀዘን መሸሽ ይኖርብናል።

ትዕግስት ተጨባጭ ሊሆን የሚችልበት ሁለተኛው መቼት የህብረተሰብ ኑሮ ነው። ሁላችንም ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነቶች ሁል ጊዜ ሰላማዊ ሊሆኑ አይችሉም፣ በተለይም የሕይወትን እቅድ ወይም የሐዋርያዊ እንቅስቃሴን የምንመለከት ከሆነ። ግጭቶች የሚከሰቱባቸው እና አፋጣኝ መፍትሄ የሚጠበቅባቸው ጊዜዎች አሉ ፣ እንዲሁም ፈጣን የፍርድ ውሳኔዎች መሰጠት ያለብን ጉዳዮችም አሉ። ወደ ኋላ ለመመለስ ፣ ሰላምን ለማስጠበቅ እና በበጎ አድራጎት እና በእውነት ሁኔታዎችን ለመፍታት የተሻለ ጊዜን ለመጠበቅ ጊዜ ያስፈልጋል። በነፋስ ማዕበል እንድንወሰድ መፍቀድ የለብንም። በነገው እለት በምንጸልየው የመዝሙረ ዳዊት ጸሎት ውስጥ ስለ መንፈሳዊ ማስተዋል የሚገልጽ ጥሩ አንቀፅ አለ። እንዲህ ይላል “ጸጥ ያለ ባሕር ዓሳ አጥማጁ እስከ ጥልቁ ድረስ እንዲመለከት ያስችለዋል። ማንም ዓሣ እዚያ ተደብቆ ከዓይኑ ማምለጥ አይችልም። በአውሎ ነፋስ የሚናወጥ  ባህር ግን በነፋሱ በሚናወጥበት ጊዜ ጭጋጋማ ይሆናል”። ልባችን ከተረበሸ እና ትዕግሥት ከሌለው በደንብ ማየት እና እውነትን ለማየት በጭራሽ አንችልም። በጭራሽ! ማህበረሰቦቻችን ይህን የመሰለ የመተጋገሻ ትዕግሥት ይፈልጋሉ-የመደገፍ ችሎታ ፣ ማለትም በራሳችን ትከሻ ላይ የመሸከም ችሎታ ፣ የአንድ ወንድም ወይም የእህቶቻችን ሕይወት፣ የእርሱን ድክመቶች እና ውድቀቶችን ጨምረን መሸከም ይኖርብናል። ጌታ ብቸኛ እንድንሆን እንደማይጠራን ልብ እንበል - በቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፣ እኛ ብቸኛ እንድንሆን አልተጠራንም ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የመዘምራን ቡድን አካል እንድንሆን ፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ በአንድነት ለመዘመር መሞከር አለብን።

በመጨረሻም ሦስተኛው መቼት ከዓለም ጋር ያለን ግንኙነት ነው። ምንም እንኳን ለመፈፀም የዘገየ እና በአለማችን ሀይማኖቶች እና ፍርስራሾች መካከል በዝምታ የሚያድግ ቢሆንም ስምዖንና አና በነቢያት የተናገሩትን ተስፋ ከፍ አድርገው ይመለከቱ ነበር። ነገሮች ምን ያህል የተሳሳቱ እንደሆኑ ቢመለከቱም አላጉረመረሙም ፣ ነገር ግን በታሪክ ጨለማ ውስጥ የሚበራውን ብርሃን በትዕግስት ፈልጉ። በታሪክ ጨለማ ውስጥ የሚበራውን ብርሃን ለመፈለግ በራሳችን ማህበረሰቦች ጨለማ ውስጥ የሚበራ ብርሃን ለመፈለግ በተስፋ መሞላት ይኖርብናል።  በማጉረምረም ወጥመድ ውስጥ ላለመግባት እኛም እንደዚህ ዓይነት ትዕግሥት ያስፈልገናል። አንዳንድ ሰዎች የማጉረምረም አዋቂዎች ፣ የቅሬታ ሐኪሞች ናቸው ፣ በማጉረምረም በጣም ጎበዝ የሆኑ ሰዎች አሉ! የለም ፣ ማጉረምረም እኛን ያሰረን “ዓለም ከእንግዲህ እኛን አትሰማንም” - ምን ያህል ጊዜ እንደዚያ እንሰማለን - - ወይም - “ምንም ተጨማሪ ድምፆች የሉንም ፣ ስለሆነም ቤቱን መዝጋት አለብን” ፣ ወይም “እነዚህ ጊዜዎች ቀላል አይደሉም” አህ ፣ አትንገረኝ! ... ” እያልን እናጉረመርማለን። እናም ስለዚህ የቅሬታዎች አካል ይጀምራል። በታሪክ እና በገዛ ልባችን ውስጥ የሚገኘውን ነገሮች በመመልከት ስለሁሉም ነገር በአስቸኳይ ለመፍረድ ያቃጣናል። በዚህ መንገድ ያንን “ትንሽ” ግን በጣም ቆንጆ የሆኑ በጎነትን እናጣለን-ተስፋችንም ይጨልማል። ትዕግሥት በማጣት ብቻ ተስፋ የሚቆርጡ ብዙ ገዳማዊያን ወንዶችና ሴቶች አይቻለሁ።

ትዕግሥት ለራሳችን ፣ ለማህበረሰባችን እና ለዓለማችን ባለን አመለካከት መሐሪ እንድንሆን ይረዳናል። በገዛ ሕይወታችን የመንፈስ ቅዱስን ትዕግሥት እንቀበላለን? በማኅበረሰባችን ውስጥ እርስ በእርሳችን ታግሰን የወንድማዊ ሕይወት ደስታን እናበራለን? በዓለም ውስጥ አገልግሎታችንን በትዕግስት እናቀርባለን ወይም ከባድ ፍርዶችን እናደርጋለን? በገዳማዊ ሕይወታችን እነዚህ እውነተኛ ተግዳሮቶች ናቸው-ላለፉት ጊዜያት በናፍቆት ውስጥ ተጣብቀን መቆየት ወይም ተመሳሳይ አሮጌ ነገሮችን ወይም የዕለት ተዕለት ቅሬታዎችን መደጋገማችንን መቀጠል አንችልም። አዳዲስ መንገዶችን በመዳሰስ ፣ መጓዝን ለመቀጠል ትዕግሥትና ድፍረት ያስፈልገናል።

የእግዚአብሔርን ትዕግስት እናሰላስል እና የሰምዖንን እና የአናን የታመነ ትዕግስት እንለምን። በእነዚህ ሁለት አረጋውያን ግለሰቦች በምስጋና ቃላቸውም እንዳደረጉት ዓይኖቻችንም እንዲሁ የመዳንን ብርሃን አይተው ያንን ብርሃን ለዓለም ሁሉ እንድናሳይ ይረዳን ዘንድ እንዲረዳን ፀጋውን እንጠይቅ። 

 

02 February 2021, 13:47