ፈልግ

የሳምፖዶሪያ እና የፍሎሬኒትና የእግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ በማደረግ ላይ በነበሩበት ወቅት የሳምፖዶሪያ እና የፍሎሬኒትና የእግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ በማደረግ ላይ በነበሩበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስፖርት "ወደ ሕይወት ፣ ብስለት እና ቅድስና የሚወስድ መንገድ ነው” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣሊያን ግዛት ጄኖቫ በመባል በሚታወቀው አከባቢ ታዋቂ ከሆነው ሳምፖዶሪያ እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንት ፣ አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ስፖርት በአጠቃላይ እና በተለይም እግር ኳስ “የሕይወት ጎዳና ፣ የብስለት እና የቅድስና ጎዳና” ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን እ.አ.አ በ 1946 ዓ.ም በሰሜናዊ ጣሊያናዊቷ ግዛት ጄኖቫ ከተማ ለተመሰረተው የሳምፖዶሪያ እግር ኳስ ቡድን አባላት ሰላምታ ማቅረባቸው ተገልጿል።  “ብቻችሁን ወደ ፊት በጭራሽ ለመሄድ አትችሉም” በማለት በግንኙነቱ ወቅት ያስታወሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ነገር ግን “ሁል ጊዜም እንደ ቡድን” በምትሆኑበት ወቅት በጋራ ወደ ፊት ለመጓዝ ትችላላችሁ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስፖርትን የሚመለከቱ ሁለት ማዕከላዊ ባህሪያትን ጠቁመዋል።

“የመጀመሪያው የስፖርት ባህሪ ስፖርት በተፈጥሮ ሁሉም ነገር በቡድን የሚደረግ መሆኑ ነው። ምርጥ ድሎች የሚገኙት በቡድን ሥራ ነው" በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው እርሳቸው ከመጡበት አገር (አርጄንቲና) እግር ኳስ ብቻውን የሚጫወት ማለትም ለሰው ሳያቃብል ኳሷን ብቻውን ይዞ የሚሮጥ ሰው “ከእራሱ ጋር ብቻ ነው የሚጫወተው” ተብሎ ሰዎች እንደ ሚዘባበቱበት የገለጹ ሲሆን ጨዋታውን ከራሱ ጋር ብቻ የሚጫወት አንድ የእግር ኳስ ተጫዋች ፣ ሌሎች ተጫዋቾችን ከግምት ሳያስገባ ሁሉንም ወደራሱ በመውሰድ “ኳሱን ብቻውን ያጠምዳል” ተብሎ ይሳለቁበት እንደ ነበረ አስታውሰዋል። በምትኩ “ሁሌም በቡድን መስራት አለብን” በቡድን መሥራት መልካም ውጤት ያስገኛል ብለዋል።

ሁለተኛው ነጥብ የአማተር ስፖርቶችን ዝቅ አድጎ አለመመልከት እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም እንቅስቃሴ ውስጥ ለመግባት እና ነገሮችን ለማድረግ ከሚፈልግ ጥሪ የሚመጣ ተግባር ነው ያሉ ሲሆን የአማተር ስፖርቶች መኖራቸው እጅግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ቅዱስነታችው ተናግረዋል።

የሳምፖዶሪያ የእግር ኳስ ፕሬዝዳንት ማሲሞ ፌሬሮ እና የሊጉሪያ ቡድን አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን ስለተቀበሏቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ያመሰገኑ ሲሆን የቡድኑ አርማ ያለበት “ፓፓ ፍራንቼስኮስ” በሚል የተጻፈበት መታሰቢያ ማሊያ በስጦታ እንደ ሰጧቸው ተገልጿል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሳምፖዶሪያ እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንት ፣ አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት
19 February 2021, 19:35