ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እግዚአብሔር በሰብዓዊ ስቃያችን ውስጥ ገብቶ ያድነናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በእለቱ በሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በየካቲት 07/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ባደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እግዚአብሔር በሰብዓዊ ስቃያችን ውስጥ ገብቶ ያድነናል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት ዝቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው ቅዱስ ወንጌ

ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው አነጻ

አንድ ለምጻም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው። ኢየሱስም ለሰውየው በመራራት እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው። እርሱም ወዲያው ከለምጹ ነጻ፤ ከበሽታውም ተፈወሰ።

ኢየሱስም ሰውየውን አጥብቆ በማስጠንቀቅ እንዲህ ሲል አሰናበተው፤ “ለማንም አንድ ነገር እንኳ እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ምስክር እንዲሆናቸው ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለ መንጻትህም ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው። ሰውየው ግን በሄደበት ሁሉ ነገሩን በሰፊው አወራ፣ ወሬውንም አሠራጨ። በዚህ ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማንኛውም ከተማ በግልጽ መግባት አልተቻለውም፤ ከዚህም የተነሣ ከከተማ ውጭ በሚገኙ ሰዋራ ቦታዎች መኖር ጀመረ፤ ሰዎች ግን ከየአቅጣጫው እርሱ ወዳለበት መምጣት አላቋረጡም (Mc 1,40-45)

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 1፡40-45) በኢየሱስ እና በሥጋ ደዌ የታመመ አንድ ሰው መካከል የተደርገውን ግንኙነት ያቀርባል። በለምጽ በሽታ የተያዙ ሰዎች እንደ ርኩስ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፣ በሕጉ መመሪያዎች መሠረት ከሚኖሩበት ሰፈር ውጭ ሳይወጡ እዚያው መቆየት ነበረባቸው። እነሱ ከማንኛውም ሰብዓዊ ፣ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ግንኙነቶች የተገለሉ ነበሩ። በሌላ በኩል ኢየሱስ ወደዚያ ሰው ለመቅረብ ፈቀደ፣ አዘነለት፣ እጁንም ዘርግቶ ይነካዋል። ስለሆነም እሱ የሚያወጀውን የምሥራች ቃል ይገነዘባል - እግዚአብሔር ራሱን ለሕይወታችን ቅርብ አድርጎ ፣ ለቆሰለው የሰው ልጅ አዝኖ ይራራል፣ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ፣ ከሌሎች ጋር እና ከእኛ ከራሳችን ጋር በዝምድና መንፈስ እንዳንኖር የሚያደርገንን ማንኛውንም እንቅፋት ለመስበር ይመጣል። በዚህ ክፍል ውስጥ ሁለት “የተጣሱ ሁኔታዎች” ሲገናኙ እናያለን - ወደ ኢየሱስ የሚቀርበው ለምጽ የያዘው ሰው እና በርኅራኄ ተነሳስቶ እርሱን ለመፈወስ በእጁ የዳሰሰውን ኢየሱስን እንመለከታለን።

የመጀመሪያው መተላለፍ ወይም የተጣሰ ነገር በሥጋ ደዌ የተያዘው ሰው የፈጸመው ጉዳይ ነው-ምንም እንኳን የሕግ እገዳዎች ቢኖሩበትም እርሱ በራሱ ፈቃድ ህግ ጥሶ ተገልሎ ከነበረበት ሥፋር ይወጣል፣ ከኢየሱስ ጋር ይገናኛል። እርሱን የያዘው የለምጽ በሽታ በኃጢያት ምክንያት በተከሰተው እርግማን ምክንያት የተከሰተ የመርገም በሽታ ተደርጎ በወቅቱ የሚቆጠር የነበረ ሲሆን ነገር ግን ኢየሱስ ሌላኛውን የእግዚአብሔርን የፊት ገጽታ ያሳየዋል፣ እግዚአብሔር የሚረግም አባት ሳይሆን ነገር ግን የርህራሄ እና የፍቅር አባት ፣ ከኃጢአት ነፃ የሚያወጣን እና ከምህረቱ ፈጽሞ የማይለየን አምላክ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ ያ ሰው ከነበረበት የተገለ ሕይወት ሊወጣ የቻለበት ምክንያት በኢየሱስ ውስጥ ህመሙን የሚጋራውን እግዚአብሔርን ሊገናኝ ነው። የኢየሱስ አመለካከት ይስበዋል ፣ ከራሱ እንዲወጣ እና አሳማሚውን ታሪኩን በአደራ እንዲሰጥ ይገፋፋዋል።

ሁለተኛው መተላለፍ እየሱስ የፈጸመው ተግባር ነው- ሕጉ በለምጽ በሽታ የተጠቁ ሰዎችን  መንካት የሚከለክል ቢሆንም ቅሉ እርሱ ግን ራራለት፣ እጁንም ዘርግቶ እሱን ለመፈወስ ዳሰሰው። ግንኙነቱ በቃላት ብቻ የተወሰነ አይደለም፣ ነገር ነገር ግን ይነካዋል። በፍቅር መንካት ማለት ግንኙነታቸውን መመስረት ፣ ወደ ህብረት መግባት ፣ ቁስላቸውን እስከ መካፈል ድረስ በሌላው ህይወት ውስጥ መሳተፍ ማለት ነው። በዚህ እንቅስቃሴ ኢየሱስ “በአስተማማኝ ርቀት” ላይ ሆኖ የሚጠብቀን እግዚአብሔር እንደሌለ ያሳየናል። በእርግጥ እሱ በርህራሄ ይቀርባል እናም እሱ እኛን ለመፈወስ ሕይወታችንን ይነካል።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች በአለም ውስጥ እንኳን ዛሬ ብዙ ወንድሞቻችን በዚህ በሽታ ይሰቃያሉ ፣ ወይም በሚያሳዝን ሁኔታ ማህበራዊ ጭፍን ጥላቻ በሚዛመዱባቸው ሌሎች በሽታዎች እና ሁኔታዎች ውስጥ ገብተው የሚሰቃዩ ብዙ ሰዎች አሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎችም እንዲሁ የሃይማኖት አድሎ አለ። ነገር ግን እያንዳንዳችን ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ለሌሎች የሚያቀርበን ቁስሎች ፣ ውድቀቶች ፣ መከራዎች ፣ ራስ ወዳድነት ሊያጋጥመን ይችላል። በዚህ ሁሉ ፊት ኢየሱስ ረቂቅ ሀሳብ ወይም አስተምህሮ አለመሆኑን ፣ ነገር ግን በቆሰለ ሰብአዊነታችን ላይ ያሉትን ቁስሎች በመንካት ራሱን “የሚበክል” እና ከቁስሎቻችን ጋር መገናኘት የማይፈራ መሆኑን ነው።፡

መልካም ስምአችንን ለመጠበቅ ስንል ህጎችን እና ማህበራዊ ልምዶችን ለማክበር ብዙውን ጊዜ ህመሙን ዝም እንላለን ወይም ይህን የሚያስመስሉ ጭምብሎችን እናደርጋለን። የራስ ወዳድነታችንን ስሌቶች ወይም የፍርሃታችን ውስጣዊ ህጎች ሚዛናዊ ለማድረግ በሌሎች ስቃይ ውስጥ አንገባም። በምትኩ እነዚህን ሁለቱን የወንጌል “መተላለፎች” በሕይወት ለመኖር ጸጋውን እንዲሰጠን ጌታን እንለምን። ያ የሥጋ ደዌው ፣ ከተለየነው ለመውጣት ድፍረቱ ስላለን እና እዚያ ለመኖር ወይም በውድቀታችን ለማዘን ወይም ከማዘን ይልቅ ፣ እኛ እንዳለን ወደ ኢየሱስ እንሄዳለን።፡ እናም ከዚያ የኢየሱስ መተላለፍ - ከስምምነቶች ባሻገር እንድንሄድ የሚያደርገን ፣ ጭፍን ጥላቻን እና ከሌላው ህይወት ጋር የመደባለቅ ፍርሃትን የሚያሸንፍ ፍቅር እርሱ ይሰጠናል።

በእዚህ ዓይነት መንገድ ላይ መጓዝ እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁላችንንም በአማላጅነቷ ትርዳን።

14 February 2021, 12:42