ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሴቶች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የኃይል ጥቃት መከላከል ይገባል አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ለጥር ወር 2013 ዓ.ም እንዲሆን በማለት ቅዱስነታቸው ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ የተለያየ ዓይነት የኃይል ጥቃት እይደረሰባቸው ለሚገኙ ሴቶች ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው በቅርቡ በቪዲዮ ይፋ ባደረጉት መልእክት የሚከተለውን መናገራቸው ተገልጿል፣ እንዲህም ብለዋል. . .

በዛሬው ጊዜ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች መኖራቸው ቀጥሏል ፡፡ የስነ-ልቦና ጥቃት ፣ የቃላት ጥቃት ፣ አካላዊ ጥቃት ፣ ወሲባዊ ጥቃት።

ብዙ ሴቶች እንደ ሚደፈሩ፣ እንደ ሚደበደቡ፣ እንደ ሚሰደቡ እና እንደ ሚደፈሩ መስማት  ያስደነግጣል። ብዙ ሴቶች የሚደርስባቸው የተለያዩ ዓይነት የግፍ አያያዝ ዓይነቶች ሴቶች እንዲፈሩ የሚያደርጉ ድርጊቶች እና የሰው ልጆች ሁሉ ዝቅ ተደርገው እንዲታዩ የሚያደርግ ነው። ይህም የሰዎችን እና የሰው ልጆች ሁሉ የሚነካ ተግባር ነው።

ዝምታቸውን ለመስበር የደፈሩ የተጎጂዎች ምስክርነት ችላ ማለት የማንችለው የእርዳታ ጩኸቶች ናቸው።

ይህንን በተቃራኒው መመልከት የለብንም፡፡

የአመፅ ድርጊቶች ሰለባ የሆኑ ሴቶች በኅብረተሰብ እንዲጠበቁ እና ሁሉም ሰዎች ስቃዮቻቸውን እንዲጋሩ እና ስቃዮቻቸውን እንዲያስቡ እንጸልይ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የኃይል ጥቃት አስመልክቶ “እኛ ይህንን ተግባር ችላ ማለት አንችልም” በማለት ለየካቲት ወር 2013 ዓ.ም ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ላይ የተናገሩ ሲሆን ቅዱስነታቸው የካቲት ወር 2013 ዓ.ም የጸሎት ሐሳብ ይሆን ዘንድ በቪዲዮ ባቀረቡት መልእክት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የተለያዩ የኃይል ጥቃቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የሚገልጽ መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል። ቅዱስ አባታችን በዚህ “የሰው ልጅ ሁሉ ዝቅጠት” ፊት ለፊት ሴቶች በኅብረተሰቡ እንዲጠበቁ እና የሚደርስባቸው ሥቃይ ሁሉም የሰው ልጆች እንድገነዘቡ ጥሪ አቅረበዋል።

ሴቶች ፣ የጥቃት ሰለባዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእዚህ ለየካቲት ወር ይሆን ዘንድ ቪዲዮ ባስተላለፉት የጸሎት ሐሳብ በጠቅላላው በዓለም አቀፍ የፀሎት አውታረመረብ በኩል በሊቀ ጳጳሱ አማካይነት ለካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ በአደራ ያስተላለፉት የጸሎት ሐሳብ ነው። በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች የሚገጥማቸውን ጥቃት የሚቃወም ኃይለኛ መልእክት ነው ፣ “ሥነ ልቦናዊ ጥቃት ፣ የቃላት ጥቃት ፣ አካላዊ ጥቃት ፣ ወሲባዊ ጥቃት” ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እነዚህ በደሎች “ሴቶች እንዲፈሩ የሚያደርጉ ድርጊቶች እና የሰው ልጆችን ሁሉ የሚያዋርድ ተግባራት” ናቸው በማለት በአጽኖት ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ ለተጎጂዎች እንድንጸልይ ይጠይቁናል “በኅብረተሰቡ እንዲጠበቁ እና የደረሰባቸውን ሥቃይ ሁሉም እንዲገነዘብላቸው እና ሊያዳምጣቸው” ይገባል በማለት ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅረበዋል።

ለየካቲት ወር ይሆን ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት የዚህ አሰቃቂ ጉዳይ ድራማ በተንቀሳቃሽ የካርቶን በምስሎችም እንዲሁ በትረካ እንዲታይ ለማድረግ ያለመ ሲሆን  ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘ እና የካርቶን ምስሎች ዲዛይነር የሆነው ፕሮፌሰር ሄርሜስ ማንጊያላርዶ ትብብር ምስጋና ይግባውና ቪዲዮው በካርቱን ስዕሎች አማካይነት የዓመፅ ሰለባ የሆነች አንዲት ሴት ታሪክ በማቅረብ ይህንን አስቸጋሪ የሆነ የገጠማትን ጥቃት ለማሸነፍ በድፍረት የምታደርገውን እንቅስቃሴ የሚወክሉ ታሪኮች የተገለጹበት ሲሆን በራሷ ጥንካሬ እና በማህበረሰቡ እገዛ ምክንያት ከጥቃት ነጻ ወጥታ ሕይወቷን በአዲስ መልክ እንደ ጀመረች ይተርካል።

በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በአኃዝ ሲገለጽ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለየካቲት ወር ይሆን ዘንድ በቪዲዮ ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ላይ እንደ ገለጹት “ብዙ ሴቶች መደብደባቸው ፣ መሰደባቸው እና መደፈራቸውን መስማት በራሱ ያስደነግጣል” ማለታቸውን ቀድም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን በእርግጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ የተሰበሰቡት አኃዛዊ መረጃዎች እ.ኤ.አ. በሕዳር 2020 ዓ.ም ባወጣው አኃዛዊ መረጃዎች የጉዳዩን አስደንጋጭነት አጉልቶ ያሳያል። በየቀኑ 137 ሴቶች በገዛ ቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ። በዓለም ዙሪያ ከሚታወቁ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ከሆኑት መካከል ግማሽ ያህሉ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። እናም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሶስት ሴቶች አንዷ በተወሰነ ጊዜ የአካል ወይም የወሲብ ጥቃት ደርሶባቸዋል (በዓለም ዙሪያ ከ 15 እስከ 19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው 15 ሚሊዮን ጎረማሳ ሴቶች አስገዳጅ ወሲባዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል)። ከዚህም በላይ ባለፈው ዓመት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ በፈጠረው አስከፊ ሁኔታ ይህ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በመጠን እና በቁጥር መጨመሩ ይታወሳል - የእንቅስቃሴ መገደብ፣ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና በኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች አለመተማመን ሴቶችን በአለም አቀፍ ደረጃ በግለሰቦች አካባቢ ለሚፈጠሩ ጥቃቶች የበለጠ ተጋላጭ አድርጓቸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለየካቲት ወር ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ እነዚህን ተጎጂዎች እንዲጠብቅ ህብረተሰቡን ይጠይቃሉ። ምንም እንኳን ቢያንስ 155 ሀገሮች የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚከላከሉ ህጎችን ያፀደቁ እና 140 አገራት ደግሞ በሥራ ቦታ ውስጥ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ትንኮሳ በተመለከተ ሕግ ቢኖራቸውም (እነዚህን ሁለት ምስላኤዎች ለመጥቀስ ያህል) ይህ ማለት ግን እነዚህ ህጎች ሁል ጊዜ ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና የውሳኔ ሃሳቦችን አያሟሉም ፣ አይተገበሩም ፣ ተፈጻሚም አይደሉም ማለት ግን አይደለም ፡፡

ጉዳዩን በሌላ መንገድ መመልከት አይገባም

ይህንን ዓላማ አስመልክቶ የሊቀ ጳጳሱ ዓለም አቀፍ የጸሎት ኔትወርክ ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል ይሆኑት አባ ፍሬድሪክ ፎርኖስ የሚከተለውን አስተያየት አስጠዋል “የቅዱስ አባታችን ጥሪ በጣም ግልፅ ነው” ነገሩን በሌላ አቅጣጫ መመልከት የለብንም። በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃቶችን ለማውገዝ ክንዳችንን አንስተን ሴቶችን ከጥቃት መከላከል ይገባናል ማለት ብቻ ሳይሆን በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ብዙ የኃይል ጥቃቶችን በሚመለከት ከእዚህ ባሻገር በመሄድ ይህም ከሚታዩ እና ከሚወገዙ ተግባራት አንስቶ ስለሁኔታው ሰዎች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በሁሉም ሁኔታዎች ሴቶችን ዝቅ የሚያደርጉ ሥር የሰደዱ የአእምሮ ማዕቀፎች እና ባህላዊ እና ማህበራዊ ምሳሌዎች ውጤቶች ይሆኑ ጥቃቶች በመሆናቸውም ጭምር ይህንን ሐስተሳበ የሚቀይሩ ተግባራትን ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን አክለው ገልጸዋል። በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ስታመነዝር የተያዘችው ሴት የተመለከተ ምንባብ ውስጥ የምናየው ይህንኑ የሚያሳይ ተግባር ነው ፣ ለምሳሌ ይህች ስታመነዝር የተገኘችው ሴት በሁሉም ተከሳለች ፣ ኢየሱስ ግን አዲስ ሕይወት ሰጣት (ዮሐ 8 2-11) ፡፡ በማንኛውም መልኩ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃቶች ወደ ሰማይ ይጮኻል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን ደጋግመው መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን ‘በሴቶች ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥቃት ከሴት የተወለደውን እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። የሰው ልጅ መዳን የወጣው ከሴት አካል ነው-የሴትን አካል በምንይዝበት መንገድ የሰውን ልጆችን ደረጃ መገንዘብ እንችላለን” በማለት የሊቀ ጳጳሱ ዓለም አቀፍ የጸሎት ኔትወርክ ዓለም አቀፍ ዳይሬክተር የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል ይሆኑት አባ ፍሬድሪክ ፎርኖስ አክለው ገልጸዋል።

ልጆችን እና ጎረምሳ ሴቶችን ጨምሮ የኃይል ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ሁሉ በጋራ እንጸልይ፣ እንዲሁም እነሱን የሚጠብቃቸው፣ የሚያዳምጣቸው እና ስቃያቸው ይቃለል ዘንድ የሚረዳ ፍትሃዊ ህብረተሰብ ይገነባ ዘንድ እንታገል፣ እንጸልይ።

06 February 2021, 11:15