ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስርዓተ አምልኮ እና ጸሎት ከክርስቶስ ጋር ሕብረት እንዲኖረን ያደረገናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን የጠቃላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደረጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት በጥር 26/2013 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በጸሎት ዙሪያ ላይ ጀምረውት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ስርዓተ አምልኮ መሳተፍ እና አዘውትሮ መጸለይ ከክርስቶስ ጋር ያለን ሕብረት እንዲጠነክር ያደረገናል ማለታቸው ተዘግቧል።

የእዚህ ዝግጅት አቃራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን ከረማችሁ!

በቤተክርስቲያኗ ታሪክ ውስጥ ይፋዊ በሆነ መልኩ የሚደረጉ የስርዓተ አምልኮ ሥርዓቶችን መንፈሳዊ አስፈላጊነት የማይቀበል ለእዚህ መንፈስ ቅርብ የሆነ ክርስትናን ለመለማመድ ብዙ ጊዜ ፈተናዎች ነበሩ። ብዙውን ጊዜ ይህ ዝንባሌ የእዚህ ዓይነቱ መንፍሳዊ የስነ አምልኮ ስርዓት ምንም ፋይዳ የለውም ወይም ጎጂ የሆኑ ሸክሞች ተደርገው የሚታዩ ሲሆን ውጫዊ የሆኑ ሥነ ሥርዓቶች ላይ የማይመሠረት ሃይማኖታዊነት የበለጠ ንፅህና እንዳለው ይናገራሉ። የትችቱ ማዕከል የተለየ ሥነ-ሥርዓት ወይም የተለየ የማክበር መንገድ አልነበረም ፣ ግን ይልቁንም ሥነ-ሥርዓቱ ራሱ ፣ የጸሎት ሥርዓተ አምልኮ ዓይነት አልነበረም በማለት ይሞግቱ ነበር።

በእርግጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ የአምልኮ ሥርዓትን በበቂ ሁኔታ ማዋሃድ ያቃታቸው የተወሰኑ መንፈሳዊ ዓይነቶችን ማግኘት ይችላል። ብዙዎች ምእመናን ምንም እንኳን በምስዋዕተ ቅዳሴ ውስጥ በተለይም በእሑድ ቅዳሴ ላይ ቢሳተፉም ይልቁንም ለእምነት እና ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከሌሎች መለኮታዊ ምንጮች ጸጋዎችን መመገብ ችለዋል።

ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ ብዙ ነገሮች ተከናውነዋል። የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ መነፍሳዊ ምስጢራትን በተመለከተ በዚህ ረዥም ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ነጥብ አስቀምጧል። እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሀሳብ ወይም ስሜት ሳይሆን ህያው የሆነ አካል እና በታሪክ ሂደት ውስጥ  ምስጢራዊ የሆነ ክስተት መሆኑን የሚጠይቅ እውነተኛ አማላጅነትን የሚያገኙበት መለኮታዊው ሥነ-ስርዓት ለክርስቲያኖች ሕይወት በጥልቀት እና በትክክል አስፈላጊ እንደ ሆነ ያረጋግጣል። የክርስቲያኖች ጸሎት ተጨባጭ በሆነ መልኩ በሚገለጽ አማላጅነት ውስጥ ይተላለፋል፣ እነዚህም ቅዱሳን በሆኑ መጽሐፍት፣ በቅዱሳን ምስጢራት፣ በስርዓተ አምልኮ ስርዓቶች በጋራ በሚደረጉ ጸሎቶች ውስጥ የተላለፋል። በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ አካላዊ እና ቁሳዊው የሆኑ ነገሮች ሊወገዱ ወይም ችላ ሊባሉ አይችሉም፣ ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ የመዳን መንገድ ሆነዋልና። እኛም ከሰውነት ጋር መጸለይ አለብን ማለት እንችላለን ሰውነት ወደ ጸሎት መንፈስ ውስጥ ይገባል።

ስለዚህ በቅዱሳን ምስጢራት አከባበር ላይ ያልተመሰረተ ክርስቲያናዊ መንፈሳዊነት የለም ፡፡ ይህንን በተመለከተ ደግሞ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ሲገልጽ እንዲህ ይላል “የክርስቶስ እና የመንፈስ ቅዱስ ተልእኮ በሚጸልይ ልብ ውስጥ የሚቀጥለውን የመዳንን ምስጢር ያውጃል ፣ ያቀርባል ፣ እንዲሁም ያስተላልፋል” (2655)። የአምልኮ ሥርዓቱ በራሱ ራሱን የቻለ ቃጣይነት ያለው ጸሎት ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን የበለጠ እና የበለጠ እውነተኛ የሆነ ነገር ነው -እሱ ሁሉንም ክርስቲያናዊ ልምድን ያካተተ ፀሎትን መሠረት ያደረገ ተግባር ነው። እሱ ክስተት ነው ፣ እየሆነ ያለ ነገር ነው ፣ ግንኙነት የመፍጠሪያ መሳሪያ ነው። ከክርስቶስ ጋር መገናኘት ነው ፡፡ ክርስቶስ በቅዱሳን ምስጢራት አማካይነት በሚተላለፉ ምልክቶች አማካኝነት ራሱን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ሕያው አድርጎ ያቀርበዋል - ስለሆነም እኛ ክርስቲያኖች በመለኮታዊ ምስጢሮች ውስጥ የመሳተፍ አስፈላጊነትን በሚገባ እንገነዘባለን። ያለ ስርዓተ አምልኮ የሚተገበር ክርስትና ለማለት እደፍራለሁ ፣ ምናልባት ክርስቶስ የሌለበት ክርስትና ነው። ሙሉ በሙሉ ክርስቶስ የሌለበት ክርስትና ነው። እጅግ በጣም አናሳ በሆነው የአምልኮ ሥርዓት ውስጥ እንኳን አንዳንድ ክርስቲያኖች በእስር ላይ ባሉባቸው ስፍራዎች ውስጥ የፈጸሙትን እና እየፈተጸሙ የሚገኙትን የአምልኮ ስርዓቶች ወይም በስደት ጊዜ በሚያገኟቸው ስፍራዎች ውስጥ የሚፈጽሟቸው ስርዓተ አምልኮዎች ውስጥ ክርስቶስ በእውነት ተገኝቶ እራሱን ለምዕመናኑ ያቀርባል።

ሥርዓተ አምልኮ በትክክል ከዓላማው ስፋት የተነሳ በቅንዓት እንዲከበሩ የሚጠይቅ ሲሆን ስለዚህ በአምልኮው ውስጥ የፈሰሰው ጸጋ እንዳይበተን ይልቁንም ለሁሉም ፀጋው በትክክል ተደራሽ እንዲሆን የሚጠይቅ ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ይህንን በተመለከተ በሚገባ ያብራራል እንዲህም በማለት ይናገራል “ጸሎት በሚደረግበት ወቅት  በኋላም ሥርዓተ አምልኮን ውስጡን ያጠናክረዋል እንዲሁም ያዋህዳል” (2655)። ብዙ የክርስቲያን ጸሎቶች ከስርዓተ አምልኮ የሚመነጩ አይደሉም፣ ነገር ግን ሁሉም ክርስቲያኖች በቅዱሳን ምስጢራት አማካይነት ከሚያማልደው ከክርስቶስ ውስጥ ይመነጫሉ።  ምስጢረ ጥምቀትን በምንሳትፍበት ጊዜያት ሁሉ ወይም በቅዱስ ቁርባን ውስጥ እንጀራውን እና የወይን ጠጁን በምንባርክበት ወቅት፣ ወይም የታመመ ሰው አካል ቅዱስ በሆነ ዘይት በተቀባ ቁጥር፣ ክርስቶስ እዚያ አለ! የታመመ ሰው ደካማ አካላትን ሲፈውስ ወይም በመጨረሻው እራት ላይ ዓለምን ለማዳን ቃል እንደ ገባ ሁሉ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባንን ስንሳተፍ እርሱ በእዚያ የሚኖረው ሥራውን የሚሰራው እርሱ ክርስቶስ ነው።

የክርስቲያን ጸሎት ኢየሱስን በቅዱሳን ምስጢራቱ አማካይነት በመገኘት የራሱ ያደርገዋል። ለኛ ውጫዊ የሆነው ነገር የእኛ አካል ይሆናል -የቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱ ይህንን የሚገልፀው በመመገብ ሲሆን ይህም በጣም ተፈጥሯዊ የሆነ መልክት ነው። መስዋዕተ ቅዳሴን እንዲሁ በቀላሉ “ሊደመጥ” የሚችል ጉዳይ ብቻ አይደለም፣ እንዲሁም “መስዋዕተ ቅዳሴን ለመስማት እየሄድኩኝ ነው” ማለት በራሱ የተሳሳተ አገላለጽ ነው። መስዋዕተ ቅዳሴ ያለ እኛ ተሳትፎ የሚከናወን፣ እኛም እንደ አንድ ተመልካች ብቻ ሆነን ቆመን የምንሰማው ነገር በቀላሉ ሊደመጥ የሚችል ነገር አይደለም። መስዋዕተ ቅዳሴ ሁሌም ይደረጋል፣ እናም እሱ በሚያከናውነው ካህን አማካይነት ብቻ ሳይሆን መስዋዕተ ቅዳሴውን በሚካፈሉ ክርስቲያኖች ሁሉ አማካይነት የሚከናወን ነው። እናም ማዕከሉ ክርስቶስ ነው! ሁላችንም ካለን የተለያዩ ስጦታዎች እና የአገልግሎት መክሊት በመነሳት የእርሱን ሥራ የምንቀላቀል ሲሆን ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስ ራሱ የስርዓተ አምልኮዋችን ዋነኛው ተዋናይ ነው።

የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ማምለክ ሲጀምሩ የኢየሱስን ድርጊቶች እና ቃላቶች በመንፈስ ቅዱስ ብርሀን እና ኃይል በተግባር በማሳየት ያከናወኑ ስለነበሩ ህይወታቸው በዚያ ጸጋ የተደረሰው ለእግዚአብሄር የሚቀርብ መንፈሳዊ መስዋእት ይሆን ዘንድ ነው። ይህ አካሄድ እውነተኛ “አብዮት” ነበር። ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኮአችሁ” (12 ፡1) ) ይለናል። ሕይወት ለእግዚአብሄር አምልኮ ይውል ዘንድ ተጠርቷል ፣ ነገር ግን ይህ ያለ ጸሎት ፣ በተለይም ያለ ስርዓተ አምልኮ ጸሎት እውን ሊሆን አይችልም። ይህ አገላለጽ ወይም አስተሳሰብ ወደ መስዋዕተ ቅዳሴ በእዚህ መንፈስ እንሄድ ዘንድ ይርዳን፣ ወደ መስዋዕተ ቅዳሴ የሚሄደው ከማሕበርሰቡ ጋር አብሬ ለመጸለይ ነው፣ እዚያው ከሚገኘው ከክርስቶስ ጋር ለመገነት ነው የምሄደው ብለን ማሰብ እንችል ዘንድ ይርዳን። ለምሳሌ ያህል የምስጢረ ጥምቀት ስነ ስርዓት በምንታደምበት ወቅት  እዚያ ያለው፣ እዚያ የሚገኘው የሚያጠምቀው እራሱ ክርስቶስ ነው። “ነገር ግን አባ ይህ ሀሳብ ፣ የንግግር ዘይቤ ነው” ልትሉኝ ትችሉ ይሆናል፣ በፍጹም እንዲህ አይደለም፣ እሱ የንግግር ዘይቤ አይደለም። ክርስቶስ በእዚያ ስፍራ ይገኛል። በስርዓተ አምልኮ ወቅት በአጠግባችን ሆኖ የሚጸልየው ክርስቶስ ራሱ ነው።

03 February 2021, 20:10

በቅርብ ጊዜ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የተደረገው ግንኙነት

ሁሉንም ያንብቡ >