ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ዐብይ ጾም ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበት ወቅት ነው” አሉ!

በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር መሰረት የላቲን ሥርዐተ አምልኮ በምትከተለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሥርዐተ አምልኮ ደንብ የዐብይ ጾም ረቡዕ እለት የካቲት 10/2013 ዓ.ም ላይ ግንባርን በዐመድ የመቀባት ስርዓት ከተደረገ በኋላ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ይህም ለመጪዎቹ አርባ ቀናት በጸሎት፣ በጾም እና ምጽዋዕት በመስጠት የሚፈጸመው ጾም እግዚኣብሔርን የሚያስደስት ጾም ይሆን ዘንድ፣ ለጿሚው ሰው ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋ የሚያስገኝለት ጾም ይሆን ዘንድ፣ እንዲሁም የፋሲካን በዓል ዋና ትርጉሙን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ይቻል ዘንድ መንፈሳዊ ዝግጅት የሚደረግበት ወቅት ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህ የዐብይ ጾም በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ የዐመድ መቀባት መንፈሳዊ ስነ ስርዓት በተከናወነበት ወቅት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት  ክርስቲያኖች የአብይ ጾምን ወቅት ወደ አብ ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የሚያደርስ መንገድ በመሆኑ የተነሳ በእዚህ ጎዳና ላይ እንዲመላለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ቤተክርስቲያን የዐብይ ጾምን ቅዱስ ወቅት እንደጀመረች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የገለጹ ሲሆን ይህንን የዐብይ ጽሞ ወቅት በዐመድ የመቀባት ስነ ስርዓት በማከናወን በይፍ እንዲጀመር ማደረጋቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዐብይ ጾም ወደ እግዚአብሔር የመመለስ ጉዞ እና ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ያለንን ፍቅር ለማጠንከር የሚረዳን ወቅት ነው ብለዋል። እግዚአብሄር ወደ ልባችን ይገባ ዘንድ ጥሪ የምናቀርብበት ወቅት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም መሰረት ቸሩ እግዚአብሔር መላውን ማንነታችንን እዲመራው ወደ ልባችን ይገባ ዘንድ ልንጋብዘው የገባል ብለዋል።

ወደ ዘላለም ቤታችን የሚወስደንን መስመር ለመፈለግ እና ሁሉም ነገር ከሚተማመንበት ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ጥልቅ ግንኙነት እንደገና የምናገኝበት ወቅት እንደ ሆነ በመግልጸ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር ምህረት እንዲያደርግልን የምንማጸንበት ወቅት ነው ብለዋል።

ከባርነት ወደ ነፃነት

ክርስቲያኖች ህይወታችን የሚመራበትን አቅጣጫ እና ወደ እግዚአብሔር ለምድረስ በምንወስደው መንገድ ላይ ምን ያህል በፅናት እንደምንጓዝ እንዲገመግሙ አሳስቧል። “የዐብይ ጾም ከባርነት ወደ ነፃነት የሚደረግ ጉዞ ነው” ብለዋል። እያደግን ስንሄድ ወደ ቀድሞ ልምዶቻችን እና ቅዤቶቻችን የመመለስ ፈተና ይሰማናል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ነገር ግን የቱንም ያህል ጊዜ መሰናክሎች ብያጋጥሙንም የእግዚአብሔርን ቃል በመመልከት መንገዳችንን እንደገና ማወቅ እንችላለን ብለዋል።

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዐብይ ጾም የመጀመሪያ እርምጃ በእምነት ምስጢረ ንስሐን በማደረግ  የእግዚአብሔርን ይቅርታ በመቀበል ወደ አብ መመለስን ያካትታል ያሉ ሲሆን “ሁል ጊዜ በእግራችን እንድንቆም የሚያደርገን የአባታችን የእግዚአብሔር ይቅርታ ነው” ብለዋል።

በመቀጠልም ወደ ኢየሱስ መመለስ ያስፈልገናል በማለት የተናገሩት ቅዱስነታቸው ልክ ፈውስ እንዳገኘው እና እርሱን ለማመስገን ተመልሶ እንደ መጣው ለምጻሙ ሰው እርሱን ለማመስገን እንደተመለሰ ሁሉ እኛም ​​ “የኢየሱስ ፈውስ ያስፈልገናል፣ ቁስሎቻችንን ለእሱ ማቅረብ እና እንዲህ ማለት አለብን ‘ኢየሱስ ፣ እኔ በአንተ ፊት ፣ ከኃጢአቴ ፣ ከሐዘኔ ጋር ነኝ። አንተ ሀኪም ነህ፣ ነፃ ልታወጣኝ ትችላለህ፣ ልቤን ፈውስልኝ ’” ልንለው ይገባል ብለዋል።

ወደ መነፍስ ቅዱስ መመለስ ይኖርብናል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ በእዚህ አሁን በጀመርነው የዐብይ ጾም ወቅት ወደ መንፈስ ቅዱስ እንድንመለስ የጋበዙን ሲሆን በጭንቅላታችን ላይ የተረጨው አመድ እኛ አፈር እንደሆንን ያስታውሰናል፣ “ሆኖም በዚህ አፈር በሆነው ማንነታችን ላይ እግዚአብሔር የሕይወትን እስትንፋስ የሰጠናል” ብለዋል።

ከልብ የመነጨ እርቅ ማድረግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ ወደ እግዚአብሔር የምንመለስበት ጉዞ ሊሳካ የሚችለው “እርሱ በመጀመሪያ ወደ እኛ ስለሚመጣ” ብቻ መሆኑን ልብ ማለት እንደ ሚገባ የገለጹ ሲሆን ኢየሱስ ኃጢአታችንን እና ሞታችንን ስለተቀበለ “እንግዲያውስ በጉዞዋችን እሱ እጆቻችንን ይዞ እንዲመራን” ልንፈቅድለት የጋብል ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእግዚአብሄር ግብዣ የሰጠነው ምላሽ ከልብ እርቀ ሰላምን “ከሚገልጹት ድርጊቶች እና ልምዶች ጋር” እንደ ሚካተት አክለው ተናግረዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአብይ ጾም ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የምንጓዝበት ትክክለኛ ጊዜ መሆኑን ያስገነዘቡ ሲሆን “ዐብይ ጾም ወደ ውስጣችን ሆነ ወደ ሌሎች በትህትና የምንመለስበት ወቅት ነው” ብለዋል። መዳን ማለት በክብር መውጣት ሳይሆን ፣ የፍቅር መውረድ መሆኑን መገንዘብ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው የቱንም ያህል ጊዜ ብንደናቀፍ ፣ ሁል ጊዜ ወደ ክርስቶስ መስቀል ዞረን የራሳችንን ጉድለቶች እና ባዶነት በእሱ ቁስሎች ላይ ማሰላሰል እንችላለን ብለዋል።

“እነዚያን የኢየሱስን ቁስሎች በመሳም ፣ እዛ በሕይወት ውስጥ በጣም በሚያሠቃዩ ቁስሎች ውስጥ እግዚአብሔር በማያልቅ ምህረቱ እንደሚጠብቀን እንገነዘባለን” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

18 February 2021, 12:22