ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በእዚህ ጥር ወር የወንድማማችነት አገልግሎት እንዲጠናከር እንጸልይ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ ይፋ በማደረግ ምዕመኑ በጸሎት እንዲሳተፍ ጥሪ እንደ ሚያቀርቡ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለእዚህ ለያዝነው የጥር ወር 2013 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ በመላው ዓለም የወንድማማችነት አገልግሎት ይጠናከር ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን በሰው ልጅ ወንድማማችነት ላይ ያተኮረውን የፀሎት ሐሳባቸውን ይፋ በማደረግ የተለያዩ ሃይማኖቶች ፣ ባህሎች ፣ ወጎች እና እምነቶች ወደ አስፈላጊው ማለትም ለባልንጀራዎቻችን ማሳየት ወደ ሚገባን ፍቅር ሕዝቡ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለእዚህ ለጥር ወር 2013 ዓ.ም ይሆን ዘንድ ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ባለፈው ማክሰኞ እለት በቪዲዮ የተለቀቀ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመን በሊቀ ጳጳሱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ (የቅዱስ ቁርባን የወጣቶች ንቅናቄን - በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል EYM ) በኩል ይፋ እንደ ሆነ ተገልጿል።

እ.ኤ.አ. 2021ዓ.ም አዲስ አመት በተጀመረበት ወቅት ይህንን አዲስ አመት ለመክፈት የተመረጠው መልእክት ለሰው ልጆች ወንድማማችነት ትኩረት የሰጠ መልእክ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን በሰው ልጆች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ምላሽ ለመስጠት እንችል ዘንድ በማሰብ ቅዱስነታቸው እራሳችንን ለሌሎች እንድንከፍት እና እንደ ሰው እና እንደ ወንድም እና እህት አንድ እንድንሆን በመልእክታቸው የጠየቁ ሲሆን እንደ ባሕሎቻችን፣ ወጎቻችን እና እምነቶቻችን ጸሎት ማድረግ ይኖርብናል ማለታቸው ይታወሳል።

በሌሎች አጋጣሚዎች ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ እንደተናገሩት “አማራጭ የለንም ወይ የወደፊቱን በጋራ አብረን እንገነባለን ወይም የጋራ የሆነ የወደፊት ጊዜ አይኖርም ፡፡ በተለይም ሃይማኖቶች በሕዝቦች እና ባህሎች መካከል ድልድዮችን የመገንባት ኃላፊነታቸውን እና አጣዳፊ ተግባራቸውን ችላ ማለት አይችሉም ” ማለታቸው ይታወሳል።

የአንድ አባት ልጆች ነን

በሊቀ ጳጳሱ ቪዲዮ የቀረበው ወደ ወንድማማችነት የሚወስደው መንገድ የሚጀምረው “አንድ የሆነውን አባታችንን በሌላው ወንድም ወይም እህት” ውስጥ በማየት ነው በማለት የገለጹ ሲሆን እርሳቸው በቅርቡ “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚል አርዕስት ቀደም ሲል ይፋ ባደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት ውስጥ ይህንን ሀሳብ በስፊው ማራመዳቸው የሚታወስ ሲሆን  “እኛ ወላጅ አልባ የሆንን ልጆች አይደለንም ፣ ነገር ግን አንድ አባት ልጆች መሆናችንን  በመገንዘብ ብቻ እኛ ከሌላው ሰው ጋር በሰላም መኖር የምንችል መሆናችንን እርግጠኛ ነን” በማለት ለሊቀ ጳጳሱ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ልዩነቶች የተለያዩ ሃይማኖቶች ከምያምኑት እምነት ወይም ከሌሎች ባህሎች ጋር በሚኖሩ ሰዎች መካከል የመገናኘት ባህልን ለማሳካት እንቅፋት መሆን የለበትም፣ ምክንያቱም ከሁሉም በላይ “እኛ የምንጸልይ ወንድሞች እና እህቶች ነን” ማለታቸው ይታወሳል።

የእምነታችን መሰረተታዊ ነገር

ይህንን የወንድማማችነት መንፈስ ለማደስ ይችላ ዘንድ አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለክርስቲያኖች “የሰው ልጅ ክብርና የወንድማማችነት ምንጭ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ እንዳለ” መዘንጋት የለብንም ብለዋል ፡፡ ከዚህ አንፃር አማኞችን ለእምነታችን አስፈላጊ የሆነውን “እግዚአብሔርን ማምለክ እና ባልንጀራን ወደ ማፍቀር” እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንዲሁ በጣሊያነኛ ቋንቋ “Fratelli tutti” (ፍራቴሊ ቱቲ) በአምርኛው ሁላችንም ወንድማማቾች ነን በተሰኘው ጳጳሳዊ መልእክት ውስጥ አክለው  እንደገለጹት ከሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ጋር በሚደረግ ውይይት ይህ መሠረታዊ ነገር ይሆናል ፣ ምክንያቱም ሌሎች ከሌላ ምንጮች ሊጠጡ ቢችሉም “እኛ ለክርስቲያኖች የሰው ልጅ ክብር እና የወንድማማችነት ምንጭ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ነው” በማለት አብክረው መናገራቸው ይታወሳል።

የጥር ወር የጸሎት ሐሳብ በሰው ልጅ አገልግሎት ላይ ያተኮረ ነው

የጥር ወር 2013 ዓ.ም የጸሎት ዓላማ

ኢየሱስን ተከትለን ወደ እግዚአብሔር ስንጸልይ እንደ ሌሎች ባህሎች ፣ ሌሎች ወጎች እና ሌሎች እምነቶች ከሚጸልዩ ሰዎች ጋር እንደ ወንድም እና እህቶች እንሰበሰባለን።

እኛ የምንጸልይ ወንድሞች እና እህቶች ነን ፡፡

ወንድማማችነት እራሳችንን የሁላችንም አባት ለሆነው እንድንከፍት እና ከሌሎች ወንድሞቻችን ወይም ደግሞ እህቶቻችን ጋር እንድንገናኝ ያደርገናል ፣ ህይወታችንን እንድናጋራ ወይም እንድንደግፍ ፣ እንድንዋደድ እና እንድንተዋወቅ ያደርገናል።

ቤተክርስቲያን ለሰው ልጆች ክብር እና የወንድማማችነት ምንጭ ለምንሆን ለእኛ ለክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ መሆኑን ሳትዘነጋ በሌሎች ሃይማኖቶች ውስጥ የእግዚአብሔርን እርምጃ ትመለከታለች ፡፡

እኛ አማኞች ወደ ምንጮቻችን ተመልሰን አስፈላጊ በሆነው ነገር ላይ ማተኮር አለብን፣ ለእምነታችን አስፈላጊ የሆነው እግዚአብሔርን ማምለክ እና ባልንጀራን መውደድ ነው ፡፡

የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ከሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ሙሉ ህብረት ውስጥ እንድንኖር እና እርስ በእርሳችን ላለመዋጋት እና እርስ በእርሳችን እንድንፀልይ ለሁሉም እራሳችንን እንድንከፍት ጌታ ፀጋውን እንዲሰጠን እንፀልይ ፡፡

09 January 2021, 12:49